በቀጣይ በካፍ ኮንፌዴሬሽን የሚሳተፉት የጣና ሞገዶቹ በተጫዋቾች የዝዉዉር መስኮት የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ፤ባለፈዉ ሳምንት የፍሬዉ ሰለሞንን ዝዉዉር ያጠናቀቁት የጣና ሞገዶቹ ዛሬም ግብ ጠባቂ ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።
ያለፈዉ የዉድድር አመት በሀዋሳ ያሳለፈዉ ግብ ጠባቂ አላዛር ማርቆስ በቀጣይ የባህርዳር ከነማ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል፤ ተጫዋቹ የሁለት አመት ኮንትራት ከባህርዳር ከነማ ጋር ተፈራርሟል።