መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ወልዋሎ አዲግራት.ዮ ኢትዮጵያ ቡናን በመርታት ሊጉን መምራት ጀመረ
ሪፖርትኢትዮጵያ ቡናወልዋሎ

ሪፖርት | ወልዋሎ አዲግራት.ዮ ኢትዮጵያ ቡናን በመርታት ሊጉን መምራት ጀመረ

አጋራ
አጋራ

  በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ 5ኛ ሳምንት  በወልዋሎ አዲግራት  ስታድየም  የተደረገ  ጨዋታ ልክ  9:08 ደቂቃ ላይ  ጨዋታው  ከመጀመሩ  በፊት  በሁለቱ ክለቦች  አርማና ባንዲራ የተዋቡ የሁለቱ የወዳጅ ክለቦች ደጋፊዎች ወልዋሎ  ሜዳ  ሞልተውት  ነበር፡፡የሁለቱ ክለቦች የደጋፊዎች አመራር ስጦታ በመለዋወጥ ነበር የተጀመረው

ጨዋታው  ሲጀመር  በወልዋሎ  በኩል 4-3-3 አሰላለፍ  በቡናዎቹ  በኩል   4-4-2  የሆነ  አሰላለፍ  ይዘው የገቡ  ሲሆን ወልዋሎዎቹ   ከመጀመርያዋ  ፊሽካ መነፋት  ጀምረው ተጭነውና  ኳስን  በፍጥነት  በመጫወታቸው  ከእረፍት በፊት  ከቡናዎች በተሻለ   ቶሎ ቶሎ  ወደ  ግብ  መድረስ ችለዋል፡፡  በዚሁ  በ 3ኛ ደቂቃ  ከድር ሳልህ  ከበረኛ ጋ ተገናቶ ሳይጠቀምበት የቀረው    አጋጣሚ ለቢጫዎቹ እሚያስቆጭ ነበር፡፡ 
 ደጋፊያቸው ድጋፍ ታጅበው የሜዳ አድቫንቴጅ ለመጠቀም  ሲራራጡ  የዋሉትሩ  ወልዋሎዎች    በ5ኛ ደቂቃ  ፕሪንስ  ሰብሪ  ያደረጉት  ሙከራ  በቡናው ግብ ጠባቂ ሀሪስተን  ለጥቂት ተጨርፎ    ወደ  ማአዝን  ያወጣት  ኳስ  ደጋፊውን  ከመቀመጫው  ቁጭ ብድግ  ያስደረገች ነበረች፡፡ በድጋሚ  በክንፍ  በኩል ከድር ሳሊህ በረኛውን አልፎ  ወደ  ውጭ   የመታት   ኳስ  ልጁ  ቀድሞ  ክለቡን ጎል አስቆጥሮ መሪ ለማድረግ ጉጉቱን የምታሳይ  ነበረች፡፡

  ወልዋሎዎች   ከእረፍት በፊት በተሻለ ወደ ጎል በመድረስ ጥሩ ነበሩ በተቃራኒው  በኢትዮጵያ ቡናዎቹ  ከእረፍት  በፊት የሄነው  የሚባል    አሰደንጋጭ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም ፡፡ ይልቁንም በሁለት አጋጣሚዎች  ከጨዋታ ውጭ  አፍሳይድ  ሲወጡ  ሁለት ቀለል ያሉ ኳሶችንም የግብ ሙከራ ማድረግ ችለዋል፡፡ በቡናዎቹ  በኩል በመጀመሪያው አጋማሽ  ግብ  ጠባቅያቸው ሀሪሰተን ሄሱ የነበረው  ኮንፊደንስና  አንድ ለአንድ ተገናኝቶ  ኳስ የማዳን ችሎታው   ከእረፍት በፊት ቡናዎቹ  ግብ  እንዳያስተናጉዱ  የበኩልን ድርሻ አበርክቷል፡፡

በሁለተኛው  አጋማሽ  በአንፃራዊነት  ቡናዎች  በተሻለ  እንቅስቃሴ  በማድረግና  ወደ  ጨዋታ  ለመመለስ  ሙከራ  በማድረግ   ከወልዋሎዎች  ተሽለው ሲቀርቡ    በተለይ የመሀል ክፍል ተጫዋቻቸው  እያሱ  ታምሩ  እንቅስቃሴ    ድንቅ ነበር፡፡ በ51ኛ ደቂቃ ላይ  የሃሪሰተን  መውጣት  ተጠቅሞ  ያገኛትን ኳስ ሙሉአለም  ጥላሁን ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡ 
በ56ኛ ደቂቃ ላይ ከመአዝን  የተመታችውን  ኳስ   ሳሙኤል  ሳኑሚ በጭንቅላቱ የገጨው   አደገኛ  እና  ለግብ ቅርብ የሆኑበት ኳስ  በረከት አማረን ተክቶ የገባው የወልዋሎው  ግብ  ጠባቂ   ዘውድ መስፍን    አድኖታል፡፡

  መሀል ክፍል ላይ ወደ ጨዋታ የተመለሱት ወልዋሎዎች  በ65 ደቂቃ  ላይ አፍወርቅ  ሃይሉ የመታውን  ጠንካራ ኳስ  በቡናው ተከላካይ ተጨርፎ ገባ ሲባል  በእለቱ  ጥሩ የነበረ  የቡናው  ግብ  ጠባቂ ሃሪሰን ሄሱ  ወደ  መኣዝን  ሊያወጣት ችሏል፡፡  

በ 68ኛ ደቂቃ  ላይ ወልዋሎዎቹ  ዋለልኝ ገብሬን በብርሃኑ  አሻሞ ቀይረው ሲያስገቡ ከቅያሪው በኃላ  የሄን  የሚባል  ሙከራ ማድረግ አልቻሉም፡፡ 

በ73ኛ ደቂቃ ላይ ኤልያስ ማሞ አክርሮ  የመታው   ኳስ ለጥቂት  ወደ ውጭ  ከመውጣቱ  በቀር  በማሃል ሜዳ ላይ  ያመዘነ  እና  ሃይል የተቀላቀለበት  የሚመስል   ጨዋታ  ነበር፡፡ ከዚህች ሙከራ ከ6ደቂቃዎች በኃላ ከድር ሳልህ ከመስመር ሰብሮ በመግባት  ወደ  ግብ  የመታው ኳስ  ሙሉአለም  ጥላሁን  ጨርፎ ወደ  ግብነት የቀየራት ኳስ    የጨዋታው  ብቸኛ ግብ ሆና ልትቆጠር ችላለች፡፡  ከዚች  ግብ መቆጠር  በኃላ የተነሳሱት ቢጫዎቹ ወልዋሎዎች ሲሆኑ  በአንፃሩ መደናገጥ ውስጥ የገቡት ቡናዎች አማኑኤል ዮሀንስን በአብዱልባሲጥ ከማል ያስገቡ  ቢሆኑም በጨዋታው ለውጥ ለማምጣትም ሆነ ውጤቱን ለመቀየር አልቻሉም፡፡

በአንፃሩ ወልዋሎዎች ያገኟትን የአንድ  ግብ ልዩነት ለማስጠበቅና ውጤት  ይዞ ለመውጣት ሰአት ሲያባክኑ ተስተውለዋል፡፡ በዚሁ ጨዋታው በወልዋሎ አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡ ወልዋሎ አዲግራትም ሊጉን በ9 ነጥብ መምራት ጀምሯል፡፡

  የአሰልጣኞች አስተያየት 

አሰልጣኝ ብርሀኔ ገብረግዚአብሔር ~የወልዋሎ አዲግራት  አሰልጣኝ

”ጨዋታው በጣም ጥሩ ነበር። ጨዋታውን ከነሱ በተሻለ ተቆጣጥረነው ነበር። በተለይም በ መጀመርያው ኣጋማሽ ብዙ የ ጎል አጋጣሚዎች መፍጠር ችለን መጠቀም አልቻልንም፡፡ ውጤቱ ይገባናል። በዚሁ  ከቀጠልን ለሻምፒዮንነት  የማንጫወትበት ምክንያት የለም። ”

 የኢትዮጵያ ቡና ም/አሰልጣኝ ~ሀብተወልድ ደስታ

“በሁለታችን በኩል  ለ ደጋፊዎቻችን  ኳስ ጨዋታ ለማሳየት  ሞክረናል  በሁለታችን በኩል  ጥሩ ተጫውተናል  የኛ  ቡድን ከግዜ  ወደግዜ  እየተሻለ  እየመጣ ነው፡፡  ለማሸነፍ  የተቻለንን ነገር  ብናደርግም    ያገኙትን አጋጣሚ የተጠቀሙት  ወልዋሎዎች  አሸንፈውናል፡፡   ያው  ውጤቱ  ቢያስከፋኝም በሁለቱም በኩል ባየናቸው ደጋፊዎች ደስተኛ  ነኝ፡፡ በልጆቹ  እንቅስቃሴም  ደስተኛ ነኝ  በቀጣይ  ከዚህ በላይ  አሻሽለንና መሪነቱን  እንይዛለን፡፡”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ወልዋሎ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ አራተኛውን የአጋማሹን አዲስ ፈራሚ በእጃቸው አስገብተዋል። በአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ...

ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

ኢትዮጲያ ቡና ካለበት የፋይናንስ ቀዉስ ለማዉጣት ከቡናዉ ሴክተር የሚገኘዉ ገንዘብ መጨመር አለበት...

ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ቡናን ከምስረታው አንስቶ በተለያዩ ሀላፊነት ከአርባ አመት በላይ መርተው...