በክረምቱ ዝውውር መስኮት ስድስት ተጨዋቾችን ማስፈረም የቻለው በዳንኤል ጸሃየ ሚመራው ሽረ እንዳስላሰ የመስመር ተከላካዩን ዓብዱሰላም ኣማንን ኣስፈርሟል።ተፈጥሮኣዊ የመስመር ተከላካይ እጥረት የነበራቸው ሽሬዎች የቀድሞው የወልዋሎ ዓድግራት ዩኒቨርሲቲ፣ኢትዮጵያ ቡና፣ደደቢት ና ወሎ ኮምቦልቻ ተጨዋች የሆነው ዓብዱሰላም ኣማንን ማስፈረማቸው ችግሩን ሊቀርፍላቸው እንደሚችል ይገመታል።
ለአንድ ወር ያክል በመቐለ ከተማ ቅድመ ዝግጅታቸውን በማድረግ በትግራይ ዋንጫ የተሳተፋት ሽሬዎች ከሰኞ ጥቅምት 12 ወደ ሽረ እንዳስላሰ በማቅናት ዝግጅታቸውን በማድረግ ይገኛሉ።
አስተያየት ይስጡ