ዋልያዎቹ ሁለተኛ ልምምዳቸውን አካሂደዋል !

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ከኒጀር ብሔራዊ ቡድን ጋር ላለባቸው ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ የደርሶ መልስ መርሐ ግብር ልምምዳቸውን ከትላንት አንስተው ማካሄድ ጀምረዋል ፡፡

በዛሬው ዕለትም ከጥቂት ሰዓታት በፊት ልምምዳቸውን ሲያጠናቅቁ በዛሬው ልምምድ አንድ ሰዓት ከ አስር ደቂቃዎችን የፈጀ ልምምድ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል ፡፡

በዛሬው ልምምድ የማሟሟቂያ ልምምዶችን ማድረጋቸው ሲታወቅ በተለይም መሀል ገብ የሚባለውን በትንሽ ቡደን ተከፋፍለው የሚሰራውን የልምምድ አይነት መስራታቸው ታውቋል ፡፡

ዋልያዎቹ በዛሬው እለት ከሰዓት ካልሆነም በነገው ዕለት ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor