የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር 119 ጨዋታዎች የተደረጉ ሱሆን ይህ ዙርም ነገ ሰኞ በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ በሚያደርጉት ጠዋታ መቋጫውን ያገኛል።

ጨዋታ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ
የጨዋታ ቀን፡ ሰኞ ታህሳስ 16/2012
የጨዋታ ቦታ፡ አዲስ አበባ ስታድዮም
የጨዋታ ሰዓት፡ 10፡00
የጨዋታ ዳኛ፡ ኢንተርናሽናል አርቢትር ዶ/ር ሃ/ የሱስ ባዘዘው

የ15ተኛው ሳምንት መቋጭቅ እና ብቸኛው የሰኞ መርሀ ግብር ከ ሶስት አመት በኋላ ዳግም ወደ አስፈሪነቱ የተመለሰውን ቅዱስ ጊዮርጊስ እና በተጨዋቾች ደሞዝ መክፈል አቅቶት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን አዳማ ከተማ የሚያገናኝ ይሆናል። ይህ ጨዋታ ትናንት (ቅዳሜ) ሊደረግ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ዝግጅት ምክንያት ወደ ሰኞ ሊዛወር ችሏል።

ፈረሰኞቹ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ጎንደር ተጉዘው በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ፋሲል ከተማ ጋር 2-2 በመውጣት መሪነታቸውን ያስቀጠሉ ሲሆኑ የነገ ተጋጣሚያቸው አዳማ ከተማ ደግሞ ምንም እንኳን ቡድኑ ውስጥ የተረጋጋ ስሜት ባይኖርም በ14ተኛው ሳምንት መርሀግብር በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ወልዋሎ አዲግራትን 2-0 በማሸነፍ ወደ ትግራይ ሸኝቶታል።

ሶስቱ የአዳማ ከተማ ኮከቦች ዳው ሁጤሳ፣ ከንዓን ማርክነህ እና ምኞት ደበበ ደሞዝ በአግባቡ አልተከፈለንም በማለት ለክለቡ መልቀቂያ እንዳስገቡ ለማወቅ ተችሏል። ይሄም ዜና በነገው ጨዋታ በቡድኑ መንፈስ ላይ ከባድ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

በሰርቢያዊው አሰልጣኝ እየተመሩ ሊጉን እየመሩ የሚገኙት ፈረሰኞቹ በነገው ጨዋታ ከዚህ ቀደሞ የሚከተሉትን አሰላለፍ እና የተጨዋቾች ምርጫ ይከተላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከፋሲል ጋር በነበረው የ14ተኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ ከበርካታ ጊዜያት በኋላ በቡድኑ ቋሚ 11 ውስጥ መካተት የቻለው አጥቂው አሜ መሐመድ በነገው ጨዋታ ላይም ቋሚ ሆኖ ሊጫዋት እንደሚችል ይገመታል።

ባስላፍነው ሳምንት ጉዳት ያጋጠመው የመስመር ተጨዋቹ ጋዲሳ መብራቴ በነገው እለት እንደማይሰለፍ የታወቀ ሲሆን ጉዳቱ ቀጣይ 10 ቀናትን ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችል ታውቋል። በተጨማሪም ናትናኤል ዘለቀ እና አቤል እንዳለ ከጉዳታቸው ያላገገሙ ሲሆን ደስታ ደሙ ደግሞ በቅጣት የማይኖር ይሆናል። በአዳማ ከተማ በጉዳትም ይሁን በቅጣት በኩል አዲስ ነገር እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።