መነሻ ገጽ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ “በዳኞች ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት እንቃወማለን፡ዳኞች ላነሱት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት አለበት፡ኘሪሚዬር ሊጉ ግን መቋረጥ የለበትም ክለቦች እና አቶ ጁነዲን ባሻ”
ኢትዮ-ኤሌክትሪክኢትዮጵያ ቡናወላይታ ድቻወልዋሎወልዲያዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ አንደኛ ሊግየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበርየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግደቡብ ፖሊስደደቢትጅማ አባቡናጅማ አባጅፋርፋሲል ከተማ

“በዳኞች ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት እንቃወማለን፡ዳኞች ላነሱት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት አለበት፡ኘሪሚዬር ሊጉ ግን መቋረጥ የለበትም ክለቦች እና አቶ ጁነዲን ባሻ”

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያና በተለይም በዳኞች ላይ እየደረሰ ባለው ድብደባ ዙሪያ ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ምክክር ሲያደርጉ በዳኞች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ተቀባይነት የሌለውና የምንቃወመው ነው፡ ዳኞች ላነሱት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት አለበት፡ኘሪሚዬር ሊጉ ግን መቋረጥ የለበትም በሚሉትና ሌሎች ጉዳዬች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በምክክሩም በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ለተነሱ ችግሮች ክለቦች እና ፌዴሬሽኑ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር የተደረገ ቢሆንም ትናንት የዳኞች እና ኮሚሽነሮች ማህበር ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በቀጣይ 3ሳምንታት የትኛውንም ጨዋታ ላለመዳኘት እና በቀጣይም ጨዋታውን ለመዳኘት ማህበሩ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ስላሉ የኘሪሚዬር ሊጉ መቋረጥ ክለቦች ከበጀትና ከሌሎችም ጉዳዬች አንፃር እንዳሳሰባቸው ገልፀው ማህበሩ ጉዳዩን በድጋሚ እንዲያየው ጠይቀዋል፡፡

ክለቦች ትኩረት ሰተው ካነሷቸውና የጋራ መግባባት የተደረሰባቸው ዋና ዋና ነጥቦች

✍በዳኞች ላይ የደረሰውን ድብደባ ኢ-ሰብዓዊ የሆነና በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑና እንደሚያወግዙት፡፡

✍ፌዴሬሽኑ የሚወስናቸው የቅጣት ውሳኔዎች አስተማሪ አለመሆናቸውና ቅጣቶች በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የሚሻሩበት ሁኔታ ፍትሀዊ አለመሆኑ፡፡

✍አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች አዘጋገብ በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴም ሆነ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ላይ ቀድመው ጫና እያሳደሩ መሆናቸው፡፡

✍የአማራና የትግራይ ክለቦች ሲገናኙ ፡ችግሩን በመሰረታዊነት ከመፍታት ይልቅ በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫዎቱ መደረጉ ትክክል አለመሆኑ

✍አንዳንድ ክለቦች ዳኛ የሚያስመድቡበትና የሚያስቀይሩበት አካሄድ ትክክል አለመሆኑ

✍ጥቂት ዳኞችና ኮሚሽነሮች የሙያቸውን ስነ ምግባር በመጣስ ጨዋታዎች በሁከት ተጠናቀው በሪፖርታቸው በሰላም ተጠናቋል በማለት ይልካሉ፡፡

✍የፌዴሬሽኑ አመራሮች ከአንድ በላይ በሆኑና በተለያዩ በውሳኔ ላይ በሚጣረሱ ስራዎች መወከላቸው አግባብ አለመሆኑ እና ሌሎችም በርካታ ነጥቦች ተነስተው ውይይቱ ሲቀጥል

ክለቦች የኘሪምየር ሊጉ ውድድር መቋረጥ የለበትም ብለው ላነሱት ሀሳብ ፡የዳኞችና ኮሚሽነሮች ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ “ትግል” ማህበሩ የኔ የግል ድርጅት አይደለም
ውሳኔው የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ነው፡፡ ነገር ግን ማህበሩ ጨለምተኛ አይደለም፡፡ስለዚህ ይህን መሻር እና ማፅደቅ ያለበት ጉባኤው ነው ሲሉ ምላሽ ሰተዋል፡፡

ክለቦች በበኩላቸው ጨዋታዎች የሚቋረጡ ከሆነ በዚህ አመት ሻምፒዬንም፡ ወራጂም ክለብ መኖር የለበትም ሁሉም ክለቦች የቀጣዩን ዓመት ውድድር መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ካልሆነ ግን ዳኞችን ከውጭ ሀገር እናስመጣለን እንጂ ውድድሩ አይቋረጥም፡፡ብዙ ወጭዎች አሉብን ውድድሮች ቀድመው ሊጠናቀቁ ይገባል በማለት ጠንከር ያለ ሀሳብ ሰንዝረዋል፡፡

በመጨረሻም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ በማጠቃለያ ንግግራቸው ውድድሮች መቋረጥ የለባቸውም፡ዳኞች ያነሷቸውን ጥያቄዎች የተወሰኑትን መልሰናል፡ያልተመለሱትን ጥያቄዎችም በሂደት ምላሽ የሚያገኙ ይሆናል፡፡በቀጣይም የዳኞችና ኮሚሽነሮች ማህበር ጋር ውይይት እናደርጋለን ከዚህ ባሻገር የፊታችን እሁድ ከፀጥታ አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ገልፀው፡፡
“ኢትዮጵያን እናክብር የራሳችንን ዜጋንም እናክብር» ብለው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...