የቀድሞው የሉሲዎቹ ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል በኡጋንዳ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል።
አሰልጣኙ የሚመራው የካምፓላ ኩዊንስ ቡድን ከሜዳው ውጪ ቶሮ ኩዊንስን ገጥሞ 0 ለ 0 ተለያይቷል።
ውጤቱንም ተከትሎ ነጥቡን 48 በማድረስ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
ቡድኑን ከሊጉ የአምስተኛ ሳምንት ጀምሮ ሲመራ የነበረው ፍሬው ኃይለገብርኤል ካደረጋቸው 16 ጨዋታዎች በ14 አሸንፎ በአንድ አቻ ሲለያይ በአንድ ብቻ ተሸንፏል።
- ማሰታውቂያ -

ቡድኑ የሊግ የመጨረሻ ጨዋታውን በቀጣይ ሳምንት መጨረሻ ከሺ ማሮን ክለብ ጋር በሜዳው ያደርጋል።
በተጨማሪም በየጥሎ ማለፍ ውድድር የሩብ ፍፃሜ ከሴንት ኖአ ጋር በመጪው ረቡዕ ጨዋታውን ያደርጋል።


