THE BIG INTERVIEW WITH YOHANNES SAHLE
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- ራስህን የመብት ታጋይ
አድርገህ ትቆጥራለህ?
ዮሐንስ፡- ታጋይ መሆን ብቻ ሳይሆን
ከምንም በላይ የህሊና ጉዳይ ነው፡፡
በማደርጋቸው ነገሮች ህሊናዬ እንዲወቀስ
አልሻም፡፡ በተጨማሪ በእኔ ላይ ሊደረግ
የማልፈልገውን ነገር በሌሎች ላይ ሲደረግ
ማየት አልፈልግም እነኚህ ሁለት ነገሮች
በተሻለ ይገልፁኛል፡፡
ሀትሪክ፡-የተጨዋቾቹ ማህበር መነሻ
ጥንስሱ መቼና እንዴት ጀመረ?
ዮሐንስ፡- ይህን ማህበር ለማቋቋም ብዙ
መስዋዕትነት ተከፍሏል… ብዙ ታግለናል…
እንቅፋቶች መሰናክሎች እያጋጠሙን
እንዳይቋቋም ሰዎች ከጀርባችን ብዙ ነገር
አድርገዋል በግሌም ብዙም ችግር
እንዲፈጠር በህይወቴና በስራዬ
ላይ ጫና ተደርጎብኛል፡
፡ ይህ ማህበር በሀገሪቱ
ደረጃ ፕሮፌሽናል
አሰራር የሚያመጣና
ትልቅ አቅም የሚፈጥር
በመሆኑ ብዙ ጫና
ያደርጉብን ወገኖች ላለፉት
አራት አመታት ታግለዋል፡፡
እኔና ጓደኞቼ ከማህበራት
ኤጀንሲ፣ ውጪ
ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከፓርላማ አፈ
ጉባኤ ድረስ ደርሰን ለፈተን ህልማችንን
አሳክተናል… ዝም ብሎ አልጋ በአልጋ
ሆኖ የመጣ ሳይሆን ብዙ መስዋዕትነት
የተከፈለበት ማህበር ነው.. ታግለን ሃሳባችንን
በማሳካታችን ደስ ብሎኛል…ይሄ ማህበር
የኢትዮጲያ እግር ኳስ ተጨዋቾች ሙያተኛ
ማህበር ይባላል፡፡
ሀትሪክ፡- ምስረታው እውን ሲሆን
የይግባኛል ጥያቄ አልተነሣም?
ዮሐንስ፡- ከዚህ በፊት የነበረ ከኛ ጋር
ተመሳሳይ የሆነ ማህበር የለም፡፡ ብዙ
አለመግባባቶች እንዲፈጠር አንፈልግም… የኛ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች ሙያተኛ
ማህበር ነው.. ሙያተኛ ማህበርና ዝም ብለህ
የምታቋቁመው ማህበር ይለያያል… ለምሣሌ
በኢትዮጵያ የቀድሞ ተጨዋቾች መረዳጃና
ደጋፊዎች ማህበር የሚባል አሜሪካ አገር
አባል የነበርኩበት ከመስራቾቹም አንዱ
የነበረኩበት ማህበር አለ ያ ማህበር
አሁንም መኖር ይችላል መብትም
አለው ከኛ ጋር የሚለየው የኛ
ማህበር ፕሮፌሽናል ተጨዋቾችን
የሚመለከት ብቻ ነው፡፡ በኛ ማህበር
ውስጥ መመዝገብ የሚችለው
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ውስጥ ተመዝግቦና ተጫውቶ
ያለፈ ብቻ ነው….
ፊ ፋ የ አ ገ ሪ ቱ ን
ፌዴሬሽን የሚያውቀው
በዚህ መልክ ነው ፊፋ
በአባልነት መዝግቦናል
ለዚህ ነው ልዩነቱ
መታወቅ አለበት
የምንለው፡፡ የኛ ማህበር
ከዚህ የተነሣ ከሌሎቹ
ጋር በምንም መልኩ
አይጋጭም፡፡
ሀትሪክ፡-ከፌዴሬሽኑ
ውሳኔው በደብዳቤ
አገኛችሁ?
ዮሐንስ፡- ለኛ
የደረሰን ደብዳቤ የለም፡፡
ለክለቦች የተላከውን ደብዳቤ
አይተን ከፌዴሬሽኑ ጽ/
ቤት ኃላፊ ዶ/ር ኢያሱ ተልኮልን ካገኘነው
ደብዳቤ ተነስተን የፃፍነው ነው፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ
ፌዴሬሽን በመንግሥት
የተቋቋመ ማህበር ነው
የኛም ተመሳሳይ ማህበር ነው
ሁለታችም እኩል መብት ነው
ያለን፡፡ ከሁለታችንም በላይ ህገ
መንግሥቱ አለ… ውሳኔዎቹ ህገ
መንግሥታዊ መብቶችን የሚጥስ
ነው፣ የእግር ኳስ ተጫዋቾችኮ
ኢትዮጵያ ሀገራቸው ናት፡፡ ተጨዋቹ
ዜጋ ነው ታክስ ከፋይ ነው በሌላ መንገድ
መታየትም የሌለበት ለዚህ ነው… ውሳኔ
ሲወስን መብታችን ተጥሶ መሆን የለበትም፡
፡ ተቃውሞ የምናሰማው ህግን አክብረን ነው
የማህበሩ አንደኛው አላማ የአባሎቻችንን
መብት ማስከበርና ግዴታቸውን እንዲያውቁ
ነው፡፡ ተጨዋቹ አንድም ጊዜ በደመወዝ ጉዳይ
ሰልፍ ወጥቶ አድማ መትቶ አያውቅም
እስከዛሬ የተሰጠውን እየተቀበለ ነው የኖረው
ከሚሰጠው ገንዘብ ላይ እንደማንኛውም
ሰራተኛ ግብር እየከፈለ ነው ያን ግዴታውን
ተወጥቶም ቢሆን መብቱ ተነክቷል ባይ ነን፡
፡ በመጀመሪያ የተጠራው ስብስባ ፌዴራል
ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ
ፌዴሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ነው ስብሰባውም
ውሳኔ የሚሰጥበት ሳይሆን የውይይት
መድረክ ነው፡፡ የተጠሩ 16 የወንዶች
ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ናቸው እዚህ ስብሰባ
ላይ የተገኙት በፌዴሬሽኑ ህግ የወረዱትም
ሆኑ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉ ተከተውበታል
ይሄ ራሱ የተዛባ ነው፡፡ 16 ተብሎ 3
ሲጨመር 19 ሆነ ማለት ነው፡፡ ድምፅ ሰጡ
የተባለውም የተደበላለቀ ነው ስብሰባው ራሱ
ስርዓት ያለው አልነበረም፤ ሁለተኛው እኛ
የፌዴሬሽኑ አባል ነን፡፡ ማንኛውም መረጃና
ማስረጃ ከፌዴሬሽኑ የማግኘት መብቱ አለን፡
፡ ፌዴሬሽኑ ግን ጥሪ ሲያደርግ ለኛ የተሰጠ
የጥናት ፅሁፍ የለም ዋና ተዋናዩ ግን እኛ
ነን፡፡ ፌዴሬሽኑና ኮሚሽኑ የጠሩት ስብሰባ
የተጨዋቾችን ደመወዝ በተመለከተ ነው
ስለኛ ለማውራት ተሰብስበው የምናውቀው
ነገር ግን የለም ራሳችን እንድንከላከል እድሉን
አልሰጡንም ይሄ ራሱ ደግሞ የአባልነት
መብታችንን መግፈፉን ያሳያል በአንድ ወገን
ብቻ ያሉ ወገኖች የተሰባሰቡበት ውይይት
ነበር ይሄ ኢፍትሃዊ ድርጊት ነው በተጨማሪ
በፌዴሬሽኑ ደንብ መሠረት ማንኛውም
የተጨዋቾች ጉዳይ ፍ/ቤት አይሄድም ይላል
እነርሱ ግን የመንግሥት አካል ይዘው ነው
ያስወሰኑት፡፡ ኮሚሽኑ የመንግሥት አካል ነው
ያንን ይዘው ነው የወሰኑት.. የራሣቸውን
ደንብም ጥሰዋል ፌዴሬሽኑ ይህን ማሰብ
አለበት፡፡ ሌላው የፌዴሬሽኑ አባል መብታችንን
ለማስከበር እንዳንችል በተገቢ መንገድ ጥሪው
አልደረሰንም፡፡
ሀትሪክ፡-በወቅቱ አንተ እንዴት ተገኘህ?
ዮሐንስ፡-የተገኘሁትማ ለሁሉም ጥሪ
ካደረገ በኋላ ነው ሲጀመር ለአስልጣኞች
ማህበር ለዳኞችና ታዛቢዎች ማህበርም
በተመሳሳይ ጥሪ ማድረጉን ከሚዲያ
ሰምተናል…ሚዲያው እንዴት ዋነኛ ተዋናይ
የተጨዋቾች ማህበር አልተገኘም ብሎ ሲያወራ
ነው ያወቅነው፡፡ ለኮሚሽኑ ፍቃድ ያለን ህጋዊ
ማህበር መሆናችንን ለኮሚሽኑና ለፌዴሬሽኑ
ማስረጃችንን ይዤ ሄጄ ረቡዕ ዕለት አስገባው
ሀሙስ ተደውሎ ለአርብ ስብሰባ ተገኙ
ተባልን በዚህ መንገድ ነው የተገኘነው፡
፡ ለውይይት ጠርተውን ውሳኔ ማሳለፋቸው
ተገቢ አይደለም፡፡ ውሳኔው ሊወሰን የክለቦች
ፕሬዚዳንትና ስራ አስኪያጆች ተጠርተዋል፡፡
የየክልል ኮሚሽነሮችም ተገኝተዋል፡፡ ቅዱስ
ጊዮርጊስ፣ ደደቢትና ስሁል ሽረ አልመጡም
ከምሳ በኋላ ደግሞ ወልዋሎ አዲግራት
አልተገኘም፡፡ ይህን ቀድሜ ባውቅ ኖሮ አንድ
ተወካይ እኔ ብቻ ስጠራ አልሄድም ነበር፡፡
ያውም የማዳመጥና ሀሳብ የመሰንዘር እንጂ
ድምጽ የመስጠት መብት አልነበረንም ይሄ
ሁሉ ስህተት ነው በኛ ላይ ሲወሰኑ ቁጭ
ብለን ነው የተመለከትነው… ከፍትህ አንፃር
ውሳኔ የሚሰጥ ከሆነ የክለቦቹ አምበሎች
ሊገኙ ይገባ ነበር እኩል መብት ማግኘት
ነበረብን፡፡ ሙያተኞች ላይ ሲወሰን እነርሱ
የሚሰሙት ከሚዲያ ነው ታዲያ የቱ ጋር
ነው መብታችን… ውሳኔው ፍትሃዊ አይደለም
መሻር አለበት ብለን እየጠየቅን ነው፡፡
ሀትሪክ፡-ማህበሩና ተጨዋቾቹ አሁን
ያላችሁ ግንኙነት ምን ይመስላል?
ዮሐንስ፡-የተፈጠረው ችግር ለኛ አንድነት
ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሯል ማለት ይቻላል፡
፡ ተጨዋቹ የሙያ ብቻ ሣይሆን የዜግነት
መብት እንዳለው እየገባው መጥቷል፡፡
ውሳኔውን የወሰኑ ግለሰቦችኮ እንደኛ ተቀጣሪ
ናቸው፡፡ ይሄ በፍ/ቤት ወይም በፓርላማ
የተወሰነ አይደለምና መስተካከል አለበት
ውሳኔው በዜጎች ላይ የተጫነ በመሆኑ
መወገድ አለበት ጉዳዩን ከሙያና ከዜግነት
አንፃር የምናየውም ለዚህ ነው ተጨዋቹ
ቤተሰብ ልጅ የሚያስተምር ብዙ ኃላፊነት
ያለበት ነው በአንድ ስብሰባ ላይ ይሄን
ያህል ይበቃዋል ማለት ምን ማለት ነው
ከምን ተነስተው ምን መብት ኖሯቸው ነው
የወሰኑት? የክለቦች ወክለዋቸው የመጡት
ብቻ ሣይሆኑ እኛም የመንግሥት አካል
ነን፡፡ መንግሥት ለስፖርቱ የበጀተውን
የሚያመጣው ከዜጎቹ የታክስ ከፋዮች ያገኘው
ነውና ገንዘቡም ይመለከተናል፡፡ ውሳኔውን
ለመወሰን እንደሆነ ብናውቅ ጉዳዩን ወደ ህግ
እንወስደዋለን እንጂ አንሄድም ነበር፡፡ ድምጽ
የመስጠት መብት ተከልክለን እንዴት መብት
አላችሁ ይባላል? መልስ መስጠት ራሱን
የመከላከል መብት አጥቶ ስብሰባ ላይ አለ
ማለት ይከብዳል፡፡ እንዴት በኛ ጉዳይ ላይ እኛ
ታዛቢ እንሆናለን ይሄኮ የተጨዋቾችን መብት
መርገጥ ነው ይሄ ራሱ ፍትሃዊ አይደለም፡፡
ስብሰባው ላይ በደመወዝ ጉዳይ የመንግሥት
ክለቦች ነን መወሰን እንችላለን ነው ያሉት፡
፡ የመንግሥት ያልሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊስና
ኢትዮጵያ ቡናንስ ምን ሊያደርጓቸው ነው?
እነሱንም ሊያስገድዱ ነው? በህግ ይችላሉ
ብዬ አላስብም፡፡ ይሄ ሊስተካከል ይገባል
ራሱ ስብስባው የስብስባን መርህ የተከተለ
አይደለም፡፡ ሁለቱ ክለቦች ባይመጡም
በውሳኔው ሊገደዱ አይችሉም ባይ ነኝ፡፡
በእግር ኳሳዊ አካሄድ መስማማት ካልተቻለ
በፊፋና በካፍ ህግ ይዳኛል ካልተግባቡ ወደ
ካስ ይጓዛል ይላል፡፡ ይሄ የፌዴሬሽኑ ደንብ
የሚለው ነው እነርሱ ይህንንም ነው የጣሱት፡
፡ በተቻለ መጠን በሀገራችን ህግ በዜግነት
መብታችን እንከራከራለን ከዚያ ውጭ ከሆነ
ጉዳዩን ወደ ካስ (አለም አቀፍ የግልግል ፍርድ
ቤት) እንወስደዋለን፡፡
ሀትሪክ፡-አሁን የሚከፈለውም ገንዘብ ሆነ
50 ሺህ ብሩ ከተጨዋቾቹ አቅም አንፃር ከበቂበላይ የሆነ ክፍያ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ…
እንደ ማህበር ምን ትላለችሁ?
ዮሐንስ፡-የተጨዋቹ ደመወዝ በ50
ብር፣ በመቶ ብር፣ በ150 ብር፣ በ300
ብር፣ በ400፣ በ10 ሺህ፣ በ20ሺህ 30 ሺህ
እያለ አሁን 300 ሺህ ብር ደረሰ፡፡ ይሄ የነፃ
ገበያው የፈጠረው እድል እንጂ ተጨዋቹ
አልፈጠረውም.. አድማ መትቶ ስራ አቁሞ
መንግሥትን በጥብጦ የመጣ ክፍያ አይደለም
እኛ እያልን ያለነው ገቢያው ይወስን እንጂ
እናንተ አትወስኑብን ነው የእግር ኳሱን ክፍያ
ገበያው እንጂ ክለቦቹና ፌዴሬሽኑ እንዲወስኑ
አንፈቅድም ከ100 ብር ተነስቶ 300 ሺህ
የከተቱትኮ ክለቦቹ ናቸው አንድ መስሪያ
ቤት ከ10 ሺህ ብር አንስቶ 300 ሺህ ብር
ልከፍል ቢል የክለብ አመራሮቹ እንቢ የሚሉ
ይመስላል? አይሉም፡፡ 300 ሺህ ብር ቢሰጥህ
መጠየቅ ያለበት ሰጪው እንጂ ተከፋዩ
አይደለም፡፡ ይሄኮ በእግር ኳስ ላይ ያሉ
አመራሮችን የሚያስገመግም ይመስለኛል፡፡
100 ብር የምታወጣ ዶሮ 400 ብር ከገዛሁ
ሰውየው ምን አደረገ? እኔ ነኝ መጠየቅ
ያለብኝ… 400 ብር አያወጣም ማለት ያለበት
ገዢው ነው ታዲያ ምን አጠፋ ተጨዋቹ?
አውሮፓም እንግሊዝ አገር 1 ሺ ዶላር
ሲከፈል ተቃወሙ 10 ሺህ ሲደርስ አበዱ
አሁንስ የት ነው ዋጋው ያለው? ገበያው
የፈጠረውን እድል ተቀብለዋል፡
፡ እኛ የምንለው የእግር ኳሱን
ክፍያ ገበያው እንጂ ክለቦቹና
ፌዴሬሽኑ አይወስኑ እያልን
ነው ዝቅተኛም ሆነ ከፍተኛ
ሳንቃወም ተቀብለናል 50
ይበቃል 70 ይበቃል ማለት
ግን ተገቢ አይደለም ነው
የምንለው፡፡
ሀትሪክ፡- ከሀገሪቱ የኢኮ
ኖሚ ደረጃ አንጻር ክፍያቸው
ተጋኗል መቀነስ አለበት
የሚሉም አሉ፡፡ ይሄስ ልክ
አይደለም?
ዮሐንስ፡- የኢትዮጵያ
ኢኮኖሚና ስፖርቱን በምን ደረጃ
ነው የምናገናኘው? ቻይናን
ተ መ ል ክ ት ኳሷ ታች
ነው ክፍያው ግን ከላይ ነው አይገናኙም…
እግር ኳሱን ለማሳደግ ከፍተኛ ክፍያ
እየፈፀመች ነው አሜሪካንን ተመልከት
ህንድንም እይ… ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው
የሀገራቸውን ኳስ ለማስተዋወቅ እየሰሩ
ነው እነ ጋና ናይጄሪያ የሚከፍሉት ክፍያ
በሀገራቸው ብር ሲመነዘር የትየሌለ ነው፡
፡ ጋና 1 ሺህ ዶላር ትከፍላለች ትንሽ ነው
ይባላል…. በሀገሪቱ ብር ሲመነዘርኮ በኛ ደረጃ
ወደ 200 ሺህ ብር ነው ይሄ ነው ትንሽ…?
የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚለው አያዋጣም… እኛ
ኢኮኖሚስት አይደለም ተጨዋቹ 100 ብር
ደመወዝም ተቀብሏልኮ.. ያኔ ታዲያ የሀገሪቱ
የኢኮኖሚ ደረጃ ነው ሊባል ነው? ያ ከሆነስ
ለምን 300 ሺህ ብር አወጡት? መጠየቅ
ያለባቸው እነርሱ ናቸው ግለሰቦች ተሰብስበው
ሳይሆን የገበያው ደረጃ የተጨዋቾቹን
ደመወዝ መወሰን አለበት ባይ ነኝ፡፡ እግር
ኳስ ስራ ነው ቤተሰብ የሚመራበት ልጆቹን
የሚያሳድግበት ስራው መነካት የለበትም፡፡
ሙያተኞች ናቸው ወይ ይሄን የሚያደርጉት?
ወይስ መንግሥትን ለማስደሰት ነው? ጠቅላይ
ሚኒስትር ዶክተር አብይ እግር ኳሱ በሌለበት
ሲሉ ተጨዋቹ ብቻ ነው እንዴ የሚጠየቀው?
መልሱ በትክክል መመለስ አለበት፡፡
ሀትሪክ፡-መንግሥት ስፖርቱን በሚገባ
ተከትሎ ርምጃ ወስዷል ማለት
ይቻላል?
ዮሐንስ፡-አይመስለኝም… የአገሪቱ
መሪዎች የተለያዩ
ሙያ ላይ ያሉ ሰዎችን
ጠርተው ሲያነጋግሩ
ስፖርቱ አካባቢ
ይሄ አልተደረገም፡፡ ይሄ ለስፖርቱ
ያላቸውን ርቀት ነው የሚያሳየው፡
፡ ከፍተኛ ገንዘብ
የፈሰሰበት ከሆነ ተገቢ ቦታ ላይ
ዋለ ወይስ አልዋለም
የሚለውን መንግስት
መከታተል ነበረበት ይሄ
እግር ኳስም ሆነ አትሌቲክስ ሌሎች
የስፖርት አይነቶችን መመልከት አለበት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በቅርብ
ጊዜ ውስጥ የሚመለከታቸውን ባለሙያዎችን
ጠርተው ያነጋግራሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- የእግር ኳሱ ደረጃ አድጓል
ወይስ አላደገም… እንደ ባለሙያ ምን ትላለህ?
ዮሐንስ፡- እግር ኳስ አደገ የሚባለው
ውጤትን ብቻ አይቶ አይደለም… በኔ ግምት
ምን ያህል አሰልጣኞቻችን በመላው አለም ላይ
ሄደው ያሰለጥናሉ? ምን ያህል ተጨዋቾች
ውጪ ሀገር ሄደው ይጫወታሉ? ምን ያህል
ዳኞቻችን ወደ ውጪ ወጥተው ይዳኛሉ?
የሚለው የእድገታችንን ደረጃ ያሳያል ብዬ
አስባለው… ቡናና ጊዮርጊስ ስለተሸናነፉ
መቀለና ጅማ ዋንጫ ስለወሰዱ የኳስ እድገት
አይደለም እድገት ሲባል ምን ያህል ተተኪዎች
አሉ? የስፖርት ፋሲሊቲዎቻችን ምን ያህል
ተቀባይነት አላቸው? እነኚህ ሁሉ ምላሽ ካገኙ
በኋላ ነው ስለ እድገቱ ሊነገር የሚችለው
ሀትሪክ፡- በአንተ ግምገማ እድገቱ አለ?
ወይስ ታች ነን?
ዮሐንስ፡- በኢንተርናሽናል ውድድር
ሜዳዎቻችን ተቀባይነት አጥተዋል
ሊያመልጠን የማይገባን የቻን ውድድር
ተሰርዞብናል… እንደ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ
አይነት ከሀገር አልፈው አፍሪካን የሚመሩ
መሪዎች ማፍራት አለብን ባለፉት 28
አመታት ግን ይህን ማድረግ አልቻልንም፣
በተጨዋች ደረጃ 1 አውሮፓ 2 አፍሪካ
ናቸው ሶስተኛው ጋቶች ከግብፅ ክለብች
ተሰናብቷል… ከ100 ሚሊዮን ህዝብ
ያሉን 3 ናቸው፣ በየጊዜው ተተኪ
እያፈራን አይደለም፡፡ በአፍሪካ ደረጃ
የአለምና የአፍሪካ ዋንጫ ላይ
ያጫወተ የምናውቀው ዳኛ አንድ
ነው.. ሌሎቹ በአርቢትር በአምላክ
ተሰማ ደረጃ ባይሆኑም ብቅ እያሉ
እየተጠሩ ነው የአፍሪካ ዋንጫ
ሲጀመር የነበረን ዳኛ አንድ
ነበር ከአመታት በኋላ ያለን
አንድ ነው ይሄን ሁሉ ስናይ
ማደግ አለማደጋችንን
ማወቅ እንችላለን…
ውጤት ብቻ የእድገት
ማሳያ ነው ብዬ
አላምንም፡፡
ሀትሪክ፡-መቐለ 70 እንደርታና
ወልዋሎ አዲግራትን መርተሃል የደርቢ
ተፋላሚዎችን እንደማሰልጠንህ ጫና
አልተፈጠረብህም?
ዮሐንስ፡- ጫና የለውም፡፡ በሁለቱም
ወገን መታወቄ ሠላማዊ ነገር እንዲኖርና
ውድድሩ በሰላም እንዲያልቅ ልዩነቱን አርጋቢ
ሆኛለው… በመቐለም ደጋፊ ጥሩ ተቀባይነት
አለኝ በሰራሁት ስራ በመወደዴ የአርጋቢነት
ሚናዬ ተሳክቶልኛል ማለት ይቻላል፡፡
ሀትሪክ፡- የባህርዳር ከተማና የአዳማ
ከተማ አሰልጥነን ጥያቄ ትተህ በወልዋሎ
አዲግራት ኮንትራትህን ያራዘምከው በምን
ምክንያት ነው?
ዮሐንስ፡- እግር ኳስ ህይወቴ ነው፡፡ የትም
ቦታ ቢሆን ኳስ ካለ እመለከታለው፡፡ ብዙውን
የዝውውር ነገር በደንብ የሚያወቁት ኤጀንቶቼ
ናቸው… ሁኔታውን አይተው መርምረው
የተሻለ ነገር አገኘን ሲሉ መስማማት ብቻ
ነው የኔ ኃላፊነት.. የተሻለና ለኔ የሚመቸውን
መርምረው ሲወስኑ ፈርምኩ.. ዝርዝሩን
የሚያውቁት እነርሱ ናቸው፡፡
ሀትሪክ፡- አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
አግሬሲቭ ነው እንጂ ሙሰኛ አይደለም
የሚሉ በርካቶች ናቸው?
ዮሐንስ፡- (ሳቅ) አልስማማም… አግሬሲቭ
የሚለው እኔን አይገልጸኝም፡፡ አግሬሲቭ ነው
የሚባለው ስንት ሰው ደበደብኩ ማንንም፤ ስንት
ሰው ጋር በማይሆን ቦታና ጊዜ ተገኝቻለው
ይሄም ዜሮ ነው፤ አቋም አለው በአቋሙ
የፀና ነው ከተባለ ይወክለኛል፡፡ ሙያውን
የማይሸጥ በጥቅም የማይደለል… ለሚሰራው
ስራ ተገቢ ክብር ያለው የሚለው ይገልፀኛል፡
፡ በዚህ ደረጃ አቋም በመያዜ ግትር ነህ ልባል
ይችል ይሆናል ይሄን እቀበላለው፡፡ የምወደው
መማርና ማስተማር ነው እነኚህ ደግሞ
ከሰዎች ጋር ተግባብቶ መኖርን ይጠይቃልና
በዚህ የምታማ አይደለሁም፡፡ በሙስና ደረጃ
ከተጨዋቾች ጋር የማልሞዳሞድም ነኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ከአሰልጣኞች ጋር ያለህ
ግንኙነት መልካም ነው ማለት ይቻላል?
ዮሐንስ፡- አዎ እግር ኳስ ግን ፍልሚያ
ስላለበት በጨዋታ ስንገናኝ ተፋላሚ ነን፡፡
በቃ ከዚያ ውጪ በግል የምጣላው የለም፡፡
ከወንድሜ ጋር ባላጋራ ሆነን ተጫውተናል፡፡
እኔ ለጊዮርጊስ ወንድሜ ለኦሜድላ ሲጫወት
ተገናኝተናል… ሜዳ ላይ ሳገኘው አለቀውም
እርሱም አይለቀኝም፡፡ ያ የማሊያ ጉዳይ
ነው ከዚያ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ በጋራ
ተጫውተናል ሲቀጥል ቤት አብረን አንድ
ላይ ነን፡፡ እግር ኳሱ ከሚፈጥራቸው ውጪ
ሌሎች ችግሮች ከማንም ጋር የለብኝም፡፡
ሀትሪክ፡-ጓደኛ የለውም… ብዙ ጊዜ
ከአሰልጣኞች ጋር አይታይም ይሉሃል..
እውነት ነው?
ዮሐንስ፡- ጓደኞች የምላቸው የስራ
ጓደኞች አሉኝ.. በግል ህይወቴ የምገናኘው
ግን ከእግር ኳስ አለም ከወጡ ሰዎች ጋር
ነው.. ሙያዬን በሚመለከት ዕርዳታ ጠይቆኝ
እንቢ ያልኩት ሰው በፍፁም ትዝ አይለኝም፤
ይሄ ነው እውነቱ፡፡
ሀትሪክ፡ በአሰልጣኝነትህ ህይወትህ
በሰጠኸው ውሳኔ ልክ አይደለሁም ብለህ
የተፀፀትክበት ጉዳይ አለ?
ዮሐንስ፡-ይሄን ለምን ወሰንኩ ብዬ
አይደለም ነገር ግን የማልረሳው ገጠመኝ
አለ፡፡ ከአልጄሪያ ጋር ተጫውተን 7ለ1
ከተሸነፍንበት ጨዋታ በፊት 22 ሰዓት ያለ
ምግብና መኝታ ተጉዘን ነበር፡፡ ተጨዋቾቼን
ሳነጋግራቸው በእነዚህ ልፋት ውስጥ
ገብታችሁ ችግር ከሚገጥመን በደንብ
ሳታርፉም ቢሆን አስገድጃችሁ ውጤት
አምጡ የምልበት መብት የለኝም፡
፡ ስለዚህ አንጫወትም አካላችን ብቁ
አይደለም አዕምሮአችን ዝግጁ አይደለም
አልተከበርንም ባንዲራውን ወክለን
መጥተን ተሰቃይተናል የምትሉ ከሆነ
ከጎናችሁ ነኝ ስላቸው እንግባና የፈለገው ነገር
ይምጣ… በኑሮአችን ላይ አደጋ ይፈጥራል
ብለው ወደ ሜዳ መግባታቸው ቅር አሰኝቶኛል፡
፡ በራሴ መወሰን ባለመቻሌ ቅሬታው አሁንም
አለ፡፡ ያ ነው የሚቆጨኝ፡፡
ሀትሪክ፡-በአቶ ሳህሉ ገ/ወልድ የአመራር
ጊዜ ፍ/ቤት ወስደህ ካሸነፍክ በኋላ የካሳ
ገንዘቡን ለበጎ አድራጎት ሰጥተሃል… እውነት
ነው?
ዮሐንስ፡- አዎ እውነት ነው… ገንዘቡን
የሚያውቀው ጠበቃዬ ነው ወደ ፍ/ቤት
የሄድነው ፍትህ ፈልገን ብቻ ነው ስለ ካሳ
አላስብንም ካሳው ሲሰጠን ደግሞ ለበጎ
አድራጎት እንዲሰጥ አድርገን መጥተናል፡
፡ ይሄ ደግሞ ደስተኛ አድርጎናል፡፡ በወቅቱ
የገንዘቡ ጉዳይ ሳይሆን በፌዴሬሽኑ ውሳኔ
ክፉኛ ተበሳጭቻለሁ፡፡ እግር ኳሱ በሙያተኞች
ይመራ በማለቴ ነው የተቀጣሁት፡፡ ይሄ
ደግሞ ተገቢ ባለመሆኑ ወደ ፍ/ቤት
ወስጄዋለው ስፖርቱን እየመሩ ያሉት ሰዎች
የሌላ ሙያ ባለቤት ሊሆኑ ይችላሉ በኳሱ
ደረጃ ያላቸው እውቀት ሲታይ ግን በተግባር
የታየው የመምራት አቅም ችግር ያለባቸው
ናቸው ለዚህ ነው አሁን የተፈጠረው ችግር
ሊፈጠር የቻለው…ስፖርቱ በባለሙያ ይመራ
በማለቴ በአሰልጣኝነት፣ በማናጀርነትና
በቴክኒክ ዳይሬክተርነት እንዳልመራ
ፌዴሬሽኑ በመወሰኑ ፍ/ቤት ወስጄ በማሸነፌ
ተደስቻለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ዋሊያዎቹና ክለቦቻችን እንዲ
ያድጉ ምን ይደረግ ትላለህ?
ዮሐንስ፡- እግር ኳስ ሁልጊዜም የሚኖር
ነው ትልቁ ነገር ሌሎቹ እንደሚሄዱት እየሄድን
ነው ወይ የሚለው ነው፡፡ ወይም ሌሎች
እንደሄዱት ሄደውም እንዳደጉት እንዳንሆን
ያደረገን ምንድነው ብሎ መነጋገር አለብን…
አንዴ ላይ ሌላ ጊዜ ታች የምንሆነው ከፍ
ያላልነው ለምንድነው የሚለው ላይ መነጋገርና
መፍትሔውን ማግኘት የግድ ይለናል፡፡
ሀትሪክ፡- አርቢትሮች ላይ ያለህ እይታ
ምን ይመስላል?
ዮሐንስ፡- ከማንኛውም ዳኛ ጋር ተነካክቼ
አላውቅም ትዝም አይለኝም ማን እንደሚዳኝ
ማወቅ እንኳን አልፈልግም… ዳኞች ላይ
ትኩረት ሰጥቼ ይሄ ዳኛ እንዲህ አደረገን
ብዬ ተናግሬ አላውቅም፡፡ እኛ አሰልጣኞች
እንደምንሳሳት ዳኞችም ሊሳሳቱ ይችላሉ
100 በመቶ ዳኛ ችግር ፈጠረ ብዬ አስቤም
አላውቅም እንዲያውም ሃይም ባይም
ያልኳቸው ጊዜ ትዝ አይለኝም ስራቸውን
ሰርተው እንዲወጡ እመኛለው… ያለባቸውን
ጫና በተለይ ባለፉት 3 እና 4 አመታት
እያየሁ ስለሆነ ለነርሱ ነው የማዝነው፡፡
ሀትሪክ፡- ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት
ለመምራት ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆንህ
አይከለክልህም?
ዮሐንስ፡- (ሳቅ) የትኛውም ማህበር
የሚቋቋመው በሀገሪቱ ህገ መንግሥት መሰረት
ነው.. ባለፈው ጊዜ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን
እንዳንሳተፍ ተከልክለን ነበር፡፡ በ2011
በወጣው አዋጅ ግን በማህበራት ጉዳይ ኤጀንሲ
ብዙ ደንቦች ተቀይረዋል በኤን.ጂ.ዮ እና
በዲያስፖራ ደረጃ ብዙ ነገሮች ተቀይረዋል፡
፡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና
ለስፖርት ኮሚሽን ህጉ ተልኳል ነገር ግን
በፌዴሬሽኑ ህግም ቢሆን አመራር ለመሆን
ትውልደ ኢትዮጵያዊ እንዳይሰሩ የሚያግድ
አዋጅ አልነበረም.. በ1994 ዓ.ም ግን ገብተን
እንድንገለግል ነው ሕጉ የወጣው… ፌዴሬሽን
ግን አሁን ድረስ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ
እያለ እገዳ ማድረጉ ልክ አይደለም፡፡ አዋጅ
ጥሰው እየሰሩ ነው በቀጣዩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ
አዋጁን ተግባራዊ ያደርጋሉ ብዬ አስባለው…
በአዋጅ የተቋቋመው ፌዴሬሽን አዋጅ ጥሶ
መኖር አይችልም፡፡ እስከዛሬ ድረስ በተለይ
ባለፉት 17 አመታት የሀገርን አዋጅ ጥሰው
ነበር ፌዴሬሽኑን ሲመሩ የነበረው… ትውልደ
ኢትዮጵያዊ ለዋሊያዎቹ እየተጫወተ ሌላው
ይከለከላል፡፡
ሀትሪክ፡-ተጨዋችና አሰልጣኝ ይችላል…
በአመራር ደረጃ ነው ክርክሩ የነበረው…
አመራር መሆንስ አሁን ይቻላል?
ዮሐንስ፡- ኢትዮጵያዊ ተብለህ እየተጫ
ወትክ ሌላው መከልከሉ በሕግ የተገደበማ
አይደለም፡፡ አሁንማ ትውልደ ኢትዮጵያዊ
ሙሉ መብት አለው፡፡ እናንተም ብትሆኑ
ይህን አልጠየቃችሁምና ተጠያቂ ናችሁ…
ለባንዲራው መጥቶ የሞተ ሰው እዚህ ደግሞ
በነፃ ላገልግል ሲል አትችልም መባሉ ልክ
አይደለም ምክንያቱ ግን ስልጣን ነቻ! አሁን ግን
ያለው የማህበር አዋጅ ትውልደ ኢትዮጵያዊ
ገብተው እንዲያገለግሉ እንዲሳተፉ ፈቅዷል
በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡
ሀትሪክ፡-ጨረስኩ.. ቀረ የምትለው ነገር
አለ?
ዮሐንስ፡-መናገር ያለብኝን ሁሉ ተናግሬያ
ለሁ ቀረ የምለው ነገር የለም፤… በዚሁ
አጋጣሚ ግን አምላኬን እግዚብሔርን አመሰ
ግናለሁ፡፡