መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ​የቅዱሰ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዓመታዊ  ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ 
ቅዱስ ጊዮርጊስጠቅላላ ጉባዔ

​የቅዱሰ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዓመታዊ  ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ 

አጋራ
አጋራ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በዛሬው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ የክለቡ ደጋፊዎች በተገኙበት አከናውኗል ፡፡
የሰፖርት ክለቡ ቦርድ እነዚህን በዝርዝር መልክ አቅርቧል 

-ምልዕተ ጉባኤ መሟላት ማረጋገጥ
-የ2009 ዓ.ም አጠቃላይ ሪፖርት ማቅረብ

-የ2008 እና 2009 ዓ.ም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርት ማቅረብ 

-በሪፖርቶቹ ላይ ውይይትና ሪፖርቶችን ማጽደቅ

-የ2010 ዓ.ም ዕቅድ ማቅረብ

እሚሉትን በዝርዝር ቀርበው በሙሉ ድምፅ ቤቱ አጽድቆታል ፡፡

ጉባኤው ረግጦ በመውጣት እግድ ተደርጎባቸው የነበሩ አምስት አባላት መኖራቸው ተገልፆ 

1.አንተነህ ፈለቀ

2 ዮሴፍ አለማየሁ

3 ተስፋዬ ነጋሽ

4 ዳንኤል ካሳ 

5.ታደሰ መሸሻ 

ሲሆኑ ከነዚህም  መካከል በደንቡ መሰረት ይቅርታ የጠየቁ እና ስራቸው ከግምት በማስገባት ቦርዱ ከአራቱ መካከል አቶ ዮሴፍ አለማየሁ በማስጠንቀቂያ እግዱ አነስቷል ፡፡በተቀሩት አራቱ አባላት ከአባልነት ይሰረዙ በሚል ቤቱ ድምፅ ሰጥቷል፡፡
በዚህም መሠረት:-

ተቃውሞ -18 
ድምፀ ተዓቅቦ – 57 

ድጋፍ – 1320 

በሆነ ድምፅ 4ቱ ስማቸው የተጠቀሱት ሰዎች  ከማህበሩ አባልነት ተሰዘርዋል። 
1.አንተነህ ፈለቀ
2.ዳንኤል ካሳ 

3.ታደሰ መሸሻ 

4.ተስፋዬ ነጋሽ 

——————————————————————

ልዩ ልዩ በሚለው አርስት አቶ አብነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ወደ አክሲዮን አደረጃጀት ለማስተላለፍ የሀሳብ እቅዳቸውን አቀርበዋል፡፡

“✍ በኢትዮጵያ  ህግ ማኀበራት ሀብት ማፍራት ስለማይችሉ ወደ አክሲዮንነት መቀየር አስፈለጊ ሇኗል። 

✍አክሲዮኑ  ሲመሠረት እነዚህ  አደረጃጀቶች ይኖሩታል
 -ጠቅላላ ጉባኤ 

– ቦርድ

-ስራ አስኪያጅ

-ኦዲት

ፋይናንስ እና ሌሎች አካላት  ይኖሩታል። 

ይህን አሰራር በቀጥታ እኛ የሰራነው ሳይሆን ባለሞያዎቹ ያመጡት የመነሻ ሀሳብ ነው፡፡

አንድ ግለሰብ የአክሲዮኑ አባል ለመሆን በትንሹ 1 ሚሊየን ብር ያስፈልገዋል ፡፡ ወይም በማኀበር በመደራጀት መግዛት  ይቻላል ፡፡ በዚህ መሠረት እስታዲየሞችን እና ሪል ስቴቶችን መግዛት እንችላለን በተለያዩ ሀገራት ይሄን ሀሳብ ወደተግባር አስገብተው እሚገኙ ክለቦች አሉ፡፡ በግሌ ከሼሩ ትርፍ አልፈልግም ግን ክለቡ እንዲቀጥል እፈልጋለሁ እኛ ባንኖርም የክለቡ ህልውና ይቀጥላል ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል”

——————————————————————

በክብር እንግድነት የተጋበዙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኘሬዚዳንት አቶ ጂነዲን በንግግራቸው 
“ቅዱስ ጊዮርጊስ እስፖርት ክለብ ዘመናዊ የክለብ አወቃቀር እና ግዜው እሚፈልገውን ሲስተም ተከትሎ ለሚሰራው ስራ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር በተያያዘ ደጋፊዎችም ኢንሹራንስ የሚያገኙበትን አሰራር አስበናል።
እናንተ ደጋፊዎች የሆነ ያልሆነውን ታፔላ ለእኛ መለጠፉን ማቆም አለባችሁ። እኛ የሁላችሁም ነን ቡናም ሲጠራ እንመጣለን እናንተም ስጠሩን እንደዛው እየመጣን ነው፡፡
ሰሞኑንም የዲሲፒሊን ማሻሻያ አድርገናል ከክለብ አመራሮች ጋር ተሰብስበን ውሳኔ እናሳልፋለን፡፡
 ✍ እናንተ ዋንጫ ወስዳቹ ዳኛ ካማረራቹ እንዴት ይሆናል ?
በታገዱ አባላት ዙሪያ ዝርዝር ውስጥ አልገባም ግን ሰላም ስትሆኑ ደስ ይለናል። ግን ሙግቱ እንዲጠፋ እና ልማቱ እንዲሰፋ እንፈልጋለን። 
ይሄኛው ሀሳቤ ባይገናኝም መልእክቴን ለማስተላለፍ ነው መድረኩ የጊዮርጊስ ቢሆንም ደጋፊውም ይሄን ይደግፋል ብዬ አስባለሁ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መፍረስ ጋር ተያይዞ ቦርዳቸው እንደሚያየው ተስፋ አደርጋለሁ። ከሊግ መውረድ መፍረስ መሆን ሞት ተደርጎ መቆጠር የለበትም ፡፡ ፌዴሬሽኑ ሙገር ሲሚንቶን ጋርም ዳሽን ቢራ ጋርም በአካል አና በደብዳቤ አናግረናል። ማፍረስ ጥሩ አይደለም ባንክ ይመለሳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” በማለት ሀሳባቸውን ቋጭተዋል::

በዚሁ የክለቡ የቦርድ ኘሬዚዳንት አቶ አብነት ኘሮግራሙን በክለቡ መዝሙር ዘግተዋል ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቢጂአይ ኢትዮጵያ ስፖንሰር ሊደረግ ነው

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀድሞው አጋሩ ጋር በድጋሚ ለመጣመር ውይይት አድርጓል። አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስን...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞው ተጫዋቾች ማህበር አቋቋሙ

የቅዱስ ጊዮርጊስን ችግር ለመቅረፍ ያለመ በቀድሞው ተጫዋቾች የተሰየመ ማህበር በዛሬው ዕለት በይፋ...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የሽግግር ኮሚቴ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ መረጠ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ካጋጠመው ውስጣዊ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተቋቋመው የሽግግር ኮሚቴ...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የፈረሰኞቹ የሰላም ውይይት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል…..

... ከሳሹ ወገን ዛሬ ቦርዱ ሃላፊነቱን መልቀቁን በይፋ ማሳወቅ አለበት እያለ ነው...