መነሻ ገጽ ሉሲዎቹ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ውድድር የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ
ሉሲዎቹሴካፋ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ውድድር የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ

አጋራ
አጋራ

በሩዋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ሶስተኛው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ውድድር የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አዘጋጇን ሩዋንዳን 3ለ0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን አጣጥሟል።

ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓ.ም የተጀመረው ውድድር ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል።

ትናንት በስታድ ደ ኪጋሊ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመሰሉ አበራ፣ ምርቃት ፈለቀና ሴናፍ ዋቁማ ጎሎች የሩዋንዳ አቻውን ማሸነፍ ችሏል።

ሉሲዎቹ ጨዋታውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ወደ ዋንጫው ፉክክር የተመለሱ ሲሆን ሶስት ነጥብና ሁለት የግብ ክፍያ በመያዝ ከነበሩበት አምስተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ ማለት ችለዋል።

ሉሲዎቹ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ከኡጋንዳ አቻቸው ጋር ባደረጉት ጨዋታ ሁለት ለአንድ መሸነፋቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ጨዋታውን ነገ በስታድ ደ ኪጋሊ ነገ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ያደርጋል።

ትናንት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ታንዛኒያ ኡጋንዳን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። በዚሁ መሰረት ታንዛንያ ነጥቧን ወደ አራት ከፍ በማድረግ ወደ ሁለተኛ ደረጃ መምጣት ችላለች።

ኡጋንዳ በስድስት ነጥብ የመሪነቱን ደረጃ የያዘች ሲሆን ቀጣይ ጨዋታዋን ነገ ከቀኑ 11 ሰአት ከ15 ደቂቃ ከአዘጋጇ ሩዋንዳ ጋር ታደርጋለች።

በአጠቃላይ አምስቱ አገሮች እርስ በእርስ በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የተሻለ ነጥብ ያስመዘገበ ቡድን የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል።

ውድድሩ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ይቆያል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሴካፋአትዮጵያውያን በውጪዜናዎች

በአሰልጣኝ ፍሬ የሚመሩት ካምፓላ ኩዊንስዎች በትላንትናው እለት ሰባት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል!!

በምስራቅ አፍሪካ ዞን የ ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ጨዋታ በአሰልጣኝ ፍሬ የሚመሩት...

ሴካፋኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

የሴካፋ ካጋሜ ካፕ ምድብ ድልድል ወጥቷል

ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ጨዋታውን ከታንዛንያው ሲጊንዳ ብላክ ጋር በአዛም ኮምሌክስ ስታድየም ማክሰኞ...

ሉሲዎቹኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ በታንዛኒያ የመጀመሪያ ዋንጫዋን አሳካች

የሉሲዎቹ ወሳኝ ተጫዋች የሆነችው አረጋሽ ካልሳ ከክለቧ ያንጋ ፕሪንሰስ ጋር የመጀመሪያ ዋንጫዋን...

ሉሲዎቹዜናዎች

“አሸንፈን እንደምናልፍ በጣም እርግጠኞች ነን” ሎዛ አበራ “ተጋጣሚያችን ከኛ የተሻለ ምንም ነገር የለውም” አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የ2026 የአፍሪካ ዋንጫ አንደኛ ዙር የማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን...