ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን

*…. ኮከቧ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለሲፋን ሀሰን በሰጠችው ፈጣን የመልሶ ማጥቃት ያልተደሰተ የለም ይስሃቅ በላይ “የሁለት ሪከርድ ባለቤቷ ለተሰንበት ግደይ ማንጸባረቋን ቀጥላለች” በሚል አሞግሷታል።

*…..የባህርዳር ከተማው ፍጹም አለሙ ባህርዳር ከተማ 2ኛ ሆኖ ያላጠናቀቀበትን ምክንያት ለሀትሪክ የገለጸ ሲሆን ” ሁሉን ክለቦች እኩል ማየት ባለመቻላችን ጎድቶናል ውጤትም ቀይሮብናል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል…

*…. ደረቅ ቼኩን ባስመቱት 15 ተጨዋቾች
ምክንያት የሀድያ ሆሳዕና የንግድ ባንክ አካውንት ታግዷል…

*….አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውና ወላይታ ድቻ
ተፋጠዋል….የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድሙ ሳሙኤል “የሚዲያ ባለቤቶች ገንዘብ ስለሚከፈላቸው ለአሰልጣኙ ወግነዋል…. ባጣ ቆየን ባለመሆናችን ደግሞ አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማርያምን አነጋግረነዋል” ሲሉ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው/ ሞሪንሆ/በበኩሉ ” ስራ አስኪያጁ አሁን የተቀጠረ ነው ስለምንም ነገር አያውቅም ” በማለት የተፈጠረውን ችግር ለሀትሪክ አስረድቷል።

*…. የወላይታ ድቻው በረከት ወልዴ “ሻምፒዮን ለመሆን እንደ ፋሲል ከነማ ለሁሉም ክለቦች እኩል ግምት ልንሰጥ ይገባል” ሲል ተናግሯል።

*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

ትኩረታችን በአውሮፓ ዋንጫው
ላይ አድርገናል…

ስለ ተጠባቂ ሀገራትና
ወቅተዊ ጥንካሬያቸው
ሙሉ ዘገባ ይዘናል

*….. ” ፈረንሳይ ትልቋ ተቀናቃኛችን ናት”ሲል
አዲስ መጽሀፉን ያስመረቀው የማን.ዩናይትድ ኮከብ ማርከስ ራሽፎርድ ተናግሯል….

*…. “የአውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮን መሆንን
እያለምኩ ነው” ሲል የፈረንሳይ ብሄራዊ
ቡድን አጥቂ ካሪም ቤንዛማ ህልሙን
ተናግሯል…

*…. የአውሮፓ ዋንጫ የምንጊዜውም ምርጡ ተጨዋች ስለሆነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዶሻንቶሽ አቪየሮ የተዘጋጀም ጽሁፍ አዘጋጅተናል…

*…. “ሪያል ማድሪድ በዋንጫ ያሸበረቀ ታሪክ ያለው ክለብ ነው”ሲሉ በድጋሚ ለማሰልጠን ወደ ሳንቲያጎ በርናባው የተመለሱት አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ክለቡን አሞግሰዋል….

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *