መነሻ ገጽ The BiG Interview “የእኛ ስንብት የዲስፕሊን ኮሚቴውና ፌዴሬሽኑ በአንድ ሳምባ እንደሚተነፍሱ ያረጋገጠ ነው”አቶ ጳውሎስ ተሰማ (የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ�)
The BiG Interviewዜናዎች

“የእኛ ስንብት የዲስፕሊን ኮሚቴውና ፌዴሬሽኑ በአንድ ሳምባ እንደሚተነፍሱ ያረጋገጠ ነው”አቶ ጳውሎስ ተሰማ (የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ�)

አጋራ
አጋራ


ሀትሪክ፡-የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴን በይፋ በትኗል፤ ከዚህ
ኃላፊነት መሰናበታችሁን የሰማኸው እንዴት
ነው?

አቶ ጳውሎስ፡- መጀመሪያ ላይ
ስለመሰናበታችን ምንም የማውቀው ነገር
አልነበረም፤ ከዚህ በፊት እንደነበረው የስራ
ግንኙነት ከፌዴሬሽኑ ስልክ ተደውሎ
“ደብዳቤ አለህ መጥተህ ውሰድ” አሉኝ፡
፡ ቀደም ሲል ደብዳቤ ሲኖረን ከፌዴሬሽኑ
ተደውሎ “የት ነው ያለኸው? ደብዳቤ
ልንልክልህ ነበር” የሚል ነገር ስለተለመደ
አባባሉ ከተለመደው የወጣና አዲስ ነገር
ሆነብኝ፡፡ ወዲያወኑ የእነሱን ስልክ እንደዘጋሁ
ለፀሐፊያችን ከፌዴሬሽን ደብዳቤ አለ ውሰዱ
ብለዋልና ሂደህ ተቀበል አልኩት፡፡ በወቅቱ
ስራ በጣም በዝቶብኝ ስለበር ሳልደውልለት
ቆየሁና ከሁለት ቀን በኋላ ደውዬ እንዴት
አደረክ ደብዳቤው ሄደህ ተቀበልክ? ስለው
“አይ ለአንተ አንሰጥም፤ እሣቸው ራሣቸው
መጥተው ይወስዱ” ተብሏል አለኝ፤ ይሄም
ያልተለመደ ስለሆነ ይሄን ያህል ምን ቢሆን
ነው በአካል ሄጄ እንድወስድ የተፈለገው?
ብዬ ራሴን ከመጠየቅ ውጪ ሌላ ክፉ ነገር
በአዕምሮዬ አልመጣም፤ ሄድኩኝ ደብዳቤውንተቀበልኩ፤ ከፍቼ ሳየው በጣም ተገረምኩ፡፡

ሀትሪክ፡-…ለምን ተገረምክ… ያልጠበከው
ነገር ስለሆነ ነው… ?

አቶ ጳውሎስ፡- ደብዳቤውን ከፍቼ
ሳየው ጉዳዩ ስንብት ይላል፤ “ግንቦት 20
ቀን የኢመርጀንሲ ኮሚቴ ከዲሲፒሊንና
ከይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ጋር ባደረግነው ስብሰባ
የስብሰባው ሪፖርት ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
ቀርቦ ውሳኔዎች ልዩነት ስላመጡ የይግባኝ
ሰሚ ኮሚቴን ማሰናበቱን አምነንበታል”
ይላል፡፡ ያነበብኩትን ማመን አቃተኝ በጣም
ገረመኝ፤ምክንያቱም ደብዳቤው እስከደረሰን
ሰዓት ድረስ ስራችንን በአግባቡ እየሠራን
ስለነበር ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴውን ለስንብት
የሚያበቃ አንዳችም ጥፋት፤ አንዳችም የህግ
ምክንያት አልነበረም፤ ፌዴሬሽኑ ግን ይሄንን
ነው ያደረገው፡፡

ሀትሪክ፡- ፌዴሬሽኑ ይሄንን ውሳኔ
ከመወሰኑ፤ የይግባኝ ሰሚ ኮሜቲውን
ከማሰናበቱ በፊት ግንቦት 20 ቀን የዲሲፒሊንም
የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ አባላትንም ጠርቶ
አነጋግሯል። ፌዴሬሽኑ ይሄንን የማድረግ
የህግ መሠረት ወይም ድጋፍ አለው…?

አቶ ጳውሎስ፡- በነገራችን ላይ ይሄ
ግንቦት 20 የተደረገው ኢመርጀንሲ ኮሚቴ
የጠራው ስብሰባ በጣም የሚያስደነግጥ ብቻ
ሣይሆን ይሄን የማድረግ የሕግ መሠረትም
የላቸውም፤ ይሄ ማለት እኮ በየትኛውም
የፍትህ ስርዓት የሌለ ነው። የሕግ ባለሙያ
ያልሆኑ ሰዎች እንዲህ አንተን አስቀምጠው
የሚወስኑ ከሆነ ቃል በቃል ነው የምለው
አንተ ባለሙያ ሳትሆን አሽከር ነህ ማለት
ነው፡፡

ሀትሪክ፡-የሕግ መሠረት ከሌላቸው፤
እንዳልከውም አሽከርነት ከሆነ ለምን
ሲጠሯችሁ በስብሰባው ላይ ተገኛችሁ?

አቶ ጳውሎስ፡-እኛ መች በዚህ ጉዳይ
ላይ መሆኑን አወቅንና? እኛን የመሰለን
ወይም የጠሩን የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊ
ሕጎች በአብዛኛው ጥሩ ነገሮች እንዳሉት
ሁሉ በርካታ ችግሮችም ስላሉበት በተለያዩ
ጊዜያቶችም በዚህ ዙሪያ እንወያይ እንነጋገር
ስለነበር በዚህ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር
የጠሩን ነበር የመሰለን፡፡ ገብተን ለስብሰባው
እንደተቀመጥን ግን ፌዴሬሽኑም የዲሲፒሊን
ኮሚቴውም ተዘጋጅተው፣ ማስታወሻቸውን
ይዘው ተቀምጠዋል፡፡ የምናየውን ማመን
አልቻልንም በመሃል ፕሬዚዳንቱ አቶ
ኢሳያስ “ዛሬ ሁለታችሁንም የጠራናችሁ
በእናንተና በዲሲፒሊን ኮሚቴው መካከል
ያለውን ሁኔታ ለማወቅና በአንዳንድ ልዩነት
ባመጡ ውሣኔዎች ላይ ለመነጋገር ነው” ብሎ
በመቀጠል “እስቲ ጳውሎስ የምትለው ነገር
ካለ?” ይለኛል…

ሀትሪክ፡-… ምን መልስ.. ሰጠህ…?

አቶ ጳውሎስ፡-ፌዴሬሽኑም የዲሲፕሊን
ኮሚቴው ሰብሳቢም ማስታወሻ ይዘው
ተዘጋጅተው መምጣታቸው እንዲሁም
የፕሬዚዳንቱ ንግግር የስብሰባውን ፍንጭ
ጠቆመኝ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ተናገር ባለኝ መሠረት
በእኛና በዲሲፒሊን ኮሚቴ መካከል ችግርም
አለመግባባትም ልዩነትም የለም፡፡ እንደ ህግ
ባለሙያ እንተዋወቃለን፤ ከሰብሳቢው ጋርም
እንተዋወቃለን ፍ/ቤትም እንገናኛለን፤ከዚህ
ውጪ ግን የተለየ ግንኙነትም ፀብም የለንም፡
፡ እኔ የማውቀው ይሄንን ነው፤ ሌላ ከዚህ
ውጪ የሚባል ነገር ካለ እንስማውና መልስ
የምንሰጥበት ይሆናል አልኩኝ። በመቀጠል
“አንተስ ምን የምትለው አለ?” ብለው
ፕሬዚዳንቱ የመናገር እድሉን ለዲሲፒሊን
ኮሚቴው ሰብሳቢ ስጡ፤ እሳቸውም
ማስታወሻቸውን እያገላበጡ አንደኛ…
ሁለተኛ… በማለት ይሄን… ይሄን… እኛ
የወሰነውን የሻሩት አለአግባብ ነው በማለት
ክሳቸውን ደረደሩ፡፡ በወቅቱ ይሄ ሁሉ ሲደረግ
እኛ ቁጭ ብለን መስማት አልነበረብንም
ነበር፤ አንዴ ከመጣን ግን እስቲ እንስማቸው
ብለን ሰማናቸው፡፡ አሰባሰቡ ሰህተት እንደሆነ
ብናውቅም አንዴ መጥተናል ለጠሩን
ሰዎች ክብርም ብለን እስኪጨርሱ ጠበቅን፤
የዲሲፒሊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አለ ያሉትን
ኃጢአት በእኛ ላይ ዘርዝረው ከጨረሱ በኋላ
አድሉ ወደ እኛ መጣ፡፡

ሀትሪክ፡- …ምን ምላሽ … ሰጣችሁ…?

አቶ ጳውሎስ፡- …በመጀመሪያ ያልነው
የኢመርጀንሲ ኮሚቴውም ሆነ የስራ አስፈፃሚ
ኮሚቴው በፍትህ ጉዳይ ላይ እኛን የማነጋገር
ስልጣን የለውም፤ይሄ ከስልጣናችሁ ውጪ
ነው። እዚህ አሁን የተቀመጥነውም ለእናንተ
ክብር ሰጥተን አንዴ መጥተናል እስኪ
እናስጨርሳችሁ ብለን እንጂ በፍትህ ጉዳይ
ላይ የማነጋገር የህግ መሠረቲም እውቀቱም
የላችሁም፡፡ ይሄም ቢሆን ደግሞ እናንተን
ለማስረዳት ምን ማለት እንደምንችል ቀድሞ
ተነግሮኝ ቢሆን ኖሮ እነዚህን ውሳኔዎች በዚህ
በዚህ ምክንያት ነው የሻርነው የዲሲፒሊን
ኮሚቴው ስህተቶችም ይሄ ይሄ ነው ብለን
መልስ መስጠት እንችል ነበር፤እኛ በዚህ
በኩል ችግር የለብንም፡፡ አሁን ግን እኛ ብዙ
ኃላፊነቶች በርካታ ስራዎች ያሉን ሰዎች ነን፡
፡ ውሳኔዎችን በሙሉ በቃላችን ሸምድደን
አንይዝም፤አንዴ ቢሮ ውስጥ ሰራን ጨረስን
ወጣን። ከዚያ በኋላ በነጋታው ብትጠይቁን
እንኳን ውሳኔውን ማስታወሻችንን ካላየን
አናስታውሰውም በቃ፡፡ ይሄ ስብሰባ ለእኛ
የሚጠቁመን ፌዴሬሽኑ አጓጉል አካሄድ
እየሄደ መሆኑን የሚያሳይ ነው አልን፤ በዚህ
ስብሰባው ተበተነ። ከዚያ በኋላ ከአመራሮቹ
ጋር አልተገናኘንም… በቃ ከስብሰባው በኋላ
የደረሰን የስንብት ደብዳቤ ብቻ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- በአንተ እይታ
ሁለታችሁን አነጋግረው እናንተን
በዚህ መልኩ ማሰናበታቸው
ተቀባይነት አለው ትላለህ…
? ስንብቱስ ምን ትርጉም ይሰ
ጥሃል…?
አቶ ጳውሎስ፡- ይሄ ውሳኔ
አንድ ነገር ይበልጥ ቁልጭ
አድርጎ አሣይቶናል፤ የዲሲፒሊን
ኮሜቲውና ፌዴሬሽኑ አብረው
እንደሚሰሩ የዲሲፒሊን ኮሚቴው
የሚወስናቸው ውሳኔዎች በሙሉ
የፌዴሬሽኑ ውሳኔዎች እንደነበሩ
ይህ ሁኔታ ምስክርነቱን ይሰጣል፡
፡ በአጭሩ የዲስፒሊ ኮሚቴውና
ፌዴሬሽኑ በአንድ ሣንባ
ሲተነፍሱ እንደነበር የሚመሰክር
ነው ፤ሁለቱም አብረው ስብሰባ
ጠሩን ሁለቱም ማስታወሻ
ይዘዋል፡፡ ይሄ ራሱ የሚናገረው
ነገር አለ፡፡
ሀትሪክ፡ – … ፌዴሬሽኑስ
እናንተን የማሰና በት ማንዴቱ
አለው…?
አቶ ጳውሎስ፡- …በፍፁም
የለውም…!ደግሞም እኮ እኛን
ለሰንብት የሚያበቃ አንዳችም
ጥፋት አላጠፋንም፡፡ የይግባኝ
ሰሚ ኮሚቴው የተዋቀረው እኮ
የደሲፒሊ ኮሚቴው የወሰናቸውን ውሳኔዎችን
ተከትሎ ይግባኝ ባይ ቢመጣ ውሳኔዎችን
ሊያሻሽል፣ ሊያፀና አሊያም ለመሻር እኮ ነው፡
፡ የዲሲፒሊ ኮሚቴ የወሰናቸውን ውሣኔዎች
ለማፅናት ብቻ ከሆነ የተቀመጠው የይግባኝ
ሰሚ ኮሚቴ ማቋቋም ለምን ያስፈልጋል?
በማንኛውም የፍትህ ስርዓት ውስጥ የተበላሸ፣
የተሳሳተ ነገር ካለ እንዲስተካከል ትክክለኛውን
ደግሞ ለማፅናት ነው፡፡ ሌላው ፌዴሬሽኑ
የማሰናበት ስልጣን አለው ወይ? ላልከው
መልሴ የለውም ነው፤ይሄንን ተከትሎ በዚህ
በደንቡ ላይ ፌዴሬሽኑ የተሰጠው ስልጣን
ምንድነው… የፍትህ ውሳኔዎች በፍትህ
አካሉም ጭምር ተጥሷል ብሎ ካመነ
ይግባኝ ማቅረብ ይችላል ነው የሚለው፡፡ እኛ
አላጠፋንም እንጂ የህግ ጥሰት ፈፅመን ብንገኝ
እንኳን ውሳኔዎቹን አላመንኩባቸውም ብሎ
ፌዴሬሽኑ ካመነ እኛን በሁለት መስመር
ደብዳቤ ማሰናበት ሣይሆን ለካስ አቤቱታ
አቅርቦ አስተማሪ ውሳኔ አስወስኖ ሊያሳየን
ይገባ ነበር፡፡
ሀትሪክ፡- የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው
ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ምከንያት ናቸው
ተብለው ከቀረቡት ውስጥ የደሲፒሊ ኮሚቴው
የሚወስናቸውን ውሳኔዎች በተደጋጋሚ
ሆን ተብሎ በሚመስል መልኩ መሻራችሁ
ይጠቀሳል፤ ይህ የሆነው በአጋጣሚ ነው?
ወይስ ሁለታችሁም የሕግ ባለሙያዎች
በመሆናችሁ በመካከላችሁ አለመግባባት…
የግል ፀብ… ወይም… የተቀናቃኝነት የፉክክር
ስሜት አለ…?
አቶ ጳውሎስ፡- …(እንደ መሳቅ እያለ)…
በጣም የሚገርምህ… ልክ አንተ በጥያቄህ
እንዳነሳኸው ሁሉ ብቸኛዋ የፌዴሬሽኑ ሴት
ስራ አስፈፃሚ የሆኑት የተከበሩ ወ/ሮ አይሻ
ምን እንዳሉ ታውቃለህ? “እኔ እንደውም
የመሰለኝ የአለመግባባታችሁ ምክንያት
ሕጉ ሣይሆን በመካከላችሁ ፀብ ያለ ነው
የመሠለኝ” ብለውን ነበር፡፡ እኔ በወቅቱም
መጀመሪያ ላይ ስጠየቅም በግልፅነት
ተናግሬያለሁ፤ በመካከላችን ምንም ቂምና
በቀልም የለም፡፡ እኛና የዲሲፒሊን ኮሚቴው
ሰብሳቢ ሙያችን አንድ በመሆኑ ፍ/ቤት
እንገናኛለን፤ከዚህ ውጪ የሚያገናኘን ነገር
የለም፤ የየራሣችን ስራ ነው የምንሰራው፡፡
ምንአልባት በመካከላችን የተፈጠረ ነገር አለ
ቢባል እንኳንየሙያ ልዩነት እንጂ ሌላ ነገር
የለም፡፡ ምናልባት እኛ የማናውቀው እነሱ
በእኛ ላይ የያዙት ቂም ካለ አናውቅም፤ ከዚህ
ውጪ እኛ ችግር የለብንም፡፡
ሀትሪክ፡- የዲሲፒሊን ኮሚቴው “እኛ
የምንወስናቸው ውሳኔዎች በይግባኝ ሰሚ
ኮሚቴው ሆን ተብለው እየተሻሩ እንድንጠላ
እየተደረገ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ለመልቀቅ
እንገደዳለን” የሚል ነገር አንሰተዋል፤
ከዚህ ሌላም ውሳኔዎች የሚሻሩት ሕግና
አንቀፅ ጠቅሳችሁ አይደለም በማለትም
ትወቀሳላችሁ… ወቀሳውን ትቀበለዋለህ…?
አቶ ጳውሎስ፡-… (በጣም… ሳቅ) …
ይሄንን ነገር በተለይ የዲሲፒሊን ኮሚቴው
አባላት ብለውት ከሆነ በጣም ትልቅ ስህተት
ብቻ ሣይሆን የሚገርም ነገር ነው፤ እኛ
እንደውም በተሻለ ሕግና ደንብ ጠቅሰን
በደንብ አብራርተን ነው ስንሽርም ስናፀናም
የነበረው፡፡ እኛ ውሳኔዎችን ስናፀናም ስንሽርም
የነበረው አስተማሪ በሆነና በማያሻማ መልኩ
ነው፡፡ አንድ ውሳኔን እንደ እነሱ በአንድ ገፅ
ሣይሆን ቢያንስ በአራትና በአምስትገፅ በጣም
ዘርዘር አድርገን አንቀጾችን ጠቅሰን እንደውም
ከእኛ አልፈን የፊፋና የካፍን አንቀጾች ሁሉ
እንደ አስፈላጊነታቸው ተጠቅመን ነው
፤ከዚህ አንፃር እንጂ ዝም ብለን በደፈናው
የምንወስነው ነገር የለም፡፡


ሀትሪክ፡- …እውነታው ይሄ ከሆነ ታዲያ
በዲሲፒሊንና በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው መካከል
ያለውን ልዩነት ከምን ጋር እናያይዘው… ?
አቶ ጳውሎስ፡- …ፌዴሬሽኑን ወደተሳሳተ
መንገድ የሚወስደው ይሄ የዲሲፒሊን
ኮሚቴ ሰብሳቢ ነው፤ ይሄ ግለሰብ ላለፉት
10 አመታት ከመጣው ፌዴሬሽን ጋር ሁሉ
አብሮ እዚህ ቦታ ላይ አለ፡፡ የፍትህ አካሉ
ትልቁ ችግር ወይም ምክንያት ነው ብዬ
የማስበውም ይሄንን ግለሰብ ነው፡፡ ይሄ ሰው
የዲሲፒሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኖ 10 አመት
ነው የተቀመጠው፡፡ አንተ ነፃ አገልጋይ
(Volunteer) ሆነህ 10 አመት ሙሉ አንድ
ቦታ ላይ ምን ትሰራለህ? አንድ አመት…
ሶስት አመት… አራት አመት… ልትሠራ
ልታግዝ ትችላለህ፤ ይሄ ግለሰብ ግን ነፃ
አገልጋይ ሆኖ 10 አመት ነው የተቀመጠው፡
፡ የተወሰነ አመት አግዘህ ልቀቁኝ ብለህ ወደ
ስራህ ትሄዳለህ እንጂ 10 አመት በዚህ መልኩ
መቀጠል ሌላ ትርጉም ያሰጣል፡፡ በጣም
የሚገርምህ ችግሮች እየተፈጠሩ ይሄ ግለሰብ
እየለመነ ነው የሚገባው፡፡ በዚህ ስራ አስፈፃሚ
ዘመን “ከዛሬ ጀምሮ አልሰራም፤ እለቃለሁ”
ብሎ ጥያቄ አቅርቦ ኮለኔል አወል ጥያቄውንም
“ተቀብለናል” ብሎ መልስ ከሰጠው በኋላ
እንደገና መልቀቁ ቆጨው መሰለኝ ትንሽ
ልስራ ብሎ ለምኖ የተመለሰ ሰው ነው፡፡ ይሄ
ግለሰብ ፌዴሬሽኑን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ
ከመውሰዱ ውጪ ላለፉት 10 አመታት
የፌዴሬሽኑ አመራሮች ላይ ተፅዕኖ አየፈጠረ
እኔ እንደዚህ ነው ያደኩት… ተጫውቼ ነው
ያለፍኩት ለስፖርቱ ነው የምሰራው የሚሉ
ቃላቶችን በመጠቀም ተፅዕኖ ሲፈጥር ነው
የኖረው፡፡ ከዚህ ሌላ፣ በተለያዩ ስብሰባዎች
ላይ እንዳየነው በተናጠል የእኛን ስም እየጠቀሰ
በማይመለከተው ጉደይ እየገባ ከስራው ውጪ
የፌዴሬሽኑ ተቆርቋሪ ለመምሰል እከሌ በዚህ
ቀን ፌዴሬሽኑን ተቸ…. እንዴት ፌዴሬሽኑን
ይነካል? እያለ የሚሟገት ሰው ነው፡፡ አሁን
በቅርቡ እንኳን ቅዱስ ጊዮርጊስ በሸራተን አዲስ
ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ፅሁፉ
እንዳቀርብ በክለቡ ተጋብዤ በተሰጠኝ ርዕስ
ላይ ንግግር በማድረጌ ኤመርጀንሲ ኮሚቴው
በጠራው ስብሰባ ላይ እንኳን ፌዴሬሽኑን
ተችቷል በማለት ከአጀንዳ ውጪ ያቀረበ ሰው
ነው፤ እኔ የፈለኩትን ባቀርብ ይሄ ግለሰብ
ምን ያገባዋል? እንዲህ የማለትስ መብት
አለው?ሌላው አንድ ትልቅ ነገር ልንገርህ…
ሀትሪክ፡-…ምን …?
አቶ ጳውሎስ፡- …ይሄ ግለሰብ የዲሲፒሊን
ኮሜቴ ሰብሳቢ ቦታ ላይ የተቀመጠው ከሕግ
ውጪ ነው ለአኔ…
ሀትሪክ፡-…ከሕግ ውጪ ስትል…?
አቶ ጳውሎስ፡- …ይሄ ግለሰብ
የፌዴሬሽኑን የዲሲፒሊን ሕግ ካሻሻሉት
ስድስት ሰዎች አንዱ ነው፤ አንድ
የዲሲፒሊን ሕግም ይሁን ሌላ ሕግ ሲሻሻል
በርካታ ባለሙያዎች፣ባለድርሻ አካላት
ተወያይተውበት፣ ተተችቶ ነው መሻሻል
ያለበት፡፡ የፌዴሬሽኑ የዲሲፒሊን ሕግ ግን
ይሄን ግለሰብ ጨምሮ ስድስት ሰዎች ናቸው
ያሻሻሉት፡፡ ሌላው ትልቁ ነገር ማንኛውም
ሕግ አውጪ አካል መልሶ ሕግ ተርጓሚ
አካል ሊሆን አይችልም፤ በተከበረው ምክር
ቤት ውስጥ ሕግ የሚያወጡ አካላት መልሰው
ዳኛ ሆነው አላየናቸውም፡፡ ይሄ ግለሰብ
የዲሲፒሊን ሕጉን ካሻሻሉት ሰዎች አንደኛው
ሆኖ የዲሲፒሊን ኮሚቴው ሰብሳቢ ሆኖ በዚህ
ደንብ እንዴት ዳኛ ሆኖ ሊዳኝ ይችላል?
ምክንያቱም እንደ ፌዴሬሽኑ ሆኖ ይሄንን
የዲሲፒሊ መመሪያ አሻሽሎ አውጥቷል፤ይሄ
ግለሰብ ሲወስን እንደ ሕጉ ሣይሆን ያኔ
እንደወጣው እያለ ነው የሚወስነው፡፡ ይሄ
ደግሞ በሕጉ ላይ ትልቅ ክፍተት ይፈጥራል፤
ይሄንንም በኢመርጀንሲ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ
አንስተን ነግረናቸዋል፡፡ ሕግ አሻሽሎ ተመልሶ
ደግሞ በዳኘነት መቀመጡ በራሱ ችግሮች
ከዚህ እንዲጀምሩ ያደርጋል፡፡
ሀትሪክ፡-ከዲሲፒሊን ኮሚቴ ጋር በውሳኔ
ዙሪያ እንድትጋጩ ያደረገው አንደኛው
ምክንያት ኢትዮጵያ ቡና ላይ የገንዘብ
ቅጣት ተጥሎ እናንተ ማንሳታችሁ ነው፤
ይሄን ያደረጋችሁበት አሳማኝ ምክንያት
አላችሁ…?
አቶ ጳውሎስ፡- ነገሩ ምንድነው መሰለህ…?
…ኢትዮጵያ ቡናዎች የፌዴሬሽኑን ስራ
አስፈፃሚ ስለተሳደቡ የዲሲፒሊን ኮሚቴው
የገንዘብ ቅጣት ወስኛለሁ አለ፤ እኛ ጋር ይግባኝ
ቀረበ፡፡ ቡናዎች በወቅቱ ምንድነው ያደረጉት
የአንድ የስራ አስፈፃሚ ስም በማንሳት “እኛ
ላይ ተፅዕኖ ይፈጥርብናል፤ ችግሮች አሉብን
ይሄንን ፌዴሬሽኑ እንዲያይልን…” ብለው
ደብዳቤ ያስገባሉ፤ ፌዴሬሽኑም ማስረጃ
ይጠይቃቸዋል፤ ይሄ ልክ አልነበረም፡
፡ ምክንያቱም አንድ ሰው ይሄ ስጋት አለኝካለ ወይ አግባብ ነው ብለህ ትቀበላለህ
አልያም ውድቅ ታደርገዋለህ፡፡
ቡናዎች ማስረጃ ሲጠየቁ “እንዴት
እንጠየቃለን? በዚህ በዚህ ቀን ይፋ
ያደረጋቸው ችግሮች ላይ የእኛ ስጋት
በግልፅ ታይቷል፤ ስለዚህ እነዚህ
በቂ ምስክሮች ናቸው” ብለው
መልስ ሲሰጡ የዲሲፒሊን ኮሚቴው
ግን ፌዴሬሽኑ ተደፈረ፣ ተሰደበ
ብሎ ብር ይቀጣሉ፤ እኛ ጋር ይግባኝ
ቀርቦ ስናየው አንዳቸም የሚያስቀጣ
ነገር ልናገኝ አልቻልንም፡
፡ ውሳኔው በሕግ አግባብ
ስህተት ሆኖ ነው
ያገኘነው፡፡ ምክንያቱም የአንድ ግለሰብ
ወይም የአንድ ተቋም አካሎች ለተቋሟቸው
አቤቱታ ማቅረባቸው ብቻውን ሊያስቀጣቸው
አይገባም፡፡ ቡናዎች እኮ ፍትህ ነው
የጠየቁት፤ዲሲፒሊን ኮሚቴው ለመገናኛ
ብዙኃን የተደረገ አስመስለው ነው ያቀረቡት፤
ቡናዎች ለሶስተኛ ወገን ሳይሆን በደብዳቤ
ነው የጠየቁት፤ የተጠቀሰባቸው አንቀፅ ግን
እንዴት እንደጠቀሱት እራሱ ግራ ያጋባል፡፡
ከዚህ አንፃር አይተን ቡናዎችን የሚያስቀጣ
ምንም ነገር ስላጣን መተቸት ወይም ስጋትን
መግለፁ ለዚህ ስለማይዳርግ ቡናዎች ላይ
የዲሲፒሊን ኮሚቴው ያስተላለፈውን ውሳኔ
ውድቅ አድርገናል፡፡ ከዚህ ውሳኔ ጋር በተያያዘ
ለማሳያ የሚሆን አንድ ምሣሌ ላንሳልህ…
ሀትሪክ፡- …ይቻላል….?
አቶ ጳውሎስ፡- …አሰልጣኝ ዮሐንስ
ሳህሌ በሚዲያ ኢንተርቪው ሲሰጥ የእነ አቶ
ሳህሉን ፌዴሬሽንን ይተቻል፤ “ፌዴሬሽኑ
የአቅም ችግር አለበት፤ በሙያተኛም
አይመራም” ብሎ ይተቻል ፌዴሬሽኑ ደግሞ
ተደፈርኩ ተተቸሁ ብሎ ይቀጣዋል፡፡ በወቅቱ
አሰልጣኝ ዮሐንስ የተላለፈብኝ ውሳኔ አግባብ
አይደለም በማለት በሕግ ለመፋረድ ሲነሣ
እንደ አጋጣሚ እኔ ጥብቅና እቆምለታለሁ፤
ዮሐንስ ጉዳዩን ወደ መደበኛው ፍ/ቤት ወስዶ
ክስ ይመሰርታል፡፡ ፌዴሬሽኑ እኛ በፌዴራል
ፍ/ቤት ልንዳኝ ወይም ጉዳዮችን ሊታይ
አይገባም በፊፋና በካፍ ነው ጉዳዩ መታየት
ያለበት ይላሉ በእኛ በኩል ግለሰብን ባልተገባ
ውሳኔ ጥቅም አሳጥታችኋል ስለዚህ ይህ
ፍ/ቤት የመዳኘት ስልጣን አለው በማለታችን
የፌዴሬሽኑ በመደበኛ ፍ/ቤት አልዳኝም
ክርክር ውድቅ ሆኖ መጨረሻ ላይ ለዮሐንስ
ሳህሌ ፍ/ቤቱ ፈረደ፡፡ ከሶስት መቶ ሺህ ብር
በላይ እንዲከፈለው እንደተደረገ አስታውሳለሁ፡
፡ በጣም የሚገርምህ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን
ለማስቀልበስ እስከ ሰበር ድረስ ሄደው
አልተሳካላቸውም፡፡ ዮሐንስ ሳህሌ ያገኘው
የፍርድ ውሳኔ የስፖርቱን ጉዳዮች መደበኛ
ፍ/ቤት ወስዶ መርታት እንደሚችል ትልቅ
ማስተማሪያ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ
ፌዴሬሽን ከውሳኔው አንፃር በፍትህ ጉዳይ
ላይ ጣልቃ ገብቷል ብሎ መናገር ይቻላል…?
አቶ ጳውሎስ፡- …በደንብ እንጂ…! …
ፌዴሬሽኑ በፍትህ አካሉ ላይ ጣልቃ
እንደማይገባ መተዳደሪያ ደንቡ የዲሲፒሊን
መመሪያው ብሎም የፊፋና የካፍም ሕጎች
ላይ በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ፌዴሬሽኑ ጣልቃ
መግባቱን ተወው ኃላፊነቱ ምንድነው?
የሚለውን ስታይ ድርጊቱ ነውር እንደሆነ
ትረዳለህለህ፡፡ የፍትህ አካላቱ ስራቸው በአግባቡ
እየሠሩ ነው ወይ? ለምሣሌ የዲሲፒሊን ኮሚቴ
ጋ አቤቱታ ሲቀርብ የሚወስንበት የሚቀመጥ
የጊዜ ገደብ አለ… በዚያ የጊዜ ገደብ ወስነዋል
ወይ? ቶሎ ቶሎ ምላሽ ሰጥተዋል ወይ?
ወደ ይግባኝ ሰሚ በመምጣትም የዲሲፒሊን
ኮሚቴ ወይም ሌሎች ኮሚቴዎች የወሰኑት
ላይ ይግባኝ ሲባል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ
ፍትህ ሰጥተዋል ወይ? የፍትህ ስርዓቱ
እንዲቀላጠፉ አድርገዋል ወይ? በማለት
ሊፈትሽ ሊያስተባብር እንጂ በውሳኔ፣ በፍሬ
ነገር እንደውም “በፍሬ ነገር” ብሎ በግልፅ
ነው ያስቀመጠው ጣልቃ አይገባም ነው
የሚለው፤ ይሄ ተከብሯል ወይም ተጥሷል?
መልሱን ለአንተ ወይም ለአንባቢያን መተውን
እመርጣለሁ፡፡
ሀትሪክ፡-ሌላው ይግባኝ ሰሚም ሆነ
የዲሲፒሊን ኮሚቴ አባላት ላይ የሚነሣው
ትልቅ ጥያቄ ተጫውተው አለማለፋቸው
የመደበኛውን ሕግ እንጂ የስፖርቱን ሕግ
ጠንቅቀው አላማወቃቸው ለተፈጠረው ክፍተት
ምክንያት ነው ብለው ይወቅሷችኋል…
ወቀሳውን ትቀበላለህ…?
አቶ ጳውሎስ፡- …ምናልባት ኳስ
ተጫወቶ ያለፈ የሚባለው ለብ/ቡድን
የተጫወተ ወይም ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ
የጨረሰ ከሆነ አላውቅም፤ ከዚህ ውጪ ደግሞ
እኔ ተጫውቼ አልፊያለሁ እያሉ ማውራትም
ለመጫወትህ ማሳያው ከሆነ ይሄም ለእኔ
እንግዳ ነገር ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር
ካስፈለገ እኛም ተጫውተናል፤ እኔ የአንድ
ክለብ አይደለም አንድ ክልልን ጭምር በግብ
ጠባቂነት ያገለገልኩ የወከልኩ ሰው ነኝ፤
መጫወት በስፖርት ውስጥ ማለፉ ክፋት
ባይኖረውም የምትሰራው ስራ የህግ፣ የፍትህ
ስራ መሆኑ ግን መዘንጋት የለብትም፡፡ የሕግ
ባለሙያ ሆነህ በሕግ ዙሪያ ስትሰራ ሕጎችን
ነው የምታየው፤ ከሙያዬ ውጩ ላለፉት
10 አመታት ከስፖርቱ ያልራኩ፣ ስፖርቱን
የምከታተል፣ በሙያዬ ስፖርቱን ያገዝኩ፣
በስፖርቱ የተበደሉ ሰዎችን በመደበኛ ፍ/
ቤት ጭምር ያስከበርኩ ሰው ነኝ፡፡ እኛ እኮ
አሰልጣኞች አይደለንም የምናወራው ወይም
የምንሰራው ህግን እንጂ ቴክኒክና ታክቲክን
አይደለም።መነጋገር ካስፈለገ ግን ተጫውተን
አልፈናል፡፡
ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ በሸራተን
አዲስ ባዘጋጀው የስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ
ባጠነጠነው የውይይት መድረክ ላይ ካቀረብከው
ጥናታዊ ፅሁፍ ውስጥ ቀልቤን የሳበ አንድ
ነገር ነበር፤ የስፖርቱ ሕግና የወንጀል
ሕጉ አብረው ተጣምረው የሚሄዱበት ነገር
መፈጠር አለበት ብለሃል… እስቲ በዚህ ዙሪያ
ለአንባቢዎቼ ሃሳቡን ድገምላቸው…?
አቶ ጳውሎስ፡- …ይሄ በጣም ሊሰመርበት
የሚገባ ጉዳይ ነው… ዳኞች በአደባባይ፣
በተመልካች፣ በሚዲያ ፊት እየተደበደቡ
ክቡሩ የሰው ልጅ ስታዲየም ውስጥ በድጋፍ
አሰጣጥና ባለመግባባትም ይሁን በሌላ ተነሳስቶ
በተፈጠረ ችግር ተፈንክቶ ደሙ ሲፈስ አካሉ
ሲጎድል አይ ስታዲየም የውድድር ቦታ ነው
ብሎ የወንጀል ሕግ ተጠያቂነት እንደማይሰራ
አድርጎ ማሰብ ስህተት ነው፡፡ ድብደባ ስድብና
ዛቻ የትም ይሁን ወንጀል ነው፤ የወንጀል
ሕጉ ስታዲየም ውስጥ አይደለም የትም
እንደሚሰራ ማናችንም ሊጠፋን አይገባም፡፡
ግን ትልቁ ችግር ምንድነው ብዙ ምስክር፣
ብዙ የቪዲዮ ማስረጃዎች ያሉበት ድብደባ
በስፖርቱ ሕግ ብቻ ተዳኝቶ ሲያልፍ ነው
የሚታየው፡፡ ይሄ ክፍተት እንዲፈጠር
ምክንያት ነው ብዬ የማምነው ደግሞ የፊፋንና
የካፍን ሕግ እንዳለ መገልበጣችን ያመጣው
ችግር ነው፡፡ ሕጉ ሲወጣና ሲሻሻል ከሀገራችን
ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተገነዘበ ነው ለማለት
ይቸግረኛል፡፡ ለምሣሌ የእኛ የመደበኛ
ሕጋችን እኮ ከፈረንሣይ ነው በቀጥታ
የተገለበጠው፤ በቀጥታ ሲገለበጥ ግን እንደ
ሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ነው እንጂ እንዳለ
እንደወረደ ወደ አማርኛ አልተመለሰም፡፡
ጎጃም ሀገር ያለ ጤፍ በስልቻ ያበደረ ገበሬ
ብድሩን የሚቀበለው ጎጃም ሀገር ባለ ስልቻ
እንጂ ባሌ መጥቶ ባሌ ባለ ስልቻ አይደለም፡፡
የዚህን ያህል ነው ከሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ
ጋር መቃኘት ያለበት፡፡
ሀትሪክ፡- የስንብት ውሳኔው ከተላለፈ
ባችሁ በኋላ የፌዴሬሽኑን ኃላፊዎች አነጋግ
ረችኋል…?
አቶ ጳውሎስ፡- …መሳሳታቸውን
ለማሳየት የተደረገ ጥረት ነበር… ግን
አልተሳካም፤ በተለይ ለፕሬዚዳንቱ የእኔ
ባልደረባ አቶ ዋለልኝ ቴክስት (የመልዕክት
ፅሁፍ) ልኮለት ነበር መልስ ግን የለም፤
በዚህም ሳያበቃ በተደጋጋሚ የፕሬዚዳንቱ
የእጅ ስልክ ላይ ቢደውል ሳያነሱ ቆይተው
በመጨረሻ አንስተው “መልሼ እደውላለሁ”
ብለው እስከአሁና ደቂቃ ድረስ የደወሉት ነገር
የለም፡፡
ሀትሪክ፡-… አሁን ተሰናብታችኋል…
ከዚህ በኋላ ምን አስባችኋል…? ውሳኔውን
አሜን ብላችሁ ተቀብላችሁ ዝም ነው
የምትሉት…?
አቶ ጳውሎስ፡- …በፍፁም ዝም አንልም…
!ለእኛ ሳይሆን ለሌሎች መማሪያ እንዲሆን
ስለምንፈልግ መሄድ እስከሚገባን ድረስ ሄደን
እንታገላለን፤መሳሳታቸውን በሚማሩበት
መልኩ ማድረግ የሚገባንን እናደርጋለን እንጂ
ዝም ብለን አንቀመጥም። ለፊፋ ቅሬታችንን
ፍትሀዊ ሠራ እንዳልተሰራ አሳውቀናል፤
ቅሬታችንን ተከትሎ ኮንታክት ያደረጉንም
አሉ፡ ፡ አሁን መግለፅ አልፈልግም እንጂ
በዚህ ዙሪያ ብዙ ሠራ እየሰራን የሚሆነውን
እየጠበቅን ነው፡፡ በቀጣይ ምን ለመስራት
አስባችኋል ለተባለው ከፌዴሬሽኑ ዞር ተደረግን
ማለት ከስፖርቱ ጋር ተቆራረጥን ወይም
አለቀ አበቃ ማለት አይደለም፤ ለፌዴሬሽኑ
ነፃ አገልግሎት ስንሰጥ እንደነበረው ሁሉ
ለክለቦች ለፍትህ ዘብ በመቆም ስፖርቱን
ከፍትህ አንፃር ይበልጥ እናግዛለን፡፡ የፍትህ
ስርዓት እንዲሰፍን ብዙ ስራ እንሰራለን፡፡
ቮሌንተር ሆነን የምንሰራው ፌዴሬሽን ብቻ
አይደለም፤ ብዙ ነገሮችን መስራት እንችላለ፡
፡ በዚህ በኩል የዮሐንስ ሳህሌ ጉዳይ ትልቅ
ማስተማሪያ ነው፤ወደፍትህ አደባባይ ወስዶና
አሳይተህ መመለስ አንደኛው ማስተማሪያ
ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …ከዚህ በኋላ የፌዴሬሽኑ
ሰዎች ልክ ቡናና የመቐሌን ጨዋታ
ውሳኔ ሶስት አራት ጊዜ እንደገለባበጡት
ውሳኔያቸውን ቀይረው ተመለሱ ወይም ፊፋ
ሕግ ተጥሷል ብሎ አዎንታዊ ምላሽ ቢሰጥ
ትመለሳላችሁ…? …ውሳኔያችሁ ምንድነው
የሚሆነው…?
አቶ ጳውሎስ፡- …ከዚህ በኋላ አሁን
ካለው አመራር ጋር መስራት በፍፁም
የማይታሰብ ነው፤ እሺ ሁሉን ነገር ትተነው
ለእግር ኳሱ ስንል እንመለስ ብንል እንኳን
ስራው ይበላሻል፡፡ ምክንያቱም እነሱም ለእኛ
ጥሩ ስሜት የላቸውም፤ እኛም በተመሳሳይ
ለእነሱ ጥሩ ስሜት ስለሌለን ብንመለስ
እንኳን የተሻለ ነገር ለመስራት ይከብዳል፡
፡ አንተ የእኛን ትላለህ ከዚህ በኋላስ ማነው
የሚሠራላቸው? ምናልባት እዛው የአነሱ
ጉዳይ አስፈፃሚ ወይም አገልጋይ አሸከር
ሆኖ የመስራት ስብዕና ያለው ሰው ካልሆነ
በስተቀር፡፡ የፍትህ አካላት እኮ ፕሮፌሽናሎች
ናቸው፤ያውም በነፃ ገንዘብህን፣ ጉልብትህን፣
አዕምሮህን እየሰጠህ ክብር የማይሰጥበት
ቦታ አዕምሮ ከሌለህ በስተቀር በዚህ ደረጀ
እየተገፋህ ምን ታደርጋለህ፡፡


ሀትሪክ፡- …ከዚህ በፊት እዚህ የፍትህ፣
የሕግ አካላት አካባቢ ባለሙያዎች አልበረክት
ብለዋል ይሄ ከምትለው ጋር ይያያዝ ይሆን?
አቶ ጳውሎስ፡- …ብዙ የታወቁ የሕግ ሰዎች
ከፌዴሬሽኑ ጋር በሙያ ቋንቋ ተግባብተው
ለመስራት ተቸግረው “እኔ ሙያተኛ እንጂ
የአንተ ጉዳይ አስፈፃሚ ወይም አሽከር”
አይደለሁም ብለው ጥለው ሄደዋል፡፡ ከዚህ
በፊት የታወቁቀ የሕግ ባለሙያዎች የሆኑት
አቶ ጌታቸው ቅጣው፣ አቶ ቀፀላ፣ እነ አቶ
ኃይሉን የመሳሰሉ ፌዴሬሽኑን የማገዝ ትልቅ
አቅም ያላቸው የሕግ ባለሙያዎች አብረው
መስራት ባለመቻላቸው እንዲሁ ከቦታው
ዞር ብለዋል፡፡ እዛ ቦታ ላይ ውርስ ይመስል
የበረከተው አንድ ሰውብቻነው፤ እሱም
የበረከተበት ምክንያትን ሁሉም የሚያውቀው
ነው። በነፃ የመታገለግልበት፣ ገንዘብህን፣
አውቀትህን የምታፈስበት ቦታ ላይ ለምነህ
ያውም ሙያህን ሸጠህ የምትኖርበት ምንም
ምክንያት የለም፡፡ እኛ እኮ ብዙ ሥራ ብዙ
ጉዳዮች ያሉብን ሰዎች ነን፡፡
ሀትሪክ፡-ፌዴሬሽኑ ለፍትህ አካላቱ
ምንም የሚከፍለው ነገር የለም ማለት…
ነው..? አንድ ጊዜ የትራንስፖርት ክፍያ
ጠይቃችሁን እንደነበር ስለሰማሁ ነው…?
አቶ ጳውሎስ፡- … አንተ ትቀልዳለህ..?
የምን ክፍያ ነው የምታወራው…? …የፍትህ
አካላት በነፃ የሚሠሩበት ፌዴሬሽን ቢኖር
እዚህ ሀገር ብቻ ነው፡፡ የሌሎች ሀገሮችን
አሠራር ለማየት ግንኙት በመፍጠር ለመረዳት
ጥረት አደርገናል፤ በተለይ አፍሪካ ውስጥ በነፃ
የሚሠራ የፍትህ አካል የለም፡ እኛ ግን ይሄ
በመሆኑ ብዙም አልተከፋንም፤ ምክንያቱም
ከመነሻው አመጣጣችን ፌዴሬሽኑን በሙያችን
ለመጥቀም እንጂ በፌዴሬሽኑ ለመጠቀም
አልነበረምና፡፡
ሀትሪክ፡- …ይቅርታ አድርግልኝና…
ሃሳባችሁ ይሄ ከሆነ ታዲያ ለምን
የትራንስፖርት ጠየቃችሁ…? መጠየቃችሁ
ስህተት ባይሆንም…?
አቶ ጳውሎስ፡- …ምንድነው መሰለህ…
ፌዴሬሽኑ ለልዩ ልዩ ወጪዎች በሣምንት
ወደ 1.5 ሚሊዮን ብር አካባቢ በወጪ ደረጃ
ያወጣል ለከሚሽነር ለዳኛ ምናምን በሚል፤
የፍትህ አካላቱ ግን ቢያንስ ክብራቸው
እንዲጠበቅ የእኔነት ስሜት ይበልጥ
እንዲሰማቸው ቢያንስ የትራንስፖርት ኩፖን
እንኳን ቢሸፈንላቸው ብለን ነው የጠየቅነው፡
፡ ወደዚህ ነገር የገፋን ደግሞ በስብሳቢነት
የይግባኝ ሰሚ ካሚቴ አባላትን ስጠራ ሁሉም
ቀርተው ብቻዬን መጥቼ የምመለስበት ጊዜ
ብዙ ነው፤ እንደውም አንዴ ከፕሬዚዳንቱ ጋር
ስታዲየም ተገናኝተን “ምነው በሠላም ነው?”
ብሎኝ አይ ስብሰባ ስላለን እየጠበኳቸው ነው፤
ብዬው አለመምጣታቸውን አይቷል። የዛን
ቀን ብቻ ሣይሆን ደጋግመው እንደሚቀሩም
ስለሚያውቅ አንድ ጊዜ ታዲያ የእነዚህን
የፍትህ አካላት ክብር ለመጠበቅ የተሻለ
የተነሳሽነት ስሜት ለመፍጠር ቢያንስየትራንስፖርት ኩፖን እንኳን ቢሰጣቸው
ይበልጥ ኃላፊነት እንዲሰማቸው ያደርጋል
ብለነው ይሄው እስከተሰናበትንበት
ተግባራዊ የሆነ ነገር የለም፡፡ አንተ ቀላሉን
የትራንስፖርት ኩፖን ትላለህ፤ የትጥቅ
ችግር ኖሮብን ሣይሆን ፊፋ ለሁለም አባል
ፌዴሬሽኖች ኮሚቴዎች የሚልከውን ትጥቅ
እንኳን ለሌሎች አድለው ትልቁንና ቁልፉን
ስራ ለሚሠራው ለፍትህ አካላት አንድ ቀን
እንኳን ተሳስተው ሰጥተው አያውቁም፡፡
ሀትሪክ፡- …ብዙ ነገር አደመጥኩህ…
አቶ ጳውሎስ እናንተ ራሣችሁ የተገቢነት
ጥያቄ እንደሚነሳባችሁ ታውቃለህ…?
አቶ ጳውሎስ፡- …የምን የተገቢነት
ጥያቄ…?
ሀትሪክ፡- …የፍትህ አካላትን ሥራ
አስፈፃሚ ኮሚቴው ለጠቅላላ ጉባኤው አቅረቦ
ጠ/ጉባኤው አፅድቆ መመረጥ ሲገባችሁ
እናንተ ግን ከጠቅላላ ጉባኤው እውቅና
ውጪ መርጦ ይሄን ኃላፊነት የሰጣችሁ ስራ
አስፈፃሚው ነውና እዚህ ጋ የሕግ ጥሰት
አይታይም…? …ህገ-ወጥ ሆናችሁ ነበር
የሕግ ሥራን ስትሰሩ የነበረው… ?
አቶ ጳውሎስ፡- …(እየሳቀ)… ምንድነው
መሠለህ…. ጥያቄህ አንድ እውነት አለው…፤
በዚያው ልክ ደግሞ የዘነጋኸው ነገርም አለ፡
፡ እንዳልከው የፍትህ አካላት በስራ አስፈፃሚ
ኮሜቴ አካላት ተጠቁመው ለጠቅላላ ጉባኤው
ቀርበው ተገቢነታቸውን የሚያፀድቀው ጠቅላላ
ጉባኤው ነው፤ የሄ የሚያከራክር አይደለም፡
፡ ነገር ግን ደንቡ ላይ ሥራ አስፈፃሚ
ኮሚቴው ከጠቅላላ ጉባኤው ውክልና
ተሰጥቶታል፡፡ በየጊዜው ጠቅላላ ጉባኤ
ስለማይጠራና አንዳንድ ሥራዎች አመት
የማይጠብቁ በመሆናቸው ሥራ አስፈፃሚው
ሙሉውን የፍትህ አካላት ወይም በጎደሉት
ቦታ ምርጫ አድርጎ የመሰየም ሥልጣን
በውክልና ተሰጥቶታል፤የእኛም አመጣጥ
ይሄው ነው፡፡ ያቺን ውክልና ተጠቅመው
በሥራ አስፈፃሚ ደረጃ አስፀድቀው መሰየም
ይችላሉ፤የማይችሉት ነገር ግን ምንድነው
ማሰናበት ብቻ ነው፡፡ ውክልናው ሥራ
ለመስራት ለማስተዳደር በመሆኑ ያዋቅራሉ
እንጂ በተለይ የፍትህ አካላቱን በዚህ መልኩ
የማሰናበት ሥልጣኑ የላቸውም፡፡
ሀትሪክ፡-… ማለት … ጥፋት.. ቢገኝባች
ሁም…?
አቶ ጳውሎስ፡- …ደንቡ የሚለው
ምንድነው “የፍትህ አካላት ጥፋት ካጠፉ ችግር
ቢገኝባቸው የወሰኑት ውሳኔ ፌዴሬሽኑን
ባያስደስተው ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርቡና
ጉባኤው የእርምት እርምጃ ይወስዳል” ነው
የሚለው፡፡ እንደውም እዚህ ጋ ስለማሰናበት
የሰጠው ስልጣን የለም፡፡ ከዚህ አንፃር ነው
ፌዴሬሽኑ ሕግ ጥሷል፣ ጣልቃ ገብቷል
ብለን የምንወቅሰው፡፡ ምክንያቱም አንደኛ እኛ
ያጠፋነው ጥፋት የለም፤ሁለተኛ ለስንብታችን
ምክንያት ተብሎ የቀረበው የውሳኔ ልዩነቶች
ተብሎ ነው፤ የውሳኔ ልዩነት ደግሞ የፍትህ
ባህሪው ነው፡፡ በመደበኛ ፍ/ቤትም በሌሎች
ተቋማትም ብንሄድ የፍትህ ስርዓቱ ውሳኔዎች
መለያየታቸው ከሥራው ባህሪ የሚመጣ ነው፡
፡ እንዳልኩህ ነው ይግባኝ ሰሚው በሰራው ስራ
የሚይደሰት ቅሬታ የገባው አካል ካለ መብቱን
አለም አቀፉ ገላጋይ ፍ/ቤት (ካስ) ድረስ ሄዶ
ማስከበር ብቻ ነው የሚችለው። ውሳኔዎች
ገዢ ናቸው፤ የፍትህ አካል ውሳኔዎች ገዢ
ከመሆናቸው አንፃር መቀበል ነው ያለባቸው፡
፡ ካለመሰላቸው ደግሞ እንዳልኩህ ካስ ድረስ
ሄደው ይግባኝ መጠየቅ ነው። የአሁኑ የእኛ
ስንብት ግን የውሳኔ ልዩነት መጣ ሳይሆን እኔ
እንደምፈልገው ሳልወስናችሁ ዞር በሉ ነው፤
ከዚህ ውጪ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡

ሀትሪክ፡- ከዚህ በፊት ከይግባኝ ሰሚ
ኮሚቴ ስብሳቢነት ራስህን ለማግለል ጠይቀህ
በእነ ኮለኔል አወል ግፊት እንደተመለስክ
አስታውሳለሁ፤ ዛሬ ላይ ሆነህ ስታየው
ተቀደምኩ፣ ምነው ያኔ በለቀኩ ብለህ
ትፀፀታለህ..? በወቅቱስ ለምን የመልቀቅ
ጥያቄ አቀረብክ…?

አቶ ጳውሎስ፡-በፍፁም አልፀፀትም…!
ተቀደምኩ ብዬም አላስብም፤ እንደውም ያኔ
እንኳን አልቀኩ ነው ያልኩት፡፡ ምክንያቱም
በወቅቱ የመልቀቂያ ጥያቄ ሳቀርብ የሚሸቱኝ
ነገሮች ነበሩ፤በነገራችን ላይ እኔን ይሄ ሥራ
አስፈፃሚ አልመረጠኝም በእኔ ላይ ነው
የመጣው፡፡ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሲመጣ
ግን አንዳንድ ያየኋቸው ነገሮች አልተመቹም፤
የተለያዩ ጉምጉምታዎችን ሰማሁኝ፡፡ ገና
ከመምጣታቸው እንደዚህ የሚያደርጉ
ከሆነ በፍትህ አካላቱ ላይ ጣልቃ የመግባት
አዝማሚያ ባማየቴ ከዚህ ሥራ አስፈፃሚ ጋር
ልሰራ አልችልም ብዬ ራሴን የማግለል ውሳኔ
አቀረብኩ፡፡ በእረፍት በሻይ ሰዓት በስፖርት
ውስጥ ትልቅ ሥራ የሠሩና የማከብራቸው
እንደ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ኮለኔል
አወል ያሉ ሰዎች “በፍፁም ጣልቃ ገብነት
አይኖርም፤አብረን እንሰራ” አሉኝ በእርግጥም
ሰዎቹ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ፣ ልምድ
ያላቸው፣ ሥራቸውን በተግባር ያሳዩ በመሆኑ
የአብረን እንሰራ ጥያቄያቸውን ለመርገጥ
አቅሙ ስላነሳኝ ሃሳቤን ቀይሬ ተመለስኩ፡
፡ ዛሬ ላይ ሆኜ ውሳኔዬን በመቀየሬ ምንም
የሚፀፅተኝ ነገር የለም፤ እንደውም ቀደም ብዬ
ልቀቅ ያልኩት ዝም ብዬ እንዳልሆነ የፈረሁት
ነገር እንደደረሰ ሁሉም ተገንዝቧል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...