ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን “ሞውሪንሆ የተሰኘው ቅጽል ስሙ ከመዝገብ ስሙ በላይ መለያው የሆነው የሰበታ ከተማው አዲሱ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው እንግዳችን ነው ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ የነበረው አሰልጣኙ …ስለ ዋሊያዎቹ ምን አስተያየት አለህ ሲባል ይለፈኝ ብሏል….አሰልጣኝ ዘላለም ስለ ምድቡ ግን የሚሰማውን ተንፍሷል.. “በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ጠንክሮ መስራትና መጸለይ የግድ ነው” ብሏል። ሞውሪንሆ “ስራ ላይ አሰሪ ከስራ ውጪ ደግሞ ለተጨዋቾቼ ወንድም ነኝ” ሲልም ተናግሯል።

*….ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ መራሹ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኦሎምፒክ ኮሚቴው ላይ የመልሶ ማጥቃት ሰንዝሯል….”ለዶክተር አሸብር አትሌቲክሱ ከረቤታቸው ለኛ ደግሞ ሳንባችን ነው” ስትል ኮማንደር ደራርቱ የሰላ ሂስ ሰንዝራለች። አብረዋት ከነበሩት ስስራ አስፈጻሚዎች መሃል አንዱ የሆኑት ዶክተር በዛብህ ወልዴ በበኩላቸው “ዶክተር አሸብር ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድኑ ለኦሎምፒክ ቢያልፍ ተጨዋቾቹን ሊመርጡልን ነበር? ” ሲሉም ይተቻሉ..በስካይ ላይት ሆቴል የተሰጠውን መግለጫ ዮሴፍ ከፈለኝ አዘጋጅቶታል።

*…የዋሊያዎቹ ሁለተኛ አምበል አስቻለሁ ታመነ ከመሸሻ ወልዴ ጋር በነበረው ቆይታ “በአፍሪካ ዋንጫው ዝቅተኛ ግምት ቢሰጠንም ወደ ውድድሩ ስፍራ የምናመራው አንድ ደረጃ ከፍ ለማለትና ክስተት ለመሆን ነው” ሲል ተናግሯል።

*…የድሬዳዋ ከተማው ሱራፌል ጌታቸው
“በአዲሱ ዓመት ክለቤን ጠቅሜና ጥሩ ብቃቴን አሳይቼ ለብሄራዊ ቡድን ን መመረጥ እፈልጋለሁ” ሲል ከመሸሻ ወልዴ ጋር በነበረው ቃለ ምልልስ ላይ ተናግሯል።

*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*…. “ለመድፈኞቹ ዳግም ተስፋ ስለጫረው ጋቦናዊው የግብ አዳኝ ፔሬ ኤምሬክ ኦባሚያንግ የሚገልጽ ዘገባ ይዘናል…..

*….. የማን.ዩናይትዱ ሜሰን ግሪንውድ ክርስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል ሜሲን አወዳድሯል “ሮናልዶና ድንቅና ታታሪ ተጨዋች ነው የማደንቀው ግን ሜሲን ነው” ሲልም ይናገራል….

*…..ጂዮርጂንሆ የጣሊያኑና የቸልሲው የመሃል ሜዳ ኮከብ የአውሮፓ የአመቱ ኮከብ ተብሎ ተመርጧል.. በዚህ ዙሪያ ዘገባ ይዘናል…

*…”በሊቨርፑል የራሴን የሆነ ታሪክ እየጻፍኩ መቀጠል እፈልጋለሁ” ሲል የሊቨርፑሉ አንዲ ሮበርትሰን በክለቡ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።

*… በዘንድሮ የአውሮፓ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ 32 ክለቦች በ8 ምድብ ተደልድለው መስከረም ላይ ፍልሚያቸውን ይጀምራሉ… ታላላቅ ክለቦችን በአንድ ምድብ የሚያፋጥጠው የምድብ ድልድልን የሚመለከት ዘገባ ይዘናል…

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team