የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴት ብሄራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲዮም 10:00 ላይ ቡሩንዲ አቻውን ያስተናግዳል።
በፖናማ እና ኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2020 ከ20 አመት በታች ሴቶች አለም ዋንጫ ላይ ለመካፈል። የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ ያለው የሴት ብሄራዊ ቡድኑ ዛሬ በመልስ ጨዋታ ባህርዳር ላይ የቡሩንዲ አቻውን ይገጥማል። በመጀመሪያው ዙር ከሜዳው ውጭ 5-0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ያሸነፉት የኢትዮጵያ ከ20 በታች ብሄራዊ ብድኑ 95% የማለፍ ተስፋ ይዞ ወደ ሜዳ የሚገቡ ቢሆንም ጨዋታውን በቀላል የሚመለከቱት ጉዳይ አይሆንም። ትላንት በስህተት ወደ ድሬዳዋ ያቀኑት ቡሩንዲዎቹ ከብዙ ውዝግብ በኃላ ወደ ሚጫወቱበት ስፍራ ባህርዳር አመሻሽ ላይ ያቀኑ ሲሆን ልምምድ ሳያከናውኑ ነው ጨዋታቸውን ሚያደርጉት። ሀትሪክ ስፖርትም ብሄራዊ ቡድኑ መልካም እድል እንዲገጥመው ይመኛል።