ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በኛ ሀገር የድል አጥቢያ ኮከቦች ብቅ ማለታቸው የተለመደ ነው ከሰሞኑ ደግሞ በእግር ኳሳችን ውስጥ ይህ ክስተት ታይቷል ኮትዲቯርን የረታው የዋሊያዎቹ የቀድሞ አለቃ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ተረስቶ በኮትዲቯር በተሸነፈው ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ያለ ምክንያት የተጓዙት የልኡካን ቡድን አባላት እርስ በርስ ሲሽላለሙ ኢንስትራክተር አብርሃምን በፕሮግራሙ ላይ እንዲገኝ አልፈቀዱም….. ኢንስትራክተር አብርሃም ግን አልሞቀው አልበረደው ከሃትሪክ ጋር ቆይታ ያደረገው አሰልጣኙ “ግለሰቦች እውቅና ቢነፍጉኝም ውለታ አዋቂው የስፖርት ቤተሰቡና ህዝቡ ቀድሞ ስለሸለመኝና እውቅና ስለሰጠኝ እጅ እነሳለሁ” በማለት አመስግኗል። በርካታ ጉዳዮችን ያነሳው አሰልጣኝ አብርሃም ለግብ አስቆጣሪዎች ባለሪከርድ አቡበከር ናስርና ለፋሲል ዋንጫ የአምበሳውን ሚና ለተወጣው ሙጂብ ቃሲም ያለውን አድናቆት ገልጾ የፋሲል ከነማውን አምበል ያሬድ ባዬን” ከጥሩ ስነምግባር ጋር ምርጥ ተጨዋችና አምበል ነው” ሲል አሞግሶታል። ” ከፋሲል ከተማ ውጪ ደመወዝ የሚከፍሉና የማይከፍሉ ሁሉም እኩል ሲፎካከሩ ማየቴ ገርሞኛል” ያለው ኢንስትራክተር አብርሃም “ከ12 ክለቦች በበለጠ ፈተናዎቻችንና ኮቪድ ጠንካራ ተጋጣሚዎቻችን ነበሩም” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል

*… ሻምፒዮኖቹ ፋሲሎች የመጀመሪያ የሆነውን ዋንጫ ቅዳሜ ያነሳሉ….የቡድኑ አባላት ስለ አንጸባራቂ ድላቸውና ገድላቸው የሚሉት ነገር አለ….

*….እሁድ 9 ሰአት ለኮንፌዴሬሽን ካፕ ተሳትፎ የተፋጠጡት ኢትዮዽያ ቡናና ሀድያ ሆሳእና ይፋለማሉ…..የኢትዮዽያ ቡናው ሃይሌ ገ/ተንሳይ “በኮንፌዴሬሽን ካፕ የመካፈል ታሪክ ለመስራትና ሀድያ ሆሳእናን ለመርታት ተዘጋጅተናል” ሲል የሀድያ ሆሳእናው አምበል ሄኖክ አርፍጮ በበኩሉ” እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁሉ ኢትዮዽያ ቡናን በመርታት ከደጋፊዎቻችን ጋር እንጨፍራለን” ሲል ፎክሯል። ማን ይሳካለት ይሆን?

….በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*……የዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ የፊታችን ረቡእ በፖላንድ ይካሄዳል ከማን.ዩናይትድና ከቪያሪያል ማን ድሉ ይቀናው ይሆን? በፍጻሜው ጨዋታ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዘገባ አዘጋጅተናል …

*……የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እሁድ ይጠናቀቃል ውጤታማ ጊዜ ያላሳለፈው አርሰናል በኢምሬትስ ብራይተንን በሚያስተናግድበት ጨዋታ የአመቱን የሊግ ፉክክር ይፈጽማል… በጉዳት የሚፈልገውን ያህል ያልተጫወተውና በቅርቡ አገግሞ ወደ ሜዳ የተመለሰው ወጣቱ ማርቴኔሊ “በደጋፊዎቻችን ፊት
ለመጫወት ጓጉቻለሁ” ሲል ተናግሯል።

*… ቸልሲና ማን.ሲቲ የፊታችን ቅዳሜ የሻምፒየንስ ሊግ የዋንጫ ጨዋታቸውን በፖርቶው ስታድየም ስታድዮ ድራጋዎ ያካሂዳሉ….የቸልሲው ተከላካይ ሩዲገር “ለሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ማለፋችን ኩራት ቢሰማኝም ትልቁ ህልሜ ዋንጫውን ማንሳት ነው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

https://www.Hatricksport.net

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team