ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን ሀዋሳ ከተማን ጥሩ ደረጃ ይዞ እንዲጨርስ ያደረገውን አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን እንግዳችን አድርገነዋል….” በሙያዬ ላይ ጣልቃ የሚገባ ካለ ለመቀበል እቸገራለሁ ጣልቃ አልገባም ማንም ጣልቃ እንዲገባብኝም አልፈቅድም”ሲል ቆፍጠን ያለ አስተያየቱን ሰጥቷል…

*….የዋንጫ ባለድሉ ፋሲል ከነማ የመሃል ሜዳ ማገሩ ሀብታሙ ተከስተ ጓደኛዬ ነው ስለሚለው አቡበከር ናስር ይናገራል
” የአቡበከር አስደናቂ አቋም አስደንግጦኛል ኮከብነቱን ቢያገኝ አልከፋም” ሲል አቋሙን አሳውቋል። ሀብታሙ ከሀትሪክ ጋር በነበረው ቆይታ ለበርካታ ጉዳዮች ምላሹን ሰጥቷል።

*…. “ከቅርብ አመታት ወዲህ በኳስ እንቅስቃሴም ይሁን በውጤት ምርጡንና የተሻለውን ኢትዮጵያ ቡናን እየተመለከትን ነው” የሚለው የኢትዮጵያ ቡናው ሚኪያስ መኮንን “በአፍሪካ የውድድር መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ማየት ከወዲሁ አጓጉቶኛል” ሲልም አስተያየቱን ሰጥቷል…..

*… በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በፕሪሚየር ሊግ ካምፓኒው መሃል ልዩነት የተፈጠረ ይመስላል…የሊግ ኩባንያው ስለ ክለቦች መውረድና መውጣት ስለትግራይ ክለቦች ጉዳይ የመወሰን መብት የለውም ይሄ የስራ አስፈጻሚው መብት ነው የሚለው የፌዴሬሽኑ መግለጫ እሁድ በካፒታል ሆቴል ከሚሰበሰቡት የሊግ ካምፓኒው ጠቅላላ ጉባኤ አባላት የሚሰጠውን ምላሽ አጓጊ አድርጎታል።

*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*….. የአውሮፓ መድረክ ንግስናን ለመቀዳጀት ነገ ምሽት 4 ሰአት የፔፕ ጋርዲዮላና ቶማስ ቱሄል ጦሮች በስታዲዮ ድራጋዎ ስለሚያደርጉት ሰላማዊ ጦርነት ያዘጋጀነው ዘገባ አለ….

*…. ፖላንድ ላይ ማን.ዩናይትድን አሸንፎ ብቸኛ አሰልጤኝ የመሆን ታሪክ ስለሰሩት ስፔናዊው የሮፓ ሊጉ ንጉስ ኡናይ ኤምሬ የምንላችሁ አለ….

*…. የተገኙ የግብ እድሎችን አምክኖ የዩናይትድ ሽንፈት ምክንያት የተደረገው የማን.ዩናይትዱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ “በዩሮፓ ሊጉ ሽንፈት ተስፋ አንቆርጥም” ሲል ይናገራል…..

*…..አርሰናል የአውሮፓ መድረክ ተሳታፊ አለመሆኑን ተከትሎ አሰልጣኙ ሚካኤል አርቴታ ክፉኛ ተከፍቷል….

*…..”በፕሪሚየር ሊጉ ሌስተር ሲቲ ላይ የሰራሁትን ሀትሪክ መቼም አልረሳውም” ሲል አድናቂዎቹ በክህሎቱ የሚደመሙበት የቀድሞ የሆላንድና አርሰናል ህያው ዴኒስ ቤርካምፕ ይናገራል….

*…..ወደ ባርሴሎና ያቀናው የመሃል ሜዳው ታጋይ ዋይናልደም “ህይወቴን ሙሉ የሊቨርፑል ደጋፊ ሆኜ እኖራለሁ” ሲል በአንፊልድ ከቀዮቹ ጋር የሰራውን ታሪክ እንደማይረሳው ተናግሯል…

*…ወደ ኦልድትራፎርድ አንድ ትልቅ ዋንጫ በ10 ቀን ውስጥ እናመጣለን ማለቱ ያልተሳካለት የማን.ዩናይትዱ አለቃ ኦሊጉናር ሶልሻየር ” ከውድቀታችን ልንማር ይገባል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team