መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ ሪፖርት | አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
ሀዋሳ ከተማሪፖርትአዳማ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

አጋራ
አጋራ

በመቐለ 2-0 ከተረቱበት ጨዋታ ጃኮፔንዜ ሱሌማን መሀመድ አዲስ ህንፃ እና የኋላሸት ፈቃዱን በማስወጣት ደረጀ አለሙ ወናፍ አወል ስሌማን ሳንጋሪ እና በላይ አባይነህን ተክተው ወደ ሜዳ የገቡት አዳማ ከተማዎች በሀዋሳ ከተማ ተከላካዮች ተፈትነው ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል። ገና ከጅምሩ በፈጣን ማጥቃት እንቅስቃሴ የእንግዳዎቹን የግብ ክልል መጎብኘት የጀመሩት አዳማዎች በ3ኛው ደቂቃ በበረከት ደስታ የሚያስቆጭ ሙከራ ማድረግ ችለው ነበር።

የሳሳ የሚመስለውን የሀዋሳ የመሀል ሜዳ ብልጫ ወስደው መንቀሳቀስ የቻሉት አዳማዎች ከነዓን ማርክነህ ለዳዋ ሁጤሳ ከመዓዘን በኩል ወደ ግብ አቅጣጫ ያሻገረለትን ኳስ ለማግኘት በፍጥነት ሲሮጥ ከበረኛው ጋር በፈጠረው ግጭት በ17ኛው ደቂቃ በቡልቻ ሹራ ተቀይሮ ወጥቷል። የመሀል ሜዳ እና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾች ችግር ለመፍታት የቤት ስራ ያለባቸው የሚመስሉት ሀዋሳ ከተማዎች ከቅዱስ ጊዮርጊስ 0-0 ከተለያዩበት አሰላላለፍ ወንድማገኝ አዘዘን እና መስፍን ታፈሰን አስወጥተው ወንድማገኝ ማእረግ እና ብርሀኑ በቀለን ይዘው ወደ ሜዳ የገቡት ሲሆን በዛሬው ጨዋታ መከላከልን መሰረት አድርገው ሲጫወቱ በብዛት ወደ ራሳቸው ሜዳ አፈግፍገው መጫወታቸው የአዳማ ከተማ አጥቂዎችን ጎል እንዳያስቆጥሩ ማምከን ተሳክቶላቸዋል። 29ኛው ደቂቃ ላይ ከዳዋ ሁቴሳ ጋር ግጭት ፈጥሮ የነበረው ግብ ጠባቂው ቢሊጋኖ በጉዳት በሀብቴ ተቀይሮ ወጥቷል። በተለይ በዛሬው ጨዋታ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ላውረንስ ላርቴ የአዳማዎችን በብዙ ጎል የማሸነፍ ህልም አምክኗል።

የመጀመሪያው አጋማሽ የአዳማዎችን የተከላካይ ስፍራ ያልፈተነ ዳንኤል ደርቤ ኢላማውን ያልጠበቀ ሙከራ ነበሩ። መደበኛው ሰአት ተጠናቆ አምስት ያህል ደቂቃ ተጨምሮ የእለቱ ዋና ዳኛ እያሱ ፈንቴ በሀዋሳዎች የግብ ክልል ኳስ በእጅ በመነካቱ ፍፁም ቅጣት ምት ሰጥተው በረከት ደስታ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቆ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

ከእረፍት መልስ አዳማዎች በጎሏ በመነቃቃት በእንግዳው ቡድን ሜዳ ላይ ተጭነው ቢጫወቱም ጎል ማስቆጠር ችግር ታይቶባቸዋል። ለአብነት በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ከነዓን ማርክነህ ከመሀል ሜዳ የተሻገረ ኳስ ቀጥታ ወደጎል ቢመታውም በረኛው አምክኖበታል። እስከ 74ኛው ደቂቃ ድረስ ሲመሩ የቆዩት ሀዋሳዎች በአዳማ የግብ ክልል ኳስ በእጅ በመነካቷ የእለቱ ዳኛ ፍፁም ቅጣት ምት ሰጥተው ሄኖክ ድልቢ ፍፁም ቅጣት ምቷን አስቆጥሮ 1-1 በሆነ ውጤት ጨዋታው ሲቀጥል ሄኖክን ቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው እስራኤል እሸቱ የበረኛውን መውጣት ተከትሎ ወደጎል የሞከራት ኳስ ተጠቃሽ ሙከራ ነበረች።

አዳማዎች አሸናፊ የሚያደርጋቸውን ጎል ፍለጋ በተደጋጋሚ የሀዋሳዎችን ደጅ ቢጠኑም ተጨማሪ ግብ ማግኘት ሳይችሉ ጨዋታውን 1-1 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...