መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

አጋራ
አጋራ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን “የምን ሜሲ ሜሲ የምን ቶሬስ ቶሬስ እኛም ሀገር አለ ዳዊት እስጢፋኖስ” የተባለለት አዲሱ የጅማ አባጅፋር ፈራሚ እንግዳችን ነው። ሳይፈራ ሳይሳሳ ድፍረት የተሞላበት ምላሽ ሰጥቷል…”እኔን የሚመርጥ አሰልጣኝ ሀሳብ ያለው ብቻ ነው” የሚለው ዳዊት ” ብሄራዊ ቡድን ያሰለጠኑትን አሰልጣኞች ጨምሮ ከካሳዬ አራጌና አሸናፊ በቀለ ውጪ ሀሳብ አላቸው ማለት አልችልም” ሲል ይናገራል። ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዊት እንደሚለው “ብሄራዊ ቡድን ለመመረጥም ስሜን ቀይሬ እመጣ ይሆናል”ሲልም አስተያየቱን ሰጥቷል።

*….ከበርካታ አመታት በኋላ ከሞቀ አቀባበል ይልቅ የሞቀ ቅሬታና የስድብ ውርጅብኝ የደረሰበት የኦሎምፒክ ቡድኑ አዲስ አበባ ገብቷል…ስለደበዘዘው አቀባበልና ዶክተር አሸብር ላይ ስለወረደው የተቃውሞ ውርጅብኝ የሚገልጸውን የይስሀቅ በላይን ዘገባንም ይዘናል…

*… ከአመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮዽያ ቡናን የተሰናበተውና ወደ ሀድያ ሆሳዕና ያቀናው ኢያሱ ታምሩ ከመሸሻ ወልዴ ጋር በነበረው ቆይታ “ከኢትዮዽያ ቡና መለየት ስሜቱ ከባድ ነው” ሲል የሚሰማውን ተንፍሷል።

*… በቅዱስ ጊዮርጊስ አራት አመት ቆይታ ዋንጫ ሳያነሳ ለፋሲል ከነማ የፈረመው አብዱልከሪም መሀመድ/ተርሚኔተር/ ከመሸሻ ወልዴ ጋር በነበረው ቆይታ
” ወደ ፋሲል ከነማ ያመራሁት እስካሁን ያላሳካሁትን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ፍለጋ ነው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*…. “ራሴን ለአዲስ ፈተና አዘጋጅቻለሁ”
ስላለውና ወደ ፒ ኤስ ጂ ሳይታሰብ ስላቀናው የንጉሱ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ድንገተኛ ዝውውር የሚገልጽ ዘገባ ይዘናል…..

*….. “በመጨረሻም ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ” ባለውና ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ዳግም በተመለሰው ሮሜሉ ሉካኩ ዝውውርም ዙሪያ የተዘጋጀ መረጃንም ይዘናል…..

*…… የማን.ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ደሂያ በዩናይትድ ቤት 10ኛ አመቱን ይዟል ግብ ጠባቂው የሰጠውን ቃለ ምልልስንም አካተናል….

*….የአርሰናሉ አለቃ ሚካኤል አርቴታ ከትላንት ምሽቱ የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ በፊት ስላስፈረማቸው ተጨዋቾች የሰጠውን ቃለምልልስን ይዘናል…..

*…. የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ትላንት ምሽት ተጀምሯል… ስለ ውድድር ዘመኑ እውነታዎች የሚዳስስ መረጃንም አካተናል…

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...