የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ማህበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ እርዳታ ዛሬ አስረከቡ

የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ማህበር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይውል ዘንድ ከፕሪምየር ሊግ እና ከከፍተኛ ሊግ ቡድን ተጨዋቾች ያሰባሰቡትን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ እርዳታ በዛሬው ዕለት ለድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አስረክበዋል ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የመስተዳደሩ እና የስፖርት ኮሚሽን ከፍተኛ ሀላፊዎች እንደዚሁም ደግሞ የየክለቡ ካፒቴኖች እና የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች አመራሮች በአዲስ አበባ ስታድየም በተገኙበት በእዚህ የገንዘብ ርክክብ ፕሮግራም ላይ ማህበሩ ይሄን ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል መርህ ኮረና ቫይረስን መነሻ አድርጎ ለሰራው ስራ ከመስተዳደሩ ከስፖርት ኮሚሽንና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል።

የተሰባሰበውን ብርና ቁሳቁስ የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ኤሊያስ ሽኩር፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት ክቡር አቶ ኢሳያስ ጅራ እና የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፋትቦለርስ አሶሴሽን ም/ፕሬዝዳንት አቶ መስፍን ብሩ በጋራ በመሆን ለአምባሳደር ምስጋናው አረጋ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አስረክበዋል ።
’’ድጋፉ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ክቡር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እና አቶ ኢሳያስ ጅራ ጥሪያቸውን ሲያቀርቡ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ በበኩላቸው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ክለቦቹ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ያሰበሰቡት የገንዘብ መጠን ከታች የተቀመጠውን ምስል ይመልከቱ 👇

Editor at Hatricksport website

Facebook

መሸሻ ወልዴ

Editor at Hatricksport website