ዋልያዎቹ በዛሬው ዕለት ልምምድ ሰርተዋል !

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሳምንታት የኒጀር ቆይታ በኋላ በትላንትናው ዕለት በመጪው ማክሰኞ የመልስ ጨዋታውን ለማካሄድ ትላንት ምሽት ኢትዮጵያ በመግባት ቦሌ በሚገኘው የጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ማረፋቸው ይታወሳል ።

ቡድኑ ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ ባህር ዳር ለማቅናት የአየር ቲኬት የተቆረጠለት ቢሆንም በወቅታዊው ሀገራዊ ሁኔታ ጉዞ ሳይሳካ ቀርቷል ። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ረፋድ ላይ ሙሉ የቡድን ስብስቡ የተለመደ ልምምዱን በአዲስ አበባ ስታዲየም ለመስራት መቻላቸውን ለማወቅ ተችሏል ።

ኢትዮጵያ በመጪው ማክሰኞ የኒጀር አቻቸውን ሲያስተናግዱ ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም የመካሄድ ከፍተኛ ዕድል አለው ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor