በትግራይ ኢንተርናሽናል ስታድየም የተካሄደው የመቐለ 70 እንደርታን የሲዳማ ቡና ጨዋታ በባለሜዳዎቹ መቐለ 70 እንደርታ 3ለ1 እሸናፊነት ተጠናቋል።
በመቐለዎች ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ የተጀመረው የመጀመርያው እጋማሽ ሁለት ግቦችን ማስተናገድ ችሏል፤የጨዋታው የመጀመርያ ጎል ከቀኝ መስመር ስዩም ተስፋዬ ያሻማውን ኳስ ነፃ እቋቋም ላይ የነበረው ያሬድ ከበደ ሊያስቆጥረው ችሏል።

ከግቡ መቆጠር በኃላ ወደ ቀኝ መስመር ያደላው የመቐለ ማጥቃት እንቅስቃሴ የቀጠለ ሲሆን እማኑኤል ገ/ሚካኤል ከቀኝ መስመር ይዞት የገባውን ኳስ ለሳሙኤል ሳሊሶ አቀብሎት ሳሙኤል በጥሩ እጨራረስ የመቐለን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ እድርጎታል።አዲስ ጊደይ ላይ ትኩረት ያደረገው የሲዳማ ማጥቃት እንቅስቃሴ ብዙ ሙከራዎችን ሳያደርግ ተጠናቋል።

ተመጣጣኝ ፋክክር፣ለማመን ሚከብዱ የመስመር ዳኞች ስህተት በታየበት ሁለተኛው ኣጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች የግብ እድሎችን መፍጠር ችለዋል።በ47 ኛው ደቂቃ ላይ ኣሚን ነስሩ በሰራው ጥፋት የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት አዲስ ግደይ እስቆጥሮ ሲዳማዎችን ወደ ጨዋታው ቢመልስም ጨዋታው ላይ ጥሩ የተንቀሳቀሰው ኣማኑኤል ገ/ሚካኤል ከዮናስ ገረመው የተቀበለውን ኳስ በሚገባ በመጠቀም የመቐለ 70 እንደርታን እሸናፊነትን እረጋጥዋል።
ውጤቱን ተከትሎ መቐለ 70 እንደርታ በ11 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሲዳማ ቡና በ13 ነጥብ ሥስተኛ ደረጃን ይዟል።
[team_standings 17713]
አስተያየት ይስጡ