ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ
በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ጋዜጣ ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ ስትውል የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ይዛላችሁ ትቀርባለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ዘገባዋ ነገ ምንን ይዛ በመውጣት ታስነብቦት ይሆን?
-በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከሆኑት አቶ ጳውሎስ ተሰማ ጋር በወቅታዊው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔዎች እና ከሃላፊነታቸው በመነሳታቸው ዙሪያ ረዘም ያለ የቃለ-ምልልስ ቆይታን አድርጎላቸው ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በነገው ሀትሪክ ላይ ምን ብለው ይሆን ?
“የእኛ ስንብት የዲስፕሊን ኮሚቴውና ፌዴሬሽኑ
በአንድ ሳምባ እንደሚተነፍሱ ያረጋገጠ ነው” ሲሉ ለሌሎችም ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽን ሰጥተዋል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ ሌላ ዘገባዋ ነገ የምታስነብቦት በፀጥታ ስጋት ምክንያት በተደጋጋሚ ጊዜ ሳይካሄድ ስለቀረው እና ነገ ሊጫወቱ ቀጠሮ ስለተያዘለት ኢትዮጵያ ቡናና መቐለ 70 እንደርታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ስለሚያደርጉትም ጨዋታ ነው፤ በግጥሚያው ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡናው አማኑኤል ዮሃንስ እና የመቐለ 70 እንደርታው አሚን ነስሩ ምን ብለው ይሆን ከጋዜጣው አጠቃላይ ዘገባውን ታነቡታላችሁ፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዋስ ነገ ምን ታስነብቦታለች፡፡
ከእነዚህ መካከል ስላልተረጋጋው አርሰናል፤ ስለ ሄዲን ሀዛርድ “እኔ ጋላክቲኮ አይደለውም ስለማለቱና በነጩ ቤት ታሪክ መስራት እፈልጋለው ስለማለቱ እንዲሁም ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ፈራሚ ዳንኤል ጀምስ የሚያነቡትና የሚወዱት ዘገባ ይቀርብሎታል፡፡ የነገዋ ሀትሪክ አታምልጦት ከዛ ውጪም ሌሎች ያልተሰሙ ዘገባዎችን ሀትሪክ ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
የሀትሪክን ትኩስ የሆኑ መረጃዎቿን ከጋዜጣዋ በተጨማሪ በርካታ ተከታታዮች ባሏት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ላይም ያገኛሉ። ይጎብኙን፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡