መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ደቡብ ፖሊስ  በሜዳው ጅማ አባቡናን  በመርታት ደረጃውን ማሻሻል ችሏል፡፡
ሪፖርትየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግደቡብ ፖሊስጅማ አባቡና

ሪፖርት | ደቡብ ፖሊስ  በሜዳው ጅማ አባቡናን  በመርታት ደረጃውን ማሻሻል ችሏል፡፡

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 6ኛ ሳምንት በምድብ- ለ እሚገኙትን  ደቡብ ፖሊስ  ከ ጅማ አባቡና አገናኝቶ ባለሜዳዎቹ ደቡብ ፖሊሶች 2ለ1በሆነ ውጤት ማሽነፍ ችለዋል፡፡

በጨዋታው  ወደ ግብ በመድረሱ እና ለግብ የቀረበ ሙከራ በማድጉ ረገድ የተሻሉ የነበሩት ባለ ሜዳዎቹ ደቡብ ፖሊሶች ሲሆኑ በ9ኛው ደቂቃ ሚካኤል ለማ የመታውኳስ በግቡ አናት ላይ  ወጣለች፡፡

በ25ኛው ደቂቃ በጨዎታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው በሓይሉ ወገኔ ከግራ መስመር ያሻማውን ኳስ የጅማ አባ ቡናው ተከላካይ በሓይሉ በለጠ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሮ ባለ ሜዳዎቹን መሪ አድርጓቸዋል፡፡ ከግቧ መቆጠር በሗላ ባለሜዳዎቹ ጫና ፈጥረው ተጫውተዋል፡፡ በ31ኛው ደቂቃ የጅማ አባቡናው የፊት መስመር ተጫዋች ቴድሮስ ታደሠ ከበረኛ ጋር አንድ ለ አንድ ተገናኝቶ  ከሳተ በሗላ በመልሶ ማጥቃት  ብርሐኑ ያሻማለትን በሐይሉ ወገኔ በጭንቅላት አስቆጥሮ ደቡብ ፖሊሶች 2ለ0 መምራት ችለዋል፡፡

በ35ኛው ደቂቃ ቴድሮስ ታደሰ የመታው ኳስ የደቡብ ፖሊሱ ግብ ጠባቂ ሲያድንበት፡፡ በ39ኛው ደቂቃ ላይ በግራ መስመር ሚካኤል ለማ ላይ የተሰራውን ጥፋት በሓይሉ  ወገኔ የመታውን  አበባው በጭንቅላት የገጨውን ኳስ ግብ  ጠባቂው በቀላሉ አድኖበታል፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ  የዳኛው  ፊሽካ በሚጠበቅበት ሰዓት ጅማ አባ ቡናዎች 16.50 ውጪ ያገኙትን ቅጣት ምት ኃይደር ሸረፋ የመታውን የደቡብ ፖሊሱ ግብ ጠባቂ   ሐብቴ ከድር ተፍቶ መልሶ ይዟታል፡፡
በዚው ውጤት የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቋል፡፡

በሁለተኛ አጋማሽ ኳስ በመቆጣጠሩ ተሽለው ወደ ሜዳ የገቡት ጅማ አባ ቡናዎች ሲሆኑ በሱራፌል አወል እና ቴድሮስ ታደሰ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም ግብ ማስቆጠር አልቻሉም፡፡በ60ኛው ደቂቃ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ  ግብ መድረስ የቻሉት ጅማ አባ ቡናዎች  ቡዛየው እዳሻው ያገኘውን ግልፅ  የማግባት ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

በ81ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ክልል ውስጥ የደቡብ ፖሊሱ ደስታ ጋቻሞ ጥፍት በመስራቱ የተሰጠውን ፍ.ቅ.ም  ሀይደር ሙስጠፋ  አስቆጥሮ  ጨዋታው  2ለ1 ሆኗል፡፡
በ84ኛው ደቂቃ ብርሃኑ ከቀኝ መስመር የሻማውን ካስ ብሩክ ኤሊያስ በጭንቅላት የመታት ኳስ ግብ ጠባቂው በቀላሉ አድኗታል፡፡ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ሐይል  የተቀላቀለበት ጨዋታን ያሳዩት ሁለቱ ቡድኖች  በ86 ኛው ደቂቃ ላይ የደቡብ ፖሊሱ አምበል ቢኒያም አድማሱ በጉዳት ወጦ ፀጋ ጎሳዬ ወደ ሜዳ

ገብቷል፡፡በተደጋጋሚ የደቡብ ፖሊስ ተጫዋቾች ጥፋት ተሰርቶብናል በማለት ሲወድቁ ጅማ አባቡናዎች ሰዓት ለመግደል ነው በማለት  ውዝግብ ተፈጥሮ ለጥቂት ደቂቃ ጨዋታው ተቋርጦም ነበር፡፡ ጨዋታዉም በባለሜዳዎቹ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ደቡብ ፖሊስ በ7 ነጥብ በ4 የግብ ክፍያ 2ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ችሏል፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

ግርማ ታደሰ – ደቡብ ፖሊስ

“ጨዋታው ከባድ እንደ ሚሆን ጠብቀን ነበር፡፡ ጅማ አባቡና ከፕሪሜየር ሊጉ ወርዶ እንደ መምጣቱ ጠንካራ ነገር እንደ ሚገጥመን አውቀን ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ተዘጋጅተን ነው የመጣነው በመጀመሪያው አጋማሽ ተጭነን ተጫውተናል በሁለተኛው አጋማሽ ጅማ አባቡና የተሻሉ ነበሩ፡፡ ያገኛናቸውን የግብ አጋጣሚዎች ተጠቅመን ወጠናል፡፡”

የጅማአባቡና አሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሐንስ ድህረ ጨዋታ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

አሰልጣኝ ጳውሎስ (ማንጎ) ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ተሰናበቱ

አዲስ የተቀጠሩት እና ዛሬ ቡድኑን የመሩት አሰልጣኝ መሳይ በየነ ቡድኑን በአንድ ጨዋታ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ለሌብነት ምቹ ወደ መሆን የቀረበው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ?

ለወትሮ ሀሜት የማያጣው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ትኩረት ሊሰጠው ወደ ሚገባው ምዕራፍ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ሦስት ስመ ጥር አሰልጣኞች ሦስት ክለቦች ለማትረፍ በሀላፊነት ተረክበዋል

ላለመውረድ እየተጫወቱ የሚገኙ ሦስት የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በሦስት የሚታወቁ አሰልጣኞች ይመራሉ። በኢትዮጵያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግጋሞ ጨንቻ

የጋሞ ጨንቻው ወጣቱ አሰልጣኝ ማነው ?

ራሱ የመሠረተውን ክለብ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እያንደረደው የሚገኘው አሰልጣኝ። ከአመት አመት አዳዲስ...