መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ ሰበታ ከተማ የኦሮሚያ ሲቲ ካፕ ዋንጫን አነሳ
ሰበታ ከተማኦሮሚያ ዋንጫ

ሰበታ ከተማ የኦሮሚያ ሲቲ ካፕ ዋንጫን አነሳ

አጋራ
አጋራ

በአራት ክለቦች መካከል ከ ጥቅምት 12 አስከ 19 ድረስ የተካሄደው የኦሮሚያ ዋንጫ በሰበታ ከተማ አሸናፊነት ተፈፅሟል፡፡ 

በቅድሚያ በ7ሰዓት ላይ የተገናኙት ለደረጃ የሚጫወቱት  ለገጣፎ ከተማ ከ ኢት.መድህን ሲገናኙ በሙሉ የጨዋታ ሰዓት 90 ደቂቃ ያለምንም ግብ 0-0 በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን  ሲያጠናቀቁ፡፡ የሶስተኛነቱን ደረጃ ለመለየት  ወደ መለያ ፍፁም ቅጣት ምት በማምራት  ለገጣፎ ከተማ 4-2 በሆነ ውጤት ኢትዮጵያ መድህንን  ማሸነፍ  ችሏል፡፡ 
በመቀጠል 9ሰዓት ላይ ለዋንጫ ፍልሚያቸውን ያደረጉት አዘጋጁ ሰበታ ከተማ ከ ጅማ አባቡና  ሲሆኑ በጥሩ የጨዋታ የበላይነት   ሰበታ ከተማ 3-1 በሆነ ውጤት ጅማ አባቡናን መርታት ችልዋል፡፡

 በውድድሩ  ጥሩ ብቃቱን እያሳየ በሚገኘው የአጥቂ መስመር ተጨዋቾች  አብይ ቡልቲ በ8ኛ እና በ36ኛ ደቂቃዎች ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ከረፍት መልስ ቀሪዋን ጎል በ48ኛ ደቂቃ ላይ ኤፍሬም ቀሬ በፍፁም ቅጣት ምት 3ኛ ግል ለሰበታ ከተማ ማስቆጠር ችሏል፡፡ በአሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሐንስ እሚመራው ጅማ አባቡናን በዜሮ ከመሸነፍ ያዳነቸውን ጎል በ75ኛ ደቂቃ ላይ ሐይደረ ሸረፋ አስቆጥሮ ጨዋታው በሰበታ ከተማ 3-1 አሸነፊነት ተጠናቋል፡፡ ሰበታ ከተማ እግር ኳስ ቡድንም ለአንድ ሳምንት የተካሄደውን የኦሮሚያ ዋንጫን በበላይነት ማንሳት ችሏል፡፡

*የውድድሩ ኮከብ ተጫዋቾች አብይ ቡልቲ 

*በኦሮሚያ ሲቲ ካፕ ዋንጫ የተወዳደሩት ክለቦች በደረጃ ሲቀመጡ

1.ሰበታ ከተማ (የዋንጫ አሸናፊ)

2.ጅማ አባቡና

3.ለገጣፎ ከተማ 

4.ኢትዮጵያ መድህን 

በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

*አሰልጣኝ ስዮም ከበደም  የመጀመሪያ ዋንጫቸውን ከአዲሱ ቡድናቸው ሰበታ ከተማ  ጋር ማንሳት ችለዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሰበታ ከተማባህርዳር ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከተማ እና ሰበታ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪማየር ሊግ 29ኛው ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሶስተኛ መርሀግብር ላለመውረድ...