በቀጣዩ የውድድር ዘመን ቅድመ ዝግጅት (pre-season ) ብቁ እንዲያደርግ የሚረዳው ስልጠና ተሰጠ

የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዛሬ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች እንደሚጠናቀቁ የሚታወቅ ነው ።

ተጫዋቾች በቀጣይ ለበርካታ ቀናት ወይም ወራት ከሜዳ መራቃቸውን ተከትሎ በቀጣይ ውድድር ዓመት በአካልና በአእምሮ ብቃቱ ረገድ አቋማቸውን ጠብቀው እንዲመለሱና የሚረዳ ፕሮግራም መሰናዳቱን ሀትሪክ ስፖርት ለማወቅ ችላለች ።

ማረፊያቸውን ሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ያደረጉት ሰበታ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ፈር ቀዳጆቹ ክለብ ሲሆኑ በ ኢንስትራክተር አብርሀም መብርሀቱ እና
የኢትዮጵያ ቡና ዋና አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ጋር በጋራ በመሆን ዕሮብ ዕለት ተጫዋቾች ለ ሁለት ሰአታት የፈጀ ትምህርትና ገለፃ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል ።

ተጫዋቾች off-Seson (እረፍት ግዜ )
ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና በቀጣዩ የውድድር ዘመን ቅድመ ዝጎጅት (pre-season )ሲመለሱ
ለውድድር ብቁ እንዲያደርግ የሚረዳው ይህ ንድፈ ሀሳብ በቀጣይ ተጫዋቾች በ ቤታቸው በመሆን በቀጥታ የዙም ቪድዮ ትምህርት ለመስጠት መታሰብም ታውቋል ።

ከትምህርቱም በኋላ የሁለቱ ቡድን አንበሎች እና ተጫዋቾች እንደተናገሩት የሰበታው ከተማ አንበል መሱድ መሀመድ ይህ ትምሀርት በጣሞ ብዙ እውቀት እንዳገኘበት ተናግራል ።

በመቀጠልም የኢትዮጵያ ቡናው ተጨዋችና የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ኮኮብ ጎል አስቆጣሪው አቡበከር ናስር ከዚህ ትምህርት ብዙ እንደተማረና በትምህርቱ ላይ ላሉት ጋደኞቹ ይህንን ትምህርት ተግባራዊ ካደረግን የተሻለ ተጫዋቾች እንሆናለን በማለት በትምህርቱም ጥሩ እውቀት እንዳገኘ ተናግራል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor