በሁለቱም ክለቦች በኩል በፕሪሚየር ሊጉ ከሚጠቀሙባቸው ተጫዋቾች በመጠኑ ያሰለፉ ሲሆን ለታዳጊ ተጫዋቾች ቦታ መስጠት ችለዋል፡፡
በአርባምንጭ ከነማ አማካኝነት የተጀመረው የመጀመሪያው አጋማሽ መጠነኛ ፊክክሮችን መመልከት ስንችል የመጀመርያወቹን 20ደቂቃዎች እንግዳዎቹ ኢትዮጵያ ቡናዎች ተጭነው መጫወት ችለዋል፡፡ ገና በተጀመረ በ5 ደቂቃ ታዳጊው ተጫዋቾች ሚኪያስ መኮንን ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ ሲችል በ10ኛው ደቂቃ የአዞዎቹ ተጫዋቾች የሰሩትን ጥፍት ተከትሎ ሳሙኤል ሳኑሚ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ አገባው ብሎ ሲጠበቅ ወደ ውጪ የመታው ኳስ ቡናማዎቹን ቀዳሚ ምታደርግ ነበረች፡፡ እንዲሁም በመልሶ ማጥቃጥ አዞዎቹ በግራ መስመር ታገል አበበ በቀጥታ ወደ ግብ የመታውን ኳስ ሃሪሰን አድኖበታል፡፡
ከዚህም ሙከራ በሃላ በተደጋጋሚ ወደ ግቡ የደረሱት ኢትዮጲያ ቡናዎች ሊፍታቸው ሰምሮ መሪ የምታደርጋቸውን ግብ ማስቆጠር ችለዋል፡፡ በ16 ደቂቃ የአርባምንጩ ተከላካይ በረከት ቦጋለ እና ግብጠባቂው አንተነህ መሳ በፈጠሩት የመናበብ ችግር ተከትሎ በአቅራቢያው የነበረው ቁመተ ለግላጋው ባፕቲስቴ ፋዬ በአግባቡ በመጠቀም ቡናማዎቹ መሪ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
ከጎሉ መቆጠር በኀላ ኢትዮጵያ ቡናዎች ወደ ኀላ በማፈግፈግ ግብ እንዳይቆጠርባቸው በህብረት መከላከልን ሲመርጡ ባለሜዳዎቹ አርባምንጮች ኳስን መስርተው በመጫወት የተጋጣሚያቸውን ግብ ክልል ሰብረው ለመግባት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል፡፡
ለዚህም ማሳያ በ25ደቂቃ ፍቃዱ ደነቀ እንዲሁም በ31ደቂቃ በረከት አዲሱ ለግብ የቀረቡ ሙከራወች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የእንግዳዎቹ ኢትዮጵያ ቡና አጫዋወት የተመቻቸው ባለመዳዎቹ አዞዎቹ በ36ደቂቃ የአቻነት ግብ ማስቆጠር ሲችሉ በቀኝ መስመር ታገል አበበ ያሻማውን ኳስ በሁለተኛ ዙር ከጋሞ ጬንቻ ቡድኑን የተቀላቀለው ፍቃዱ ደነቀ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል፡፡
በዚህም መሰረት የመጀመሪያው አጋማሽ 1-1 በሆነ የአቻ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል፡፡
በሁለተኛ አጋማሽ ሁለቱም ብድኖች ተዳክመው የታዩበት በሙከራ ረገድ እንግዳዎቹ አትዮጵያ ቡና ተሽለው የተገኙበት ነበር በ74 ደቂቃ ሚኪያስ መኮንን የመታው ኳስ በግቡ አግዳሚ ስትወጣ በ79ደቂቃ ሳኒሙ ጣጣውን ጨርሶ ያቀበለውን ኳስ ባፕቲስቴ ወደ ውጪ የመከሩት አጋጣሚዎች ተጭነው ለመጫወታቸወው ተጠቃሽ ነበሩ፡፡
አዞዎቹ በመሀል ላይ ብቻ የተገታ አጨዋወት መጫወታቸው ወደ ተቃራኒ ግብ ክልል ዘልቀው እንዳይሄዱ አድርጓቸዋል ለዚህም ማሳያ አጥቂው በረከት አዱሱ መሀል ሜዳ ወርዶ ለመጫወት ሲሞክር ተስተውለዋል፡፡ በ81ደቂቃ ብርሀኑ አዳሙ ለግብ የቀረበ ሙከራ ከማድረጉ ውጪ ይህ ነው የተባለ ሙከራ ማድረግ ሳችሉ ቀርተዋል፡፡

ጨዋታ ሊጠናቀቅ 3ደቂቃ ሲቀረው በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ታዳጊው ሚክያስ መኮንን ከግብጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ሲመልስበት በአቅራቢያው የሚገኘው መሱድ መሀመድ አገባው ሲባል አድነት አዳነ በግንባሩ ያወጣበት አጋጣሚ የቡናማዎቹን የጎል መጠን ወደ ሁለት ከፍ የምታደርግበት አጋጣሚ ነበረች፡፡
የመደበኛ ጨዋታ ክፍለ ግዜ 1-1 በመጠናቀቁ በተሰጡት መለያምቶች እንግዳዎቹ ኢትዮጲያ ቡና 5-3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍቸውን አረጋግጠዋል፡፡
አስተያየት ይስጡ