….ሁለተኛው አሰልጣኝ ሆነዋል
የሀድያ ሆሳዕናው አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ በቤተሰባቸውና በግል ህይወታቸው ምክንያት ከክለቡ ሃላፊነታቸው ራሳቸውን ማግለላቸው ተሰማ።
አሰልጣኙ ባቀረቡት ምክንያት ከህዳር 1/2016 ጀምሮ ራሳቸውን ከክለቡ ሃላፊነት ማግለላቸውና የፊርማ የወሰዱትን እስከሰሩበት ድረስ ያለውን ቆርጠው ሌላውን ገንዘብ እንደሚመልሱ መግለጻቸውን ከታማኝ ምንጭ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አባተ አሰልጣኙ የቦርዱ ድጋፍ እንዳላቸው ቢገልጹም አሰልጣኙ ግን ራሳቸውን አግልለዋል። ሀድያ ሆሳዕና በእስካሁኑ 5 ጨዋታ 2 ሽንፈት 3 አቻ ውጤት አስመዝግቦ በ3 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኝ ዮሀንስ ከሻሸመኔ ከተማው አሰልጣኝ ጸጋዬ ወንድሙ በመቀጠል ሀለተኛው ራሳቸውን ያገለሉ አሰልጣኝ ሆነዋል።