የአሰልጣኞች አስተያየት| ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ባህርዳር ከተማ
አዲስ አበባ ስታዲዮዮም ላይ የተደረገው የ10ኛው ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለተም ቡድን አሰልጣኞች ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ከጨዋታው ነጥብ እንፈልግ ስለነበር ጫናዎች ነበሩ ሰርዳን ዥቪጅኖቭ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ስለጨዋታው
ጨዋታው ጥሩ ነው ሆኖም ግን የሊጉን መሪ መቐለ 70 እንደርታ ለመከተል ከጨዋታው ነጥብ እንፈልግ ስለነበር ጫናዎች ነበሩበ መደመሪያዎቹ አጋማሽ ኳስን ተቆጣጥረን መጫወት ብዙ እድሎች መፍጠር ብንችልም ግብ ማስቆጠር ግን አልቻልንም። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ያገኘነውን አጋጣሚ በሚገባ ተጠቅመን ግብ አስቆጥረናል። ግብ ካስቆጠርንም በኋላ ቡዙ እድሎችን መፍጠር ችለናል።
የዛምብያ ብሄራዊ ቡድንን ለመያዝ ሲቪ ማስገባትህ ከክለቡ ጋር ለመቀጠል ጫና አይፈጥርብህም
ሲቪየን ያስገባሁት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመያዜ በፊት ስለሆነ ምንም ችግር አይፈጥርብኝም።
በክለቡ ደጋፊዎች ያሉ ተቃውሞዎች
ማንም አሰልጣኙም ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲመጣ ጫናዎች እንዳሉበት ያውቃል። ምክንያቱም ደጋፊዎች ሁልጊዜ ሻምፐሸዮን መሆን ነው ሚፈልጉት። ቢሆንም ግን የክለቡ ደጋፊዎች ሁልጊዜ ማሻነፍ ከባድ እንየሆነ ይረዳሉ። አሁን ከመሪው ያለን የነጥብ ልዩነት 2 ነው። ይህም ክለቡ ያለው ጥሩ ነው። ብየ ስለማስብ ተቃውሞዎች አያስጨንቁኝም።
የምንችለዉን ኣድርገናል ያገኘናቸዉ የጎል እድል ኣለመጠቀማችን የኋላ ኋላ ዋጋ ኣስከፍሎናል (ፋሲል ተካልኝ ባህርዳር ከተማ)
ስለጨዋታው
በመጀመሪያ ተጋጣሚያችን 3 ነጥብ ስላገኘ እንኳን ደስ አላቹህ ማለት እፈልጋለሁ ከዛ ውጪ ወደ ጨዋታ ስንመለስ ቡድኔ ከዚህ ሜዳ ነጥብ ይዞ ለመውጣት ተጫዋቾቹ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል ። እነሱ የሚያጠቁበትን ቦታ ዘግተን እኛ የጎል እድሎች ፈጥረን ለማሸነፍ የምንችለዉን ኣድርገናል ያገኘናቸዉ የጎል እድል ኣለመጠቀማችን የኋላ ኋላ ዋጋ ኣስከፍሎናል። እግር ኳስ ነው ግን ጨዋታዉ ዉጤቱን ይገልፀዋል ብየ አላስብም ።
የሳሙኤል ተደጋጋሚ ስህተት
ሳሙኤል ጥሩ እየተጫወተ ነው። ወጣት ተጫዋች ነው ስህተቶችን ሊሰራ ይችላል። ስህተቶችን ግን እያረምን እንሄዳለን። በሱ ቦታ ሲጫወት ከነበረው ተጫዋች አንሷል ብየ አላስብም ጥሩ እየተጫወተ ነበር መጨረሻ ላይ እንደተጫዋች የራሱን ውሳኔ ወስኗል። ይህ ደግሞ ያጋጥማል ግን ተቀይሮ መውጣት ነበረበት የሚል ስሜት የለኝም።
አስተያየት ይስጡ