
ሀትሪክ፡- ለኢትዮጵያ ቡና
ለመጫወት ፊርማህን አኑረሃል፤
ምን ስሜት ተሰማህ? ክለቡንስ
እንዴት የቅድሚያ ምርጫህ
አደረግክ?
አለምአንተ፡- ኢትዮጵያ ቡና
ለእኔ የመጀመሪያና ተቀዳሚ
ምርጫዬ ሊሆን የቻለው ክለቡ
በአገራችን የእግር ኳስ ታሪክ
በበርካታዎች ዘንድ የሚወደድና
የሚደገፍ ከመሆኑ ባሻገር የአዲስ
አበባም ክልል ቡድን ስለሆነ ነው፤
ከዛ ባሻገር ከአሜሪካ ሀገር ቡድኑን
ለማሰልጠን ለመጣው የአሰልጣኝ
ካሳዬ አራጌም የአጨዋወት ፍልስፍና
የአንተ እንቅስቃሴ አመቺ ነው
በሚልም ጥያቄ ስለቀረበልኝና
በቡድኑም ስለተፈለግኩኝ ቡናን
እንድመርጠውና ወደ ቡድኑ
በመግባቴም ደስተኛ አድርጎኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡና
የአንተን አጨዋወት በመረዳት
እንድትመጣ ያደረጉህ አካላቶች
እነማን ናቸው?
አለምአንተ፡- ኢትዮጵያ ቡና በአሰልጣኝ
ካሳዬ አራጌ አማካኝነት ለሚከተለው የጨዋታ
ፍልስፍና አንተ ትሆናለህ በሚል ለክለቡ
እንድጫወት በመፈለግ እኔን ወደ ክለቡ
ያመጡኝ ሰዎች በምልመላው ላይ ቡድኑ
ኃላፊነት የሰጣቸው የአሰልጣኞች ስብስብ
ሲሆኑ ከእነዛም መካከል አሰልጣኝ ዘላለም
ፀጋዬ /ዞላ/ በዋናነት ይጠቀሳል፤ ከእነዚህ
መልማዮች ውጪም ከክለቡ ፕሬዝዳንት
መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞም ጋር ተነጋግረን
መግባባት ደረጃ ላይ ስለደረስን በእዚሁ ደረጃ
ወደ ቡና ልገባ ችያለው፡፡
ሀትሪክ፡- ስለ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ
የጨዋታ ፍልስፍና ምን የምታውቀው ነገር
አለ? አሰልጣኙንስ ታውቀዋለህ?
አለምአንተ፡- የኢትዮጵያ ቡና የቀድሞ
ተጨዋችና አሰልጣኝ የሆነውን ካሳዬ አራጌን
ሲጫወትና ሲያሰለጥን በታሪክ ስለ እሱ
ሰማው እንጂ እኔ ፈፅሞ አልደረስኩበትም፤
የእሱን የጨዋታ ፍልስፍና በተመለከተ ከብዙ
ሰዎች ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ማድመጥ ችያለው፤
ሲያሰለጥን አንድ ተጨዋች ባለው ነገር ላይ
ሰርቶ ችሎታውን የሚያሳድግበትን እንቅስቃሴ
እንደሚከተልና ተጨዋቹ የሌለውን ነገር
ደግሞ በጊዜ ሂደት እንዲያመጣ የሚያደርግ
በፓሲንግ ፉትቦልና ወደ ቶታል ፉትቦልምየሚያመራ ስልጠናን እንደሚሰጥ ተረድቻለ
ውና ይሄንን እኔ በመልካም ሁኔታ ልቀበለ
ውና በቡናም ጥሩ የውድድር ጊዜን ለማሳለፍ
ተዘጋጅቻለው፡፡
ሀትሪክ፡- ለኢትዮጵያ ቡና ከረጅም
ዓመታት እና ከእነ ዮሴፍ ተስፋዬ፣ ዓሊ
ረዲ፣ ካሊድ መሐመድ፣ ዑመር አብደላ፣
ቴዎድሮስ ብርሃኑና መሰል ተጨዋቾች
በኋላ አንተ ከኳስ ሜዳ አካባቢ በመውጣት
ለክለቡ ልትጫወት ተዘጋጅተሃል፤በዚህ ዙሪያ
የምትለው ነገር ካለህ…?
አለምአንተ፡- የእውነት ነው የአሁን
ሰዓት ላይ ኳስ ሜዳ ተጨዋቾች በጠፉበት
ሰዓት እኔ ከላይ ከጠቀስካቸው ተጨዋቾች
በኋላ ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት ፊርማዬን
ማኖሬ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ አሁን ላይ
በትልቅ ቡድን ደረጃ ከአካባቢያችን ኳስን
የምንጫወተው ከሶስት አንበልጥም፤ ይሄ
ሁኔታ የቁጭት ስሜት ቢፈጥርብኝም እኔ
ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናን በሚያህል ቡድን
ተፈልጌ ለክለቡ ልጫወት ዝግጁ መሆኔ ዕድለኛ
ከመሆኔ ባሻገር ከፍተኛ የደስታ ስሜትም ነው
በውስጤ እየፈጠረብኝ የሚገኘው፡፡
ሀትሪክ፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡና ስታመራ
በየትኛው ሊግ ላይ እንደሚጫወት አውቀህ
ነው?
አለምአንተ፡- ኢትዮጵያ ቡና በየትኛውም
ሊግ ላይ ይጫወት ቡድኑ የእኔ የቅድሚያ
ምርጫ ሊሆን ችሏል፤ ከዛ ውጪ ሌላው ነገር
እኔን አያስጨንቀኝም፡፡
አስተያየት ይስጡ