ቅድመ ጨዋታ ዕይታ| ጅማ አባ ጅፋር ከ ድሬዳዋ ከተማ

 

በ14ኛ ሳምንት ሌላኛ ሌላኛው ጅማ አባ ጅፋር ወረጅ ቀጠና ውስጥ ሚገኘው ድሬዳዋ ከተማን የሚያስተናግደበት ተጠባቂ ጨዋታ እንደሚከተለው አይተነዋል።

ጅማዎች በሜዳቸው በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ከሜዳቸው ውጭ ከሚከተሉት ወደ መከላከል ያዘነበለ አቀራረብ ይልቅ በመጠኑ ኳስን ተቆጣጥረውለመጫወት ጥረት ያደርጋሉ። ቡድኑ ምንም እንኳ የተጠቀሰው አጨዋወትን መርጦ ቢጫወትም በአማካይ ክፍል ላይ ያለው የፈጣሪ አማካይ ችግር እና አጨዋወቱ በኤልያስ አሕመድ ላይ የተንጠለጠለ መሆኑ በርካታ የግብ ዕድሎች እንዳይፈጥር እክል ሆኖበታል። በተለይ የጋባዦቹ የቡድኑ ጠንካራ የመከላከል አደረጃጀት በዛሬው ጨዋታም በሙህዲን ሙሳ ላይ የተንጠለጠለው የግብ እድል ለመፍጠር እና ግብ ለማስቆጠር የሚጥረው የድሬዳዋ ከተማ የአጥቂ ክፍል ይፈተናል ተብሎ ይጠበቃል በማጥቃት እንቅስቃሴያቸው በብዙዓየሁ እንደሻው ላይ የተንጠለጠለው ጅማዎች ያለባችውንት ግብ የማግባት ድክመት ግን በዛሬው ጨዋታም ፈተና ሊሆንባቸው እንደሚችል ይገመታል።ተጋባዦቹ አሁንም ወደ ድል ለመመለስ እየተቸገሩ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ከጨዋታው ነጥብ ለማግኘት ጥንቃቄ የተሞላበት ማጥቃት እና ማጥቃት ብቸኛ ምርጫቸውን አድርገው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ደካማው የመከላከል አቅማቸው ባለፈው ሳምንትም በጎደሎ የተጫወተው ስሑል ሽረ ከሜዳቸው አንድ ነጥብ ይዞ እንዲሄድ ያስገደደደቻው ሲሆን በተለይም በዛሬው ጨዋታ ቡርቱካናማዎቹን ስጋት ይሆንባቸዋል ተብሎ ሲጠበቅ። እንደ ቡድን የሚያደርጉት ደካማ እንቅስቃሴ ዋጋ እንዳያስከፍላቸው ያስፈራል። በሀለቱም ቡድኖች በቅጣትም በጉዳት ከጅማ አባጅፋር በኩል ሰኢድ ሀብታሙን በግል ጉዳይ አብርሀም ታምራትን በቅጣት ሲያጡ በድሬዳዋ በኩል ረመዳን ናስር እና ያሬድ ታደስ በጉዳት እሚያጡ ይሆናል።

የእርስ በእርስ ግንኙነት

ከዚህ ቀደም አራት ግዜ ሲገናኙ ቡርቱካናማዎቹ ሁለት ጨዋታ ሲረቱ ጅማዎች አንድ ግዜ አሸንፋል። በቀሪው አቻ ተለያይተዋል። ይህ ጨዋታ ዛሬ 9:00 ሲል በኢንተርናሽናል አርቢት በላይ ታደሰ እየተመራ ይከናወናል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor