የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ

2014
ከሀትሪክ ጋር:-

የአዳዲስ መረጃዎች የመፍለቂያ አመት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን
ምርጥ ስራችንን ለሌሎች ነግረው ድክመታችንን ለኛ አሳውቀው አብራችሁን እንደነበራችሁ 2014 ከ2013 በተሻለ የጠበቀ አብሮነት የምናሳይበት አመት እንደሚሆን ርግጠኞች ነን…

ቅዳሜ አዲሱ አመት እንቁጣጣሽ በመሆኑ ሀትሪክ በዚህ ሳምንት ብቻ ነገ አርብ ጳጉሜ 5/2013 ጠዋት እጅዎ ትገባለች.. እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን ገና ከጠዋቱ በታዳጊነቱ ትልቅ አደራ ትከሻው ላይ የተጫነበት የብረት ምሰሶ ጠባቂ የማኑኤል ኑኤር በእግር መጫወት እያየ የተሳበ የጂያንሉጂ ቡፎን አድናቂ ለአዲሱ አመት ምርጥ ስጦታ የሰጡን የዋሊያዎቹ ምሰሶ ጠባቂ ፋሲል ገ/ሚካኤል የአመቱ የመጨረሻ እትማችን እንግዳችን ነው። እንደሜዳው ጀግና ልቡ ሳይፈራ ሳይሳሳ ድፍረት የተሞላበት ምላሽ ሰጥቷል ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረገው ፋሲል…”ዕድሉ ቢሰጠን ኢትዮጵያዊ ግብ ጠባቂዎች ጠንካሮች ነን”ሲልም ለኢትዮጵያዊያን ግብ ጠባቂዎች ልባቸው የጨከነውን አሰልጣኞች እስቲ ለሀገሬ ልጆች ልባችሁ ይከፈት ያለ የሚመስል ጥሪ አድርጓል።

*….የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀግኖች ሴቶች በሴካፋ ፍልሚያ በኬንያው ክለብ ተረትተው ዋንጫ ቢያጡም አስገራሚው ግስጋሴያቸው የሚረሳ አይደለም ይሄ ታሪክ በስኬት የሚጠቀስ በመሆኑ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛውና ስብስቡ የሞቀ አቀባበል ይጠብቃቸዋል ተብሎ ይገመታል…የሀትሪኩ ይስሃቅ በላይ በሴካፋ አዲስ ታሪክ የጻፈውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጉዞ እንዲህ ዳሶታል…

*… ዋሊያዎቹ ዚምባብዌን ባለቀ ሰአት በተቆጠረ የፍጹም ቅጣት ምት ባህርዳር ላይ አሸንፈው የአዲስ አመት ስጦታ አበርክተውልናል…መሸሻ ወልዴ ከቡድኑ ተጨዋች ይሁን እንዳሻው ጋር አውግተዋል….

*….ፋሲል ከነማ በፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮናነቱ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክል ሲሆን ከነገ በስቲያ እሁድ መስከረም 2/2014 ባህርዳር ላይ ከሱዳኑ አል ሂላል ጋር ይጫወታል…መሸሻ ወልዴ ከፋሲሉ አዲስ ፈራሚ አስቻለሁ ታመነ ጋር ቆይታ አድርጓል።

*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*…. ” የማን.ዩናይትዱ የመሃል ሜዳ ጀግና ፖል ፖግባ ሁለቱን የዘመኑ ኮከቦች አድንቆ አያበቃም…” ሮናልዶና ሜሲ ለእግርኳሱ ዓለም የተሰጡ ምርጥ ስጦታዎች ናቸው” ሲልም አስተያየቱን ሰጥቷል…

*… ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከ12 አመት በኋላ ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ ማን.ዩናይትድ ተመልሷል… በተጨዋችነት ዘመኑ በርካታ ስኬቶችን ያሳካው ሮናልዶ ገድሉ የሚረሳም አልሆነም.. ለዛሬ የሮናልዶ 12 ስኬቶችን እንዲህ አዘጋጅተናቸዋል..

*…..አርሰናል ከሶስቱ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎቹ በሶስቱም ተሸንፎ ምንም ግብ አለማስቆጠሩ አርሰናላዊያንን ቢያበሳጭም የክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር ኤዱ” የወደፊቱን አርሰናል እየገነባን ነው..በአርቴታና በቡድኑ እምነት አለኝ” ሲል ተናግሯል……

*…… የሊቨርፑሉ ፋቢንሆ ስለእቅዱ የተሰማውን ተንፍሷል..”በፕሪሚየር ሊጉና ሻምፒየንስ ሊጉን በድጋሚ ለመጫወት ናፍቄያለሁ” ሲል ተናግሯል ..

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *