የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ 42ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በአዳማ ከተማ አካሂዷል።
ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
በጉባኤው 12 ዋና ዋና አጀንዳዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የ2016 የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦም ምክክር ተደርጎበታል።
በጉባኤው የፋይናንስ እና ኦዲት ሪፖርት ተመርምሮ ፀድቋል።
የቀጣይ አራት አመታት ስትራቴጂካዊ እቅድ መፅደቁም ተገልጿል።
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን ለቀጣዮቹ አራት አመታት ለመምራት ብቸኛ እጩ ሆነው የቀረቡት የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኮሚቴው ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
ዶክተር አሸብር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት መምራታቸው ይታወሳል።
Managing Editor at Hatricksport Website