ኡመድ ኡኩሪ በትናንትናው እለት ለግብፁ ክለብ ስሞሃ ለሶስት አመት ለመጫወት ፈርሟል፡፡ኡመድ ኡኩሪ በ2016/17 የግብፅ ፕሪምየር ሊግ ካሳየው ጥሩ ብቃት በተጨማሪ ከኮከብ ጎሎ አስቆጣሪዎች ተርታ መሆን ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል በግብፅ ሊጎች ተፈላጊነቱ እንዲጨምር አድርጎት ነበር ።
የግብፁ ክለብ ስሞሃ በድህረገፁ የኡመድ ኡኩሪን ዝውውር ይፋ አድርጎ ኡመድ እንኳን ደህና መጣህ በማለት ለደጋፊዎቹ የተጨዋቹን ዝውውር አብስሯል።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ወደ ግብጽ አምርቶ በግብፅ ክለቦች ለኢትሃድ አልክሳንደሪያ፣ ኢ ኤን ፒ ፒአይ እና ኤል ኤንታግ ኤል ሃርቢ ክለብ መጫወት ችሏል፡፡
አስተያየት ይስጡ