መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ ደደቢት በሰፊ ግብ በማሸነፍ የሊጉ መሪ መሆን ችሏል።
ሪፖርትሲዳማ ቡናደደቢት

ሪፖርት | በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ ደደቢት በሰፊ ግብ በማሸነፍ የሊጉ መሪ መሆን ችሏል።

አጋራ
አጋራ

10:05 ሲል በአዲስ አበባ በተደረገው የደደቢት እና የሲዳማ ቡና ጨዋታ በደደቢት 5-2 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል። ለደደቢት ጎሎቹን ወጣቱ ድንቅ አጥቂ አቤል ያለው 3 ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሲሰራ ደስታ ዳሙ እና ኤፍሬም አሻሞ ቀሪዎቹን ሁለት ግቦች አስቆጥረዋል። ለሲዳማ ቡና አዲስ ግደይ እና መሐመድ አብዱልለጢፍ ከሽንፈት ያላዳነውን ግቦች ማስቆጠር ችለዋል።
በሁለቱም ቡድኖች በኩል ጥሩ እንቀቅስቃሴ በታየበት በዚህ ጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ለማድረስ ጥረት ማድረግ ችለዋል።

16ኛው ደቂቃ ላይ የደደቢቱ የአብስራ ተስፋዬ ከጌታነህ ከበደ የተቀበለውን ኳስ ሞክሮት በግቡ አናት ላይ ወጥቷል። 21ኛው ደቂቃ ላይ የደደቢቱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጪ የሞከረውን ኳስ የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ፍቅሩ ወዴሳ በግሩም ሁኔታ አውጥቶበታል። ከ1 ደቂቃ በኋላ የደደቢት ተከላካዮችን ስህተት ተጠቅሞ ያገኘውን ኳስ አጥቂው አዲስ ግደይ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሮ ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር። ከዚህ  ግብ መቆጠር በኋላ ሲዳማ ቡና ሙሉ ለሙሉ ጨዋታውን በልጦ መንቀሳቀስ ሲችል ያገኟቸውን አጋጣሚዎች መጠቀም ባለመቻላቸው ተጨማሪ ግብ ማግባት ሳይችሉ ቀርተዋል።

30ኛው ደቂቃ ላይ ኩሊቫሊ ከድር ከግራ በኩል ያሻገረለትን ኳስ ሽመክት ጉግሳ በግንባር ሞክሮት ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል። ከ2 ደቂቃዎች በኋላ ሽመክት ጉግሳ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተገኘውን ቅጣት ምት ጌታነህ ከበደ በቀጥታ ሞክሮት በግቡ አናት ላይ ወጥቷል። በጥንቃቄ በመጫወት በመልሶ ማጥቃት መጫወት የመረጡት ሲዳማ ቡናዎች 43ኛው ደቂቃ ላይ የሲዳማ ቡናው አብይ በየነ የሞከረውን ኳስ የደደቢቱ ግብ ጠባቂ በድንቅ ሁኔታ አውጥቶበታል። የመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታ መጠናቀቂያ ላይ የዳኛው ፊሽካ በሚጠበቅበት ሰዓት ድንቁ አጥቂ አቤል ያለው ግሩም ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን አቻ አድርጎ ወደ መልበሻ ቤት መግባት ችለዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ሙሉ በሙሉ ብልጫ መውሰድ የቻሉት ደደቢቶች ሁለተኛውን ግብ ለማስቆጠር 10 ደቂቃዎች ብቻ ፈጅቶባቸዋል። 55ኛው ደቂቃ ላይ የደደቢቱ ተከላካይ ደስታ ደሙ በግንባሩ ገጭቶ ያስቆጠረው ኳስ ደደቢትን መሪ ማድረግ ችሏል። በተደጋጋሚ ወደ ሲዳማ ቡና የግብ ክልል መድረስ የቻሉት ደደቢቶች ከ4 ደቂቃዎች በኋላ አቤል ያለው ለራሱ ሁለተኛውን ለቡድኑ ሶስተኛውን ግብ ማስቆጠር ችሏል። 61ኛው ደቂቃ ላይ የደደቢቱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጪ የሞከረውን ኳስ የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ፍቅሩ ወዴሳ በግሩም ሁኔታ አውጥቶበታል። በሁለተኛው አጋማሽ እጅግ ተዳክመው የቀረቡት ሲዳማ ቡናዎች ሶስተኛው ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላ ለመነቃቃት ባደረጉት ጥረት 61ኛው ደቂቃ ላይ የደደቢቱ ተከላካይ ስዩም ተስፋዬ የሰራውን ስህተት ተጠቅሞ መሐመድ አብዱልለጢፍ ግብ በማስቆጠር ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት አድርገው ነበር። 73ኛው ደቂቃ ላይ የሲዳማ ቡናው ሀብታሙ ገዛኸኝ የሞከረው ድንቅ ኳስ በግቡ አናት ላይ ወደ ውጭ ወጥቷል። ከዚህ ሙከራ 1ደቂቃ በኋላ የደደቢቱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከበረኛው ጋር ብቻ ለብቻ ተገናኝቶ በረኛው ያወጣበት ኳስ እጅግ የሚያስቆጭ ነበር። 83ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ኤፍሬም አሻሞ ከጌታነህ ከበደ የተሻገረለትን ኳስ አስቆጥሮ በ2 የግብ ልዩነት መምራቱን አስተብቋል። መደበኛ የጨዋታ ጊዜው ሊጠናቀቅ 1ደቂቃ  ሲቀረው በጨዋታው ድንቅ የነበረው ወጣቱ አቤል ያለው ለቡድኑ 5ኛ ግብ አስቆጥሮ ደደቢትን አሸናፊ ማድረግ ችሏል።

ጨዋታው 5-2 መጠናቀቁን ተከትሎ ደደቢት በ13 ነጥቦች ሊጉን መምራት ሲጀምር ሲዳማ ቡና በአንፃሩ 5ነጥቦችን ብቻ ሰብስቦ 15ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በጨዋታው ሀትሪክ መስራት የቻለው የደደቢቱ አቤል ያለው ለኢትዮጵያ ኳስ ተስፋ እንደሆነ ያሳየበትን ጨዋታ አሳይቷል። የኳስ አጠቃቀሙ የአዕምሮም ሆነ የሰውነት ፍጥነቱ እጅግ የሚያስገርም ነበር። አቤል ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ከ hatricksport.com ድረገጽ ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ “ከብሔራዊ ቡድን መልስ ባደረኩት የመጀመሪያ ጨዋታ ሀትሪክ በመስራቴ በጣም ደስ ብሎኛል። ከእግዚአብሔር ጋር ከዚህ በኋላ ጠንክሬ በመስራት ክለቤን እና ሀገሬን ለመጥቀም እፈልጋለሁ።” በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኀላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የደደቢት አሰልጣኝ ~ንጉሴ ደስታ 

“በመጀመሪያ ጨዋታዎች ላይ የነበረብንን ግብ የማግባት ችግር እየቀረፍን መምጣት ችለናል። ከጨዋታ ጨዋታ የተሻሉ ነገሮች እየፈጠርን ነው እና አጥቂዎቻችን ጥሩ ብቃት ነው እያሳዩ ያሉት ሊጉ መቆራረጥ ከሌለው ከዚህ የተሻለ ምርጥ ብቃታችንን በማሳየት ለዋንጫው እንፎካከራለን።” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የሲዳማ ቡናው አሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ

 “አምና ከነበረው ቡድን ብዙ ልጆች ስለለቀቁብን ዘንድሮ አዲስ ቡድን ነው እየሰራን ያለነው። በተጨማሪ እያየናቸው ያሉት ካርዶች ዋጋ እያስከፈሉን ነው። የመጀመሪያው ጎል የባከነ ሰዓት ላይ ስለተቆጠረብን ልጆቼ ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል። የደደቢት አጥቂዎች ውጤታማ ነበሩ። ያገኙአቸውን አጋጣሚዎች በአግባቡ በመጠቀማቸው ሊያሸንፉን ችለዋል።” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የግብ ዘብ ከዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ውጪ ሆኗል። በትላንትናው...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና የግብ ዘብ ከማንኛውም እግር ኳስ ታግዷል። በዩጋንዳ ፕሪምየር ሊግ...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

አማካዩ ቀሪ ውል እየቀረው ሲዳማ ቡናን ለቋል። ሁለት ወሳኝ ዝውውሮችን የፈፀመው የአሰልጣኝ...