ቅ/ጊዮርጊስ የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨ
ርስቲና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን
ጠንካራ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋችየሆነውን ደስታ ደሙን ከደደቢቶቹ የአማካይ ስፍራ ተጨዋቾች አቤልና የአብስራ
ተስፋዬ በኋላ ማስፈረም ችሏል፤ ቅዱስጊዮርጊስ ደስታ ደሙን ማስፈረም የቻለው
በተከላካይ ክፍሉ ላይ ያለውን ጥንካሬ
ይበልጥ ለመጨመር እና በእዛም ስፍራ ላይ
በቋሚነት ለመጫወት ጥሩ ፉክክር እንዲኖር
በማሰብ ሲሆን ደስታ ደሙም ወደ ቡድኑ
ከመጣና ፊርማውን ካኖረም በኋላ የሚዲካል
ምርመራን ጨርሶ በአሁን ሰዓት የክለቡ
ሙሉ ንብረት ሆኗል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊሶች ደስታ ደሙን ማስፈ
ረማቸውን ካረጋገጥን በኋላም ተጨዋቹን
ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ በወቅታዊ ጥያቄዎች
ላይ ያናገረው ሲሆን የተጨዋቹም ምላሽ
ከእዚህ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
ሀትሪክ፡- ከሙገር፣ ከደደቢት፣ ከወልዋሎ
አዲግራት ቡድኖች የተጨዋችነት ህይወት
ቆይታህ በኋላ አሁን ላይ ቀጣይ ማረፊያ ቅ/
ጊዮርጊስ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ፊርማህንም
አኑረሃል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን የምትለን ነገር
አለ?
ደስታ፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነት ያለፉት ቅ ዓመታት ህይወቴን ከላይ በጠቀስካቸውቡድኖች ውስጥ በመጫወትና መልካም
የውድድር ጊዜንም በማሳለፍ አሁን ላይ
ለውጥና ዕድገትን በመፈለግ ለቅ/ጊዮርጊስ
ለመጫወት የመጣሁት ቡድኑ የመጀመሪያ
ምርጫዬ ስለሆነ ነው፤ ይህንንም ወደ
ቡድኑ የመግባት እልሜን ስላሳካው በጣም
ደስተኛ ነኝ፡፡
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
ተመርጠህ በምትጫወትበት ወቅት ነው ወደ
ቅ/ጊዮርጊስ ያመራከው፤ ለብሔራዊ ቡድን
መጫወት ስሜቱን እንዴት አገኘከው? ስለ
ወቅታዊ አቋምህስ ምን ትላለህ?
ደስታ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
ተመርጦ መጫወት መቻል ያለው ስሜትና
ደስታ በጣም ከፍተኛ ነው፤ አሁን ላይ ለሀገሬ
እየተጫወትኩ ባለሁበት ሁኔታ ላይ ወደ
ትልቁ ክለብ ቅ/ጊዮርጊስ መምጣት መቻሌም
ችሎታዬን የበለጠ እንዳሳድግም ያደርገኛልና
በእዚህ ላይ በርትቼ እሰራለው፤ ስለ ወቅታዊ
አቋሜ ማለት የምፈልገው አሁን ላይ እኔ
በምፈልገው ደረጃ ላይ አይደለም ያለሁት፤
ያም ሆኖ ግን ከአሁን በኋላ በሚኖረኝ የተ
ጨዋችነት ቆይታ በትልቅ ደረጃ ላይ እንደምገኝ እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለውኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ቅ/ጊዮርጊስን የቅድሚያ
ምርጫህ ያደረግክበት የተለየ ምክንያት አለ?
ደስታ፡- አዎን፤ የመጀመሪያው
ሀገራችን ውስጥ ካሉት ቡድኖች በታሪክም፤
በውጤታማነትም ግምባር ቀደሙ
ክለብ ስለሆነ ነው፤ ከዛ ውጪም በርካታ
ደጋፊዎችም አሉት፤ በእዚህ ታሪካዊ ቡድን
ውስጥ መጫወትን የማይፈልግ ማንኛውም
ኢትዮጵያዊ ተጨዋች የለምና እኔም ይህንን
አውቄና ዋንጫም የማንሳት ናፍቆትና
ጉጉትም ስላለብኝ ነው ወደ ቡድኑ የመጣሁት።
ሀትሪክ፡- ወደ ቅ/ጊዮርጊስ መምጣትህ
የዋንጫ ጥማትህን ይቀርፈዋል?
ደስታ፡- አዎን፤ የደደቢት ተጨዋች
ሳለው ለሁለት ጊዜያት ያህል ይህንን ዋንጫ
የማግኘት አጋጣሚዎች ተፈጥሮልኝ የነበረ
ቢሆንም ወደ መጨረሻ ጨዋታዎቻችን
አካባቢ ሳይሳካልን ቀርቷል፤ ስለዚህም
ይህንን የዋንጫ ጥማቴን በአዲሱ ቡድኔ
የተጨዋችነት ቆይታዬ በእርግጠኝነት
የማሳካው ነው የሚሆነው፡፡
ሀትሪክ፡- ቅ/ጊዮርጊስን የተቀላቀልከው
በየትኛው ሊግ ላይ ይጫወታል ብለህ ነው?
ደስታ፡- ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየቅከኝ፤
አሁን ላይ ለሁለት የተከፈለ ነገር አለ፤ የአዲስ
አበባ ሊግ እንዲሁም ደግሞ የኢትዮጵያ
ፕሪምየር ሊግ፤ ቡድናችን በአዲስ አበባ
ሊግ ላይ ለመጫወት ፍላጎቱን ያሳወቀ
ስለሆነ እኔም ይህንን አመዛዝኜና አውቄም
ነው ለክለቡ ለመጫወት ወስኜ የመጣሁትና
በእዚሁ ለአዲሱ ቡድኔ የሚቻለኝን ጥሩ
ግልጋሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኛለው፡፡
ሀትሪክ፡- በቅ/ጊዮርጊስ የተሳካ የውድድር
ዘመንን ታሳልፋለህ?
ደስታ፡- አዎን፤ ዋናው ጤና ይስጠኝ፤
ጤና ካለህ ሁሉም ነገር ሊመጣ ይችላልና
አሁን ላይ ካለኝ ወቅታዊ አቋም አንፃር ጥሩ
የውድድር ዘመንን የማሳልፍ ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ውስጥ እንደ እነ
አስቻለው ታመነን የመሳሰሉ ተጨዋቾች
በአንተ ቦታ ላይ አሉ፤ ይሄ በቋሚነት ተሰልፎ
በመጫወቱ ላይ አያሰጋህም?
ደስታ፡- በፍፁም አያሰጋኝም፤ ወደ
ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጣሁት እኮ ሁሉንም
ነገሮች አውቄ ነው፤ እንደውም ለመሰለፍ
ፉክክር ወዳለው ቡድን መምጣቴም ጥሩ
ነው፤ አቅሜንም አውቅበታለው፤ ክለቡ
ልምድ ያላቸው ተጨዋቾች አሉት፤ ከእነሱ
ብዙ ልምድ አገኛለው፤ የመሰለፍና ያለመሰለፍ
ሁኔታውን የሚወስነው ደግሞ አሰልጣኙ
እስከሆነ ድረስ ጠንክሬ ሰርቼ በመምጣት
በቋሚ ተሰላፊነት ለመጫወት ጥረትን
አደርጋለው፡፡