መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ አሰልጣኝ ደረጄ በላይ ከመድህን ጋር ስላላቸው የወደፊት ቆይታ ይናገራሉ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

አሰልጣኝ ደረጄ በላይ ከመድህን ጋር ስላላቸው የወደፊት ቆይታ ይናገራሉ

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያ መድህን  ከወር በፊት ቡድኑን የተረከቡት አሰልጣኝ ደረጄ በላይ ክለቡ ጋር ስላላቸው እቅድ እና ስለ ቀድሞ ቡድናቸው ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ክለቡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 25ተኛ ሳምንት ድረስ ባለው ውጤት በምድብ-ሀ  25 ጨዋታዎችን ተጫውተው በ4የጎል ክፍያ በ31 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ መድህንን እንዴት አገኘኸው   ?

ደረጄ:- ክለቡ ጥሩ ክህሎት ያላቸው ልጆች አሉት በአሁኑ ሰዓት እየሰራሁ ያለሁት ለቀጣይ አመት እሚሆነኝን ቲም እየሰራሁ ነው፡፡ አሁን ያለው ስብስብ በቀድሞ አስልጣኝ ያለውን ቲም ነው የያዝኩት አሁን ያለውን ቲም እንደ አዲስ ለኔ የጨዋታ ታክቲክ በሚሆን  መልኩ መገንባት አለብኝ፡፡ ለቀጣዩ አመት ከራሴ ፍልስፍና ጋር እሚሄዱ ተጨዋቾች ለመስፈረም እና ክለብ ውስጥ ምርጥ እሚባሉ ልጆችን ውል ለማደስ እየተነጋገርኩ ነው፡፡


የክለቡ ኃላፊዎች አቀባበል እንዴት አገኘኸው ?

ደረጄ- ያሉት ነገሮች እንዳሉ ነው፡፡ ከጀመርኩ ቅርብ ግዜ ነው ፡፡ያሉብንን ችግሮች ተቀራርበን ለመፍታት እየሞከርን ነው፡፡በቀጣዩ ዓመት ክለቡን ወደ ኘሪሜየር ሊግ እንደማሳድገው ቃል ገብቼላቸዋለሁ፡፡

ከቀድሞው ክለብህ ጅማ አባቡና  ጋር ያለህ ግኑኘነት ምን ይመስላል ፡፡ ክለቡ በኘሪሜየር ሊጉ ላለመውረድ እየታገለ ይገኛል ?


ደረጄ:- ለጅማ ትልቅ አዲስ ነገር ፈጥሬያለሁ ፡፡አሁን ከተማ ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ ጅማ አባቡና የፈጠረው ነው፡፡ ጅማ ከተማ ከተመሠረተ 30ዓመቱ ነው፡፡ ጅማ አባቡናን ከተመሠረተ በ3ዓመቱ ነው ወደ ኘሪሜየር ሊጉ ያስገባነው፡፡ ከክለቡ አመራሮች ጋር መልካም ግንኙነት ነው ያለኝ፡፡ ጅማ አባቡና ባይወርድ መልካም ነው፡፡ የመወረድ ስጋት ውስጥ በመሆኑ እንደኔ እሚጨነቅ ያለ ሰው እሚኖር አይመስለኝም፤ ክለቡ ሲቆይ ነው ያንተም ስም አብሮ ሊቆይ እሚችለው፤ ከወረደ በኃላ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም ወይ ሊቀጥል ወይም  ሊፈርስ ይችላል ለራሴ ስም ስል ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ እንዲቆይ እፈልጋለሁ   ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

አሰልጣኝ ጳውሎስ (ማንጎ) ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ተሰናበቱ

አዲስ የተቀጠሩት እና ዛሬ ቡድኑን የመሩት አሰልጣኝ መሳይ በየነ ቡድኑን በአንድ ጨዋታ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ለሌብነት ምቹ ወደ መሆን የቀረበው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ?

ለወትሮ ሀሜት የማያጣው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ትኩረት ሊሰጠው ወደ ሚገባው ምዕራፍ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ሦስት ስመ ጥር አሰልጣኞች ሦስት ክለቦች ለማትረፍ በሀላፊነት ተረክበዋል

ላለመውረድ እየተጫወቱ የሚገኙ ሦስት የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በሦስት የሚታወቁ አሰልጣኞች ይመራሉ። በኢትዮጵያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግጋሞ ጨንቻ

የጋሞ ጨንቻው ወጣቱ አሰልጣኝ ማነው ?

ራሱ የመሠረተውን ክለብ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እያንደረደው የሚገኘው አሰልጣኝ። ከአመት አመት አዳዲስ...