በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ጨዋታ አዲስአበባ ከተማ ሰበታ ከተማን 4ለ3 በሆነ ዉጤት አሸንፏል።
አስቀድሞ ለበርካታ ወራት በወራጅ ቀጠናዉ ላይ ይገኙ የነበሩት ሁለቱ ክለቦች ከዉጤት ማጣት ባሻገርም ከደሞዝ ጋር በተገናኘ በተጫዋቾች እና አመራሮች መካከል በተመሳሳይ ለወራት ያክል በንትርክ ዉስጥ መሰንበታቸው ይታወሳል። በዚህም በሜዳና እና ከሜዳ ዉጭ እንቅስቃሴ ጥሩ ያልከረሙት ሰበታ ከተማዎች በዛሬዉ ዕለት ከሊጉ መዉረዳቸዉን ያረጋገጡበትን ዉጤት አስመዝግበዋል።
በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ ምንም እንኳን ከሰበታ ከተማዎች በይበልጥ ሲንቀሳቀሱ የተስተዋሉት እና ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርጉ የነበሩት አዲስአበባ ከተማዎች ብልጫቸው ፍሬ አፍርቶ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ በተቃራኒው በ16ኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ለማስተናገድ ተገደዋል። በዚሁ ደቂቃ ላይ ከግራ መስመር በኩል ፍፁም ገ/ማርያም ያሻገረዉን ኳስ አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ግብ በማስቆጠር ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

ምንም እንኳን ጥሩ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አዲስአበባ ከተማዎች አስቀድሞ ግብ ቢቆጠርባቸዉም ከአምስት ደቂቃዎች በኋላ አቻ መሆን ችለዋል። የአዲስአበባ ከተማዉ የመስመር አጥቂ ፍፁም ጥላሁን የሰበታ ከተማ ተከላካዮችን አለመናበብ ተከትሎ የቸገኘዉን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን አቻ አድርጓል።
ከመጀመሪያው አጋማሽ የዉሀ ዕረፍት መልስ ደግሞ በ28ኛዉ ደቂቃ ላይ አዲስአበባ ከተማዎች በቶሎ ግብ ማስቆጠር ችለዋል። የቀኝ መስመር ተከላካዩ እንዳለ ከበደ ያሻማዉን ኳስ ፍፁም አለሙ በግንባሩ በመግጨት ለራሱም ለክለቡም ሁለተኛ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ከዚች ግብ መቆጠር በኋላ በእንቅስቃሴ እና በሙከራ ረገድ ምንም እንኳኝፈን የአዲስአበባ ከተማዎችን የበላይነት ብንመለከትም በተቃራኒው ግን ሰበታ ከተማዎች በ42ኛዉ ደቂቃ ላይ ለግብ የቀረበ አደገኛ ሙከራ ማድረግ ችለዉ ነበር። ከቀኝ መስመር ተከላካዩ ሃይለሚካኤል አደፍርስ የተሻገረዉን ኳስ ዱሬሳ ሹቤሳ በግንባሩ በመግጨት ቢሞክርም በግብ ጠባቂው ዳንኤል ተሾመ አማካኝነት ከሽፋለች።
ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ ግን አዲስአበባ ከተማዎች መሪነታቸውን ወደ ሶስት ከፍ ያደረጉበትን ግብ አስቆጥረዋል። በዚሁ ደቂቃ ላይ በድጋሚ ፍፁም ጥላሁን የሞከረዉን ኳስ ግብ ጠባቂዉ ሳይቆጣጠረዉ በመቅረቱ ምክንያት አጥቂዉ ሪችሞንድ አዶንጎ ኳሷን ወደ ግብነት ቀይሮ የመጀመሪያው አጋማሽ በአዲስአበባ ከተማ 3ለ1 መሪነት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ችሏል።
ከዕረፍት መልስ ሰበታ ከተማዎች ምንም እንኳን የተጫዋቾችን ለዉጥ አድርገዉ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርጉም በተቃራኒው በ53ኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ተቆጥሮባቸዋል።
ሙሉቀን አዲሱ ከመስመር በኩል ያሻገረውን ኳስ ሪችሞንድ አዶንጎ አስቆጥሮ አዲስአበባ ከተማ መሪነቱን ወደ 4ለ1 ከፍ ማድረግ ችሎ ነበር።

በተደጋጋሚ በሜዳዉ የመሐል ክፍል ላይ ያመዘነ የጨዋታ ሂደትን ባስመለከተን የሁለቱ ቡድኖች እንቅስቃሴ በ67ኛዉ ደቂቃ ላይ ሌላ ግብን ሰበታ ከተማዎች አስመልክተዉናል። ከቀኝ መስመር በኩል ከጌቱ ሀይለማርያም የተሻገረውን ኳስ ፍፁም ገ/ማርያም አስቆጥሮ ክለቡን ወደ ጨዋታው ለመመለስ ሞክሯል።
በዚህ ሂደት በቀጠለዉ የሀለቱ ክለቦች ጨዋታ ወደ መገባደጃዉ ሲቃረብ ግን በ88ኛዉ ደቂቃ ላይ ሰበታ ከተማዎችን ይበልጥኑ ወደ ጨዋታው መመለስ የምትችል ግብ ሳሙኤል ሳሊሶ ከርቀት አክሮሮ በመምታት ግብ ማስቆጠር ቻለ። ከዚች ግብ በኋላም የዕለቱ ጨዋታ በአዲስአበባ ከተማ 4ለ3 በሆነ ዉጤት ሰበታ ከተማን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠናዉ ፈቀቅ ያሉበትን ዉጤት አስመዝግበዋል።

አስተያየት ይስጡ