መነሻ ገጽ Oldies but Goodies  “ወርቃማ የነበረው ኤሌክትሪክ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ላለመውረድ መጫወቱ ሁሌም ያንገበግበኛል” ኃይሉ አድማሱ /ቻይና/
Oldies but Goodies ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

“ወርቃማ የነበረው ኤሌክትሪክ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ላለመውረድ መጫወቱ ሁሌም ያንገበግበኛል” ኃይሉ አድማሱ /ቻይና/

አጋራ
አጋራ

​በመሸሻ ወልዴ

የኤሌክትሪክ ክለብ ውስጥ 19 ከስር አድጎ 
በመጫወት የላቀ ብቃቱን ያሳየው ኃይሉ አድማሱ 
(ቻይና) በአሁን ሰአት ላይ የአሰልጣኝነት ሙያ ላይ 
የተሰማራ ሲሆን ተጨዋቹን ከረጅም አመታት በኋላ 
ባሳለፈው የእግር ኳስ ህይወት ላይ በመንተራስ 
ላቀረብንለት ጥያቄ ምላሹን ሰጥቶናል ተከታተሉት፡፡ 
–በእግር ኳስ በጣም የተደሰትክበት ቀን፦ጊዜው 
1993 ዓ.ም ነበር ያኔም የአገሪቱ ትልቅ ክለብ 
ከሆነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ጋር ያደረግነው 
ጨዋታ በጣም የሚያምርና በእኛ የበላይነት 
ተፋላሚያችን 4-1 በሆነ ውጤት ዶሚኔት አድርገን 
ያሸነፍንበት ጨዋታ መቼም ቢሆን አይረሳኝም፤ 
ይህንን ግጥሚያ ሁሌም በመልካምነት የማነሳው 
ነው፤ በወቅቱም ጨዋታውንም በሰፊ ግብ ስናሸንፍ 
ሶስቱን ኳሶች ያቀበልኩትም (አሲስት) ያደረኩትም 
እኔ ነበርኩ፡፡
–በእግር ኳስ በጣም ያዘነበት፤ልቡ የተሰበረበት 
ቀን፦
በ1993 ዓ.ም የነበረው ኤሌክትሪክ የአገሪቱን 
እግር ኳስ በበላይነት የተቆጣጠረበት ጊዜ ስለነበር 
የእኛን ቡድን ማሸነፍ ለሁሉም ክለቦች በጣም ከባድ 
አስቀድሞም ሻምፒዮና ሆነን ግን የሁለተኛው ዙር 
ጨዋታችንን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረግንበት 
የክረምት ወራት በመራበት ግጥሚያ ወደ ናዝሬት 
ሄዶ እዚያ ነበር ያንን ጨዋታም በአለም ወጣቶች 
;;;; ሄደን በከተመለስን በኋላ ያከናወንነው ነበር 
በጨዋታውም 2-1 ተሸነፍን ያንን ጨዋታን 
መሸነፋችንንም ፍፁም ያላመኑት የኢትዮጵያ 
ቡና ደጋፊዎች እኛ ከአቅም በታች ተጫውተን 
እንደተሸነፍን በመቁጠር የተረዱበት ስሜት ነበርና 
እኛ ላይ ደስ የማይል ስሜት ነው ሊፈጠርብን 
የቻለውና ያን እለት በጣሙን አዝኛለሁ፡፡
–እግር ኳስ ተጫዋች ባይሆን ኖሮ በምን ሙያ 
እናገኘው ነበር፦
ስወለድ አንስቶ ኳስ ተጫዋች ነው 
የምትሆነው የሚል ትዕዛዝ ከላይ ስለተሰጠኝ ከእዚያ 
ውጪ ራሴን በሌላ ነገር ፈልጌውም አላውቅም፤ 
ለእዚህም ነው በአሁን ሰዓትም ኳስ አቁሜም ከኳሱ 
ሳልርቅ ወደ አሰልጣኝነት ህይወት ጎራ ያልኩት፡፡
–በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ባላየውና 
ባልሰማው ብሎ የሚመኘው፦
የኤሌክትሪክ ክለብ 
እኔን ያሳደገኝና ለትልቅ ደረጃም ያበቃኝ ከመሆኑ 
አኳያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ክለቡ ላለመውረድ 
የሚጫወትበት መንገድ በጣም ያሳዝነኛል፤ በዚህ 
ደረጃ መጫወቱን ሳይና ስሰማ ያመኛልና፤ ሌላው 
ደግሞ የአዲስ አበባ ክለቦች ለኢትዮጵያ እግር ኳስ 
ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚፈርሱበት ሁኔታ 
ያሳቅቀኛልና ያንን ባላይ ነው የምመርጠው፡፡ 
–ኃይሉ አድማሱ ራሱን በ3 ቃላቶች 
ሲገልፅ፦
ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ያወሩልህ እንጂ 
ስለራስህ ብዙ ማውራት የለብህም የሚል አባባል 
ቢኖርም እኔ ግን ስለራሴ ስናገር ለሰዎች መልካም 
እንደሆንኩ፣ታማኝና ሰዎችን አክባሪነቴ መሆኔ 
እኔነቴን በደንብ ይገልፁታል፡፡ 
–በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኑ ዛሬም ድረስ 
የሚቆጭበት፦
የኤሌክትሪክን የዋና ቡድን ከታዳጊው 
ሲ ቡድን እኔን ጨምሮ የተወሰኑ ጥሩ ችሎታ 
ያላቸው ተጨዋቾች ካደግን በኋላ በችሎታችንም 
ስኳድን ስንቆጣጠረውና አድናቆትንም ስናተርፍ 
የመጫወቻ እድሜያችን ላይ አርጅተዋል የሚል 
ዘመቻ ተከፍቶ ኳስን ያለ ዕድሜዬ እንዳቆም መደረጌ 
ይቆጨኛል፡፡
-በምድር ላይ ካጧሃቸው መኖር አልችልም 
ስለሚላቸው፦
ቤተሰቦቼን፣ ባለቤትንና ልጆቼን ምንም 
ነገር እንዲነካብኝ አልፈልግም፤ የእኔን ብቻ ሳይሆን 
የሌላውንም። እነሱን አጥቶ መኖርም በጣም ከባድ 
ነውና ፈጣሪ ሁሌም እንዲጠብቃቸው ፀሎቴን 
አደርሳለሁ፡፡ 
–ኤሌክትሪክ ውስጥ ቻይና የሚል ቅፅል ስም 
ያለው ሞክሼ ስለመኖሩ፦
ቻይና የሚል ቅፅል 
ስም ያለው ተጫዋች እኛ ካደግን ዓመታት በኋላ 
ዋናውን ቡድን ከስር በማደግ ተቀላቅሎ ነበር፤ ዋና 
ስሙም መስፍን አሰፋ ይባላል፤ እኔ ቀዩ ቻይና እሱ 
ደግም ጥቁሩ ቻይና ተብለን እንጠራ ነበርና ያኔ 
ሁለታችንም በከለርም በችሎታም የሚያገናኘን ነገር 
ባለመኖሩ ያንን የማስታወሰው ነው፡፡
–የጨዋታ ዘመኑ ምርጥ ግብ፦ የ1994ቷን 
ያችቺን ግቤን ፈፅሞ አልረሳትም፤ በበርካታ 
ደጋፊዎቹ ታጅቦ ከሚጫወተው ኢትዮጰያ ቡና 
ጋር ያደረግነው ጨዋታም ነበር፤ 2-0 ከተመራን 
በኋላም ጨዋታውን 4-2 ያሸነፍንበት ነው፤ 
ኳስን ያስቆጠርኩበት መንገድ ከአለማየሁ ዲሳሳ 
(ዴልፒዬሮ) ጋር የአንድ ሁለት ያማረ ቅብብል 
በማድረግ ወደ እነሱ የግብ ክልል ሄደን ከዚያም 
ከፔናልቲ ቦክስ ውጪ ግብ ጠባቂው ሳዳት ላይ 
በመምታት ነው ኳሷን ያገባኋትን ግቧን ዛሬም 
ድረስ በምርጥነቷ የምገልፃት ነው፡፡
–የጨዋታ ዘመኑ ምርጥ ጨዋታ፦የእግር ኳስ 
ተጫዋችነት ዘመኔ ላይ ብዙ ምርጥ ጨዋታዎችን 
የማስታወስ ቢሆንም አንድ በአንድ ማስበለጥ 
ስላለብኝ የአልጀሪያውን ክለብ የኤሌክትሪክ ተጨዋች 
ሆኜ የተፋለምንበት ግጥሚያ ለእኔ ምርጡ የሚባል 
ነው፤ ያንን ጨዋታ እኛ ብዙ የግብ ዕድሎችን 
ፈጥረን 1-0 ብናሸንፍም ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ 
ባንችልም ጨዋታውን ግን በምርጥ ጨዋታነት 
የማነሳው ፡፡ 
–የጨዋታ ዘመኑ ምርጥ አሰልጣኝ፦ምን 
ያስጠይቃል? ነፍሳቸውን ይማረውና ማስተር 
ቴክኒሽያን ሐጉስ ደስታ ናቸው፤ ጋሽ ሐጎስ 
ከጥሩ አሰልጣኝነታቸዉ በተጨማሪ የሚገርም 
ስብዕና ያላቸው ባለሙያ ነበሩ፡፡ በእዚያን ዘመን 
በሙያው ቀድመው ያወቁ የነቁ ቢሆንም ብዙም 
ሳንጠቀምበቸው በሞት ያጣናቸው ናቸው፤ 
እሳቸውን ያኔ እንደ አሰልጣኝ ብቻ ሳይሆን እንደ 
አባትና ወንድም በመሆን ብዙ ነገርን ያወሩን ስለነበር 
እሳቸውን ያጣንበት መንገድ ትንሽ ይከብዳል፡፡
-በጨዋታ ዘመኑ በጣም ያስቸገረው 
ተጨዋች፦
ብዙም ያስቸገረኝ ተጨዋች አላጋጠመኝም፡
፡ 
–አብሮት ተጣምሮ ሲጫወት በጣም የሚመቸው፦ 
ተክሌ ብርሃኔ ፤ እሱ ተአምረኛ የሆኑ እግሮች አሉት፤ 
ያኔ እሱ ከመድን መጥቶ ቡድናችንን በተቀላቀለበት 
ጊዜ ደግሞ እኔ ከኤሌክትሪክ ታዳጊ ቡድን አድጌ 
የዋናው ቡድን ተጫዋች የሆንኩበት ጊዜ ስለነበር 
መጫወቱ ላይ በመጓጓትና አቅምም ስለነበረኝ አንድ 
ነገርንም ለማሳየት በማሰብ በጣምም እሮጥ ነበር፡፡ 
ያኔ ታዲያ ከእሱ አጠገብ ሆኜ ስጫወት ሁኔታዬን 
አይቶ ኳስ እንዴት አድርጌ ተቆጣጥሬ መያዝና 
መጫወት እንዳለብኝ ብዙ መስመርንም ያሲያዘኝ 
ተጨዋች ስለነበር ከእሱ ጋር ስጫወት በጣም ነው 
ደስ ያለኝና ያኔ እሱ ይመቸኝ ነበር፡፡
–አብሮት ባለመጫወቱ ዛሬም ድረስ 
የሚቆጨው፦
ከካሳዩ አራጌና ከጌቱ ተሾመ ጋር 
አለመጫወቴ በጣም ነው የሚቆጨኝ፤ ከሁለቱም ጋር 
ላለመጫወቴ የቁጭት ስሜት ውስጥ ያስገባኝም ካሳዬ 
የአገራች እግር ኳስ ላይ ተረጋግቶ በመጫወት ኳስን 
ክልል ቦክስ ሸፍኖብህ በመጫወት እንደውም ነፃ የሆነ 
ኳስንም በማቀበሉ የአገሪቱ ምርጥ አማካይ በመሆኑ 
ሲሆን ጌቱ ተሾመ ደግሞ የዘመናዊ እግር ኳስ ላይ 
ቦክስ ቱ ቦክስ በመጫወት ጥሩ ብቃቱን የሚያሳይ 
የሰፈሬ ልጅና አብሮ አደግ ጓደኛዬ ሰለሆነ ነው፡፡
–በእግር ኳስ ተማሮ ኳስ ለማቆም የወሰነበት 
አጋጣሚ፦
ኢትዮጵያ ቡና ውስጥ እያለሁ በአሰልጣኝ 
አብርሃም ተ/ኃይማኖት ዘመን ኳስን ለማቆም ከጫፍ 
ደርሼ ወዲያውኑ ወደ ሙያው የተመለስኩበትነው፤ 
ያኔ ቡድኑን ለቅቄ ወደ ቤቴም ሄጄ ነበር፤ ምክንያቱ 
ደግም የክለቡ የተጨዋችነት ቆይታዬ ላይ ብዙም 
የመሰለፍ እድልን በሜዳ ላይ ታይቼ ከማግኘት ይልቅ 
ማጣቴ ነገሮች ከከለቡ ጋር እንድለያይ ስላደረገኝ 
ያንን አጋጣሚ አልረሳውም፡፡ በኋላ ግን ሐዋሳ ከተማ 
በመግባት ለመጫወት ቻልኩ፤ ቀጥዬ የውሃ ስራ 
ቡድን ውስጥ ገብቼ ተጫወትኩ፡፡
–በፈረንሳዊው አሰልጣኝ ዲያጎ ጋርዚያቶ ይመራ 
በነበረው ቡድን ውስጥ ስለነበረው ቆይታ፡-
የኢትዮጵያ 
ወጣት ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ዲያጎ ጋርዚያቶ 
ሲመራ ያኔ እኔ ለቡድኑ የተመረጥኩት ከዛምቢያ 
ታዳጊ ቡድን ጋር ስንጫወትና ባሳየሁት ጥሩ ብቃትም 
ወጣት ቡድናችን ለአርጀንቲናው የዓለም ዋንጫ 
ሲያልፍ ነበር፤ የአፍሪካ ወጣቶች ዋንጫ ሀገራችን 
ላይ ሲዘጋጅ ግን ከእዚያ በፊት የታዳጊ ቡድናችን 
ተጨዋች ሆነን እኔን ጨምሮ የተወሰኑ ተጨዋቾች 
ማለትም የአወቀ አሰፋ የኤርሚያስ ኪዳኔ ጌዬ እና 
የተካበ ቤቢ ስም ወደ ወጣት ቡድኑ ተጠርተን ስኳዱን 
እንደንቀላቀል ቢደረግም ስማችን ግን ሊላክ ባለመቻሉ 
ስኳዱን በኋላ ላይ ሳንቀላቀል ቀርተናል፤ ያኔ 
አሰልጣኝ ጋርዚያቶ እኛ ወደ ቡድኑ ስማችን ባለመላኩ 
የተነሳ መቅረታችንን ባለማወቅ ተበሳጭቶብን የነበረ 
ቢሆንም በኋ ላ ላይ በታዳጊው ቡድን ዮርዳኖስ 
አባይ ብቻ ነበር ቡድኑን የተቀላቀለው፡፡ የአርጀንቲና 
ስኳድ ከተቀላቀልኩ ግን የነበረውን ቡድን መቼም 
አልረሳውም የእግር ኳስን ሳይደክም የሚጫወት 
ወጣ ያለ ቡድንም ነበር ጋርዝያቶ የሰራው፡፡ ያኔ 
እሱ አገራችን ከፍ ሊይደርጋት ችሏልና በውጭ 
አገር አሰልጣኝ አንዳንዴ መስራትም ጥቅምእንዳለው 
መናገር ይቻላል በተለይ እርሱ ሲያሰራ ታክቲካል 
ደሲችሊን ሆነህ እንድትጫወት የሚያደርግበት 
መንገድ ጥሩ ነው፡፡
–ስለ አርጀንቲና ትውስታው፦የአለም ወጣቶች 
ዋንጫን በአስተናገደችው አርጀንቲና ብዙ የማይረሱ 
ትዝታዎች አሉን፤ የእኛ ቡድን በእግር ኳስ ከፍ 
ያለ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ከእነ ሆላንድ እንደዚሁም 
ደግሞ ኢኳዶርን ከመሳሰሉት ቡድኖች ጋር መጫወት 
ቀላል ነገር አልነበረምና የተለየ ሰሜትን ነው 
ሊፈጥርብን የቻለው፤ ጥሩ ጨዋታን በመጫወትም 
አምባሳደርነታችንን በሚገባ ማሳየትን ችለናል፡፡ 
የእዚህ አገር ጉዞአችን ላይ እኔ መቼም የማይረሱኝ 
አሰልጣኝ ጋርዚያቶ እኔን ይጠራኝና አንተ ገና ህፃን 
ነህ በደንብም ማደግ አለብህ በሚል ራሴን እንዳውቅ 
ያደረገበትና ውድድሩን ቁጭ ብዬ በመመልከት 
ያገኘሁትን ልምድ መቼም ቢሆን አልረሳውም፡፡
-እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ በማለፉ ምን ትርፍ 
አግኝቷል፦
የእግር ኳስ ጨዋታን ልጅ ሆኜ አንስቶ 
አፈቅረውና በጣምም እወደው ስለነበር በመጀመሪያ 
ያገኘሁት ጥቅም በመጫወቴ እርካታን ያገኘሁበት 
መሆኑ ነው፤ እግር ኳስ ቀጥሎ ስራዬም ስለሆነ 
ዛሬ የምመራውን ቤተሰቤን እንዳስተዳድርበትም 
የጥርጊያው በሩን ሊከፍትልኝ የቻለ ነው፤ ከዚያ 
ውጤትም በችሎታዬ ታዋቂ በመሆን ብዙ 
አድናቂዎችን ጥሩ ጥሩ ወዳጆችም በጓደኝነት 
ያገኘሁበት ስለሆነም ትርፉን በእዚህ መልኩ 
ነው የምገልፀው፡፡
–ለባለውለተኛ ተጨዋቾች ስለሚሰጠው 
ክብር፦
ባለውለተኛ ተጫዋቾችን በሚመለከት 
ሁሌም ክብር ሊሰጣቸውና ሊመሰገኑ የሚገባቸው 
ናቸው፤ እኛ ከስር አድገን ስንመጣ የእነሱ 
የምክርና አንዳንድ እገዛዎች ተደምሮበት ነው 
ለጥሩ ደረጃ ልንበቃ የቻልነው፤ ያን ማድረግ 
መቻላችን መልካም ነው፤ እሱን ደግሞ በምንም 
ነገር አታገኘውም እንዚይም ሰዎች ቅን ናቸውና 
ለባለውለተኞቻችን ፈጣሪ ብድሩን ይክፈላቸው 
ነው የምለው፡፡ 
–ወርቃማ ስለነበረው ስለ 1993ቱ 
የኤሌክትሪክ የሶስትዮሽ ዋንጫ ድልና 
ከግጥሚያዎቹ በኋላ ስለነበራቸው 
ፈንጠዝያ፦
የ1993ቱ ኤሌክትሪክ በስፖርት 
ቤተሰቡም ሆነ በእኛ ተጫዋቾች ዘንድ ፍፁም 
የማይረሳ ነው፤በምርጥ ተጫዋቾች የተገባ 
ቡድን ነበር፤ ጥሩ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል 
እንደሚባለው የኛም ቡድን አንድ ነገር ሊያደርግ 
እንደሚችል ያስታውቅ ነበር ሁሉንም ግጥሚያ 
እንደምናሸንፍ እርግጠኛ ስለነበርን ያንን ማሳካት 
ችለናል፡፡ እንደውም አንዳንዴ ገና ሳንጫወት 
ኢንሴንቲቭ ይሰራ የምንልበት ጊዜም ነበር፡፡ 
ለዚህ ቡድን ውጤታማነት የብዙዎቻችን ልጆች 
በተመሳሳይ እድሜ ላይ መገኘት፤ ጥቂት ሲኒየር 
ተጫዋቾች ብቻ ያሉበት በመሆኑና የምንከባበር 
መሆኑ ምንም የሚረብሽ ሰውም ስላልነበር 
እንደዚያ ውጤት ራሳችንን ዘና ለማድረግ ፊልም 
የምናይበት ጊዜም ስለነበር እንዲሁም በሃሳብም 
እንግባባ ስለነበርም ለስኬት ሊያበቃን ችሏል፡፡
–ስለመጀመሪያው ደመወዙ መጠንና ምን 
እንዳደረገበት፦
ኤሌክትሪክ ክለብ ውስጥ የነበረው 
አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ታዳጊ ቡድን ውስጥ 
ስጫወት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠኝ ደሞዝ 30 
ብር ሲሆን የዋናው በድን ላይ ደግሞ 800 ብር 
ነው፤ ታዳጊ እያለሁ ወደ ልምምድ የምንሄደው 
በባስ ነበር፤ ብሩን ስናገኝ እድገት አሳይተን 
በታክሲ ሄድን፤ የጌም ብሩን ደግሞ ለቤተሰቦቼ 
ነው የሰጠሁት፡፡ 
–ደመወዙን አሁን ከሚከፈለው በወር 
166 ሺህ ብር ጋር ሲያነፃፅረው ዛሬ ተጫዋች 
ብሆን ይል ይሆን?
በፍፁም አልልም፤ የገንዘቡ 
መጠን አድጎ ጥሩ ክፍያን እያገኙ ያሉት 
ጊዜው ስለሆ ነው፤ ከእኛ በፊት ያሉት እኮ 
ጥቂት ተከፍሏቸዋል፤ እንደዚህ ማሰብ 
አይነት ተጨዋች አይደለሁም፡፡ የእግር ኳስ 
ተጫዋቾች የእግር ኳስ መጫወቻቸው አጭር 
ከመሆኑ የተነሳ ሲጠቀሙ ማየት በጣም 
ነው ደስ የሚለኝ፤ ያግኙም ማለት ነው 
የምፈልገው፤ግን እንደሚያገኙት ጥቅም በሜዳ 
ላይም የሚቻላቸውን ያህል መስዋዕትነትም 
ይክፈሉ ነው ማለት የምፈልገው፤ ይሄ ደግሞ 
እነሱን ብቻ ሳይሆን ባለሙያዎችንም ጭምር 
የሚመለከት ነው፤ የገንዘቡ ማደግ ብቻ እግር 
ኳሱን ስለማያሳድገው ኳሳ ችንን ለማሳደግ 
የሁሉም ጥረት ያስፈልጋል፡፡
–ስለትዳር ህይወቱና በአሁን ሰአት ኑሮውን 
በምን መልኩ እየመራ ስለመሆኑ፦
የትዳር 
ህይወቴ በጣም ጥሩ ነው፤ በመልካም ሁኔታም 
እየመራሁትም ነው፤ ከልጅነቴ አንስቶ 
የተዋወኳት ጥሩ ባለቤትም ስላለችኝ ደስተኛም 
ነኝ፤ ለእዚህ ደግሞ አምላኬን አመሰግናለሁ፡፡ 
–በበርካታ ደጋፊዎች ታጅበው 
የሚጫወቱትን የቅድስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ 
ቡናን ለመግጠም ሲመጡ ስለሚያደርጉት 
ቅድመ ዝግጅት፦
ቅድስ ጊዮርጊስንና ኢትዮጵያ 
ቡናን ስንገጥም በብዙ ደጋፊዎች ታጅበን 
ነው፤ የእኛም ቡድን ትልቅ ነበር፤ ከእነሱ ጋር 
ስንጫወት ከቡና ጋር ሲሆን ኳስን መስርተን 
እንድንጫወት የምናደርግበት እንቅስቃሴ ነበረን፡፡ 
ከቅድስ ጊዮርገስ ጋርም ስንጫወት እንሱን በምን 
መልኩ መቋቋም እንዳለብን በጥሩ ስነልቦና ላይ 
ሆነን ስለምንገባም በጥሩ ስነ-ልቦና ላይ ሆነን 
ስለምንጓዝ ብዚ ጊዜ እናስቸግራቸው ነበር። 
–ኤሌክትሪክ በእናንተ ዘመን ላይ ኒው 
ጄኔሬሽን የሚል ስይሜን ስለማግነቱ፦
ኤሌክትሪክ 
“ኒው ጄኔሬሽን” የሚል ስያሜን ያገኘው በወቅቱ 
ከስር የሚያሳድጋቸው ጥሩ ችሎታ ያላቸው 
ልጆች ስለነበሩ ነው፤ ያም ቡድን ነው ጥቂት 
ልምድ ያላቸው ልጆችን ብቻ በመጨመር 
የስኬታማነትም ድል ሊጎናፀፍ የቻለው 
የኤሌክትሪክ የ1993 ዓ.ም ቡድንን ስናነሳ ብዙ 
ከስር ያደጉ ልጆች ነበሩበት፤ ውጤታማም 
ሆነ፡፡ ያን ቡድን መቼም ቢሆን አልረሳውም፤ 
አንዳንዴ ከአንዋር ጋር እየተገናኘን ስለዚያ 
ቡድን እናወራለን፡፡ ህልማችንን ነው የኖርነው 
ብለንም እንነጋገራለን፡፡ 
–በአሰልጣኝነት ህይወት ስለመስራቱ፦
ከእግር ኳሱ አካባቢ መራቅን ስለማልወድ 
ነው ወደ አሰልጣኝነት ህይወት የመጣሁት፤ 
ወደዚህሙያ ስመጣ በመጀመሪያ በአሰልጣኝ 
አቤል አስመላሽ ባዬና ጥላሁን የሚባሉ ጓደኞች 
አሉኝ ከእነሱ ጋር ብራይት ስፖርት ክለብ ጋር 
በመጀመሪያ እዚያ ሰራው ከዚያ በኋላ ነብሱን 
ይማረውና ታዋቂው ተጨዋች አሰግድ ተስፋዬ 
ያቋቋመው የአሴጋ ፕሮጀክት ቡድን አለና እሱ 
ጋር መስራት ጀመርኩኝ፡፡ አሁን 3ኛ አመቴን 
በስልጠናው ይዣለው፤ ለአገሬ አንድ ነገርን 
ለመስራትም ስል ነው ወደ ሙያው የመጣሁት፡፡ 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...