በደጋፊዎች ውብ ህብረ ዝማሬ የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሜዳው እና በደጋፊዎቹ ፊት በሊጉ ያለመሸነፍ ጉዞዎን ለማስቀጠል እንዲሁም ድሬድዋ ከተማ ከሽንፈት ለማገገም ያደረጉት ጨዋታ ነበር ::
ከጨዋታው ጅማሮ በፊት የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሰርጆቪች ሚቾ በስታዲየም ሲገኙ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ::
ጨዋታው እንደተጀመረ ፈጣን ምላሽ የሰጡት ፈረሰኞቹ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ከቀኝ መስመር ጋዲሳ ያሻማውን ካስ ጌታነህ ከበደ ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል ::
ከጎሉ መቆጠር በሃላ ጫና ፈጥረው መጫወት የቀጠሉት ፈረሰኞቹ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርጉም ወደ ግብነት መቀየር ሳይችሉ ቀርዋል ::
ድሬድዋ ከተማዋች በኤልያስ ማሞ የመሀል ክፍሉን ብልጫ መውሰድ ቢያስቡም በመልሶ ማጥቃት መጫወት ምርጫቸውን አድርገዋል ::
ሙከራዎችን ማድረግ የተሳናቸው ድሬዳዎች በአንድ አጋጣሚ በቅጣት ምት ሞክረው ባህሩ ነጋሽ ካደነባቸው ሙከራ ውጪ አስደንጋጭ ሙከራ ሲያደርጉ አልተስተዋለም ::
በመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ ሳላህዲን ሰኢድ ባጋጠመው ጉዳት ሳቢያ ከሜዳ ተቀይሮ ሊወጣ ችሏል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ሳልሀዲንን በጉዳት ያጡት ፈረሰኞቹ አቤል እንዳለን ቀይረው በማስገባት የሁለተኛውን አጋማሽ ጀምረዋል ::
በሁለተኛው አጋማሽ ጅማሮ ላይ ተጭነው የተጫወቱት ጊዮርጊሶች በእለቱ ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያደርጉ ባመሹት ጌታነህ ከበደ እና ጋዲሴ መብራቴ በደቂቃዎች ልዩነት አከታትለው ባስቆጠራቸው ጎሎች የጎሉን መጠን ከፍ ማድረግ ችለዋል ::
ከጎል መቆጠር በሃላ ካስን በመያዝ አፈግፍገው የተጫወቱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ለድሬድዋ ከተማ ምቹ ሆኖ ተስተውላል ::
ድሬድዋዎች ከሶስተኛው ጎል መቆጠር በሃላ ወደ ጨዋታው የተመለሱበትን ጎል በድሬድዋ በኩል ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴን ሲያደርግ የቆየው ሪችሞንድ ኦዶንግ ባስቆጠራት ግብ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት አድርገዋል ::
ለፈረሰኞቹ አሳሳቢ እየሆነ በመጣው የጉዳት ዜና በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ሌላኛው አጥቂያቸው ጌትነህ ከበደ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከሜዳ ሊወጣ ችሏል።

ከጎሉ መቆጠር በሃላ ጫናዎችን ለመፍጠር የሞከሩት ድሬድዋዎች በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ሲደርሱ ተስተውላል ::
በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ የተዘናጉ የሚመስሉት ፈረሰኞች በጭማሪ አራት ደቂቃዎች ላይ ጎል አስተናግደዋል ::
ድሬድዋዎች ከሽንፈት ያልታደገች ጎል በሙህዲን ሙሳ አማካኝነት አስቆጥረዋል ::

ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ በደረጃው ሰንጠርዥ አራተኛ ሲቀመጡ በጨዋታው ሽንፈት ያስተናገዱት ድሬድዋዎች በወራጅ ቀጠናው ውስጥ ለመቆየት ተገደዋል ::
አስተያየት ይስጡ