ራያ ቀድሞ ባስቆጠረው ጎል 1 ለ ምንም እየመራ፤ 90ኛው ደቂቃ ላይ ደባርቅ የአቻነቱን ጎል እንዳገባ፤ ወዲያውኑ የራያ አዘቦ ደጋፊ ወደ ሜዳ በመግባት በተጨዋቾቹ ላይ ጉዳት አደርሰዋል
ከተጎዱት የደባርቅ ተጨዋቾች መካከል፤ ቻላቸው አሰፋ፣ ፋሲል ፋንታሁን፣ሸጋው አስማረ፣ አቤል ፋንታሁን፣ ዮሃንስ ኪሮስ፣ ፍስሃ ረዲ እና አሰልጣኝ ስጦታው ይገኙበታል።
የተጎዱትን ወደ ሆስፒታል ከአመሩ በኋላ ፥የጨዋታው ኮሚሽነር የባከነውን 5 ደቂቃ እንዲጨርሱ ሁለቱንም ቡድን ያዘዙ ሲሆን የደባርቅ ተጨዋቾቹ አቋርጠው ወጥተዋል።
- ማሰታውቂያ -
ደባርቅ በብሄራዊ ሊጉ 8ኛ ደረጃ ላይ ሲሆን ፥ ራያ አዘቦ 6ኛ ነው። ሁለቱም ቡድኖች ወደ ልዕለ ደራጃው የማደግ እድል የላቸውም።
source-TBM