የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር በዳኞች ላይ እየተከሰተ በመጣው የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል፡፡
በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች ማህበር በሴቶችና ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ፣በከፍተኛ ሊግ፣በአንደኛ ሊግ እና ሌሎች ማንኛውም ፌድሬሽኑ በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ጨዋታዎችን ላለመዳኘት መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ከሶስት ሳምንት በኋላ ወደ እግር ኳስ ዳኝነት ለመመለስም በርከት ያሉ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል በ2010 ዓ.ም በእግር ኳስ ጨዋታዎች በስፖርታዊ ጨዋነት የተጎዱ ዳኞች ካሳ እንዲከፈላቸው እና ለሚደርስባቸው ጉዳት የህይወት መድህን ኢንሹራንስ እንዲገባላቸው ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በክልል በሚደረጉ ውድድሮችም ለዳኞችና ታዛቢዎች የክልል ጸጥታ ሀይሎች ጥበቃ የሚያደርጉበትን መንገድ ፌድሬሽኑ እንዲፈጥርም ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም በክልል የሚካሄዱ የእግር ኳስ ውድድሮችን ለመዳኘት አውሮፕላን በሚያርፍባቸው ቦታዎች ላይ የአውሮፕላን መጓጓዣ እንዲመቻችላቸውና ሌሎች ተያያዥ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉላቸው ጠይቀዋል፡፡