መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ “ዛሬ ያገኘሁት ሽልማት ቀላል አይደለም፤ ለቡናም ምን ሰርቼለት ነው የተሸለምኩትም እንድል አስብሎኛልና ከቡና ጋር ሻምፒዮና ሆኜ ነው መጨረስ የምፈልገው” አቡበከር ናስር
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

“ዛሬ ያገኘሁት ሽልማት ቀላል አይደለም፤ ለቡናም ምን ሰርቼለት ነው የተሸለምኩትም እንድል አስብሎኛልና ከቡና ጋር ሻምፒዮና ሆኜ ነው መጨረስ የምፈልገው” አቡበከር ናስር

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች የሆነው አቡበከር ናስር ዛሬ ምሽት በነበረው የስካይ ላይት ሆቴል የሽልማት አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ የክለቡ አጋርና ስፖንሰር በሆነው ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር አማካኝነት የተዘጋጀውን የዓመቱን የክለቡን የኮከብ ተጨዋችነት ሽልማት በማሸነፍ ሊወስድ ችሏል።

የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር ይህን የዋንጫና የ1.4 ሚሊዮን ብር ግምት ያላትን የ2021 አዲስ ሞዴል ሱዙኪ መኪና ሽልማትን በማሸነፍ በአንደኝነት በመመረጥ ሊያገኝ የቻለው ከእሱ ጋር በእጩነት ቀርበው የነበሩትን የቡድኑ አጋሮቹን ታፈሰ ሰለሞንን እና አስራት ቱንጆን በመብለጥም ነው።

የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በኮከብ ተጨዋችነት ተመርጦ የመኪና ቁልፉን ከተረከበ በኋላም በሽልማቱ ዙሪያ ስለተሰማው ሁኔታም ተጠይቆም የሚከተሉትን ምላሾች ሰጥቷል።

“በዛሬው ምሽት ፕሮግራም የዓመቱ የክለቡ ኮከብ ተጨዋች ተብዬ በመሸለሜ ምስጋና ለፈጣሪዬ ይግባና በጣም ደስ ብሎኛል፤ የሸለመኝን አካልም አመሰግናለው። ይህን ሽልማት እንዳገኝ ጥረቱ የእኔ ብቻ አይደለም። የአሰልጣኛችን የአሰልጣኞቻችን ስታፍና የተጨዋቾቻችንም እገዛ ጭምር ነው። ለእኔ የዘንድሮ የውድድር አመት የተለየ ነው ደጋፊውንና የቦርድ አመራሮቹንም አመሰግናለው፤ በተለይ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ሁሌም በየጨዋታው ያበረታታኛል። ለእሱም ምስጋና አለኝ።

በዛሬው ፕሮግራም ላይ የእኔ መሸለም በታዳጊ በሴቶች እና በወጣት ደረጃ የተሸለሙ ተጨዋቾችም አሉና ለእነሱ አርአያቸው እሆናለውም ካለ በኋላ ስለ ሽልማቱ አክሎም ሲገልፅ “ይሄ የዛሬው ሽልማት ቀላል አይደለም። ለቡና ምን ሰራውም እስክልም ድረስ ነው የደረስኩትና ቡድኑን ለሻምፒዮናነት አብቅቼም ነው በቡድኑ ቆይታዬ መጨረስ የምፈልገው” ብሏል።

– አቡበከር ናስር በዕለቱ ከተናገራቸው ውስጥ የግብ ጠባቂያቸው አሰልጣኝን ፀጋዘሀብ አስግዶምን ጠቅሶ እሱ ከዚህ በፊት በነበረባቸው የኢትዮ ኤሌክትሪክና የደደቢት ቡድን ቆይታው ዮርዳኖስ አባይና ጌታነህ ከበደ የግብ ሪከርድን በሰበሩበት ወቅት አብሮ የስኳዱ አባል ነበረና አሁን ደግሞ ቡና ከመጣ በኋላ በተለይ ዘንድሮ ይህን ሪከርድ እንድሰብር ብዙ ነገር ነግሮኛል። ከእሱ ውጪ ፊዚዮቴራፒስታችን ይስሃቅ ሽፈራውና ወደ ቡና በ2009 ከሚኪያስ ጋር ስገባም እነ መስዑድ መሐመድ፣ ኤፍሬም ወንድወሰን፣ ጋቶች ፓኖምና ኤልያስ ማሞና እያሱ ታምሩ ያደረጉልኝን ነገርም የማልረሳው ነው ከልብም አመሰግናቸዋለው ካለ በኋላ በአሁን ሰዓት በቡድኑ ውስጥ ስለሚገኘው እያሱ ታምሩም ይህን ብሏል። “እያሱ በቡና ቡድን ውስጥ ዘንድሮ ብዙም አልተጫወተም። ቡድኑ ግን ሻምፒዮና እንዲሆን ይፈልጋል። ለቡና ያለው ፍቅር የሚገርም ነው። ቡናን ብወድም እኔ ያለኝ ፍቅር የእሱን ያህል ነው ማለት አልችልም። በአጠቃላይ እዩን እንደወንድሜ ያህል ነው የማየው” ብሎ ንግግሩን ሲያጠቃልል በሆቴሉ የታደሙት የቡድኑ ደጋፊዎች አቡበከርን መኪና መሸለሙን ተንተርሰው ፒ!ፒ!ፒ!ፒ!ፒ እያሉ ሲያወድሱት እያሱን ደግሞ “እያሱ ታምሩ ዘላለም ማማሩ” ብለው በማወደስ ምስጋናቸውንና አድናቆታቸውን ገልፀውለታል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...