በተጠናቀቀዉ የውድድር አመት ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደግ የቻለዉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዝውውር ገበያዉ ላይ በመንቀሳቀስ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ በመቀላቀል ላይ ሲገኝ አሁን ደግሞ የመስመር ተከላካይ ማስፈረሙ ታውቋል።
በዚህም የአዲስ አዳጊዉ ክለብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሌላኛዉ ፈራሚ ሁኖ ክለቡን የተቀላቀለዉ የመስመር ተመላላሹ ሱለይማን ሀሚድ መሆኑ ታውቋል ፤ ከሀዲያ ሆሳዕና ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካመራ በኋላ ጥሩ የሚባሉ ሁለት አመታትን በፈረሰኞቸለ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ ተጫዋቹ ከአመታት ቆይታ በኋላ በሁለት አመት ዉል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።