የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የነበረዉን አሰልጣኝ ዉበቱ አባተን አፄዎቹ በይፋ የክለባቸዉ አሰልጣኝ አድርገዉ ቀጥረዋል።
የ2014 ዓ/ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆን የቻሉት አፄዎቹ በ3 ዓመት ኮንትራት አሰልጣኙን የግላቸዉ ማድረጋቸዉን በአሁን ግዜ በጁፒተር ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘዉ የፊርማ ስነ ስርአት እና ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልፀዋል።
አሰልጣኙ ፋሲል ከነማን በወር 415,000 (አራት መቶ አስራ አምስት ሺህ) ብር እየተከፈላቸዉ እንደሚያሰለጥኑም ተገልጿል።