ለኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ለማለፍ ሀዋሳ ላይ እየተካሄደ የነበረውየኢትዮጵያ ሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በአዲስ አበባው አራዳ ክ/ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በፍፃሜ ጨዋታ የተገናኙት አራዳ ክ/ከተማ እና ሱሉልታ ከተማ በፉክክር የተሞላ ጨዋታ አከናውነዋል ።በተደጋጋሚ ወደ ጎል በመድረስ የደጋፊውን ቀልብ የገዛው ጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች ጎል ለማስቆጠር ሲቸገሩ ተመልክተናል ።
ጨዋታው ሊጠናቀቅ አራት ተጨማሪ ደቂቃውን አራተኛ ዳኛዋ ካሳየች በኋላ አራዳዎች ጎል በማስቆጠር አንድ ለባዶ አሸንፈው የውድድሩን ዋንጫው የግላቸው አድርገዋል።ሱሉልታ ከተማ ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።
ከፍፃሜው ጨዋታ በፊት ለደረጃ በተደረገ ጨዋታ የሎዛ አበራ የትውልድ አካባቢ የሆነው ከንባታ ጠንባሮ ዞን ሀላባ ከተማን ከመመራት ተነስተው ሁለት ለአንድ አሸንፈዋል።ከንባታ ጠንባሮ በውድድሩ አስደናቂ አቋማቸውን በማሳየት በብዙዎች ተወድሰዋል ።
- ማሰታውቂያ -
የውድድሩ ኮከብ አሰልኝ ከአራዳ ክ/ከተማ አሰልጣኝ ዘሪሁን ታዬ ሲመረጥ ኮከብ ተጫዋች አሁንም ከአራዳ ሀና በሀይሉ ተመርጣለች ።በውድድሩ ሶስት ግቦችን ብቻ በማስተናገድ ኮከብ ግብ ጠባቂ የሆነችው ሀዳስ ዝናቡ በመሆን ተመርጣለች ።የውድድሩ ኮከብ ጎል አግቢ ከሱሉልታ ከተማ አስር ቁጥር ለባሿ ማርታ በስምንት ጎል አሸንፋለች።