መነሻ ገጽ ቁጥሮች “በሊጉ እስከመጨረሻ ተፎካካሪ ሆነን በመጨረስ ዋንጫ የማንሳት አቅም አለን” በሊጉ ከተቆጠሩ ጎሎች 150ኛዋን ግብ ያስቆጠረው ኢታሙናይ ኬይሙኒ
ቁጥሮችቃለመጠይቅዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“በሊጉ እስከመጨረሻ ተፎካካሪ ሆነን በመጨረስ ዋንጫ የማንሳት አቅም አለን” በሊጉ ከተቆጠሩ ጎሎች 150ኛዋን ግብ ያስቆጠረው ኢታሙናይ ኬይሙኒ

አጋራ
አጋራ

 

የ2012 ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከተጀመረ ጀምሮ በጠቅላላ 166 ግቦች ተቆጥረዋል። በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሊግ በመምጣት ድንቅ እንቅስካሴን ከሚያደርጉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው የቀድሞ የድሬዳዋው አጥቂ ናሚቢያዊው ኢታሙናይ ኬይሙኒ። ክለቡ ወልዋሎ በዘጠነኛ ሳምንት ባህርዳርን ሲገጥም 26ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ የሊጉ 150 ኛ ግብ ሆና ተመዝግባለች። እኛም 150 ኛዋን ግብ ያስቆጠረውን አጥቂ የሀትሪክ ስፖርቱ ሚሊዮን ኃይሌ አነጋግሮ ተከታዮን አዘጋጅቶልናል።

 

በመጀመሪያ የሊጉን 150ኛዋ ግብ ማስቆጠርህ ምን ተሰማህ ?

በጣም ጥሩ እና ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ። ምክንያቱም አጥቂ ስትሆን የግድ ግብ ማስቆጠር ይጠበቅብሀል። እኔ ደግሞ ግብ አስቆጥሪ የዚህ ታሪክ ተጋሪ መሆኔ በጣም ድስ ብሎኛል።

 

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንዴት አየህው?

ሊጉ በጣም ጥሩ ነው። ሆኖም ግን ጥራቱን ስንመለከት ትንሽ ዝቅ ያለ ነው። ፉክክሩ በጣም ከባድ ነው። በጣም የኳስ አፍቃሪን ደጋፊዎችም ያሉት ነው። ይህም ደግሞ የክለቦችን አቅም ከፍ ከማድረጉም በተጨማሪ ሊጉ እንዲያድግ አስተዋፅኦ አለው።

 

በሊጉ ጥሩ ከሚንቀሳቀሱ የውጭ የተጫዋቾች መካከል አንዱ አንተ ነህ እና በቀጣይ ከክለብህ ጋር ምን ታስባለህ?

እውነቴን ነው ምልህ እኔ አጥቂ ስለሆንኩኝ የወልዋሎን ደጋፊዎች ከኔ ብዙ ጎሎችን ይጠብቁ ይህን ለማድረግ ደግሞ ጠንክሬ እሰራለው። ለደጋፊዎች መናገር የምፈልገው ነገር ደግሞ በዚህ አመት በሊጉ እስከመጨረሻ ተፎካካሪ ሆነን በመጨረስ ዋንጫ የማንሳት አቅም አለን። ይህ እንዲሳካ ደግሞ ደጋፊያችን ከጎናችን ከሌለ ተጫዋች ብቻ ምንም ማድረግ ስለማይችል እስከመጨረሻ ደግፉን ነው እናስደስታቹሀለን ነው የምለው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...