በትግራይ ስታድየም የተካሄደው የሰሜን ደርቢ በሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝ ፋክክር የታየበት ሲሆን ወልዋሎዎች ጅማ ኣባጅፋርን ከገጠመው ቡድን ኣስራት መገርሳን በኣማኑኤል ጎበና ሲቀይሩ እጼዎቹ ኣምሳሉ ጥላሁንን በሰለሞን ሃብቴ ቀይረዋል።
በሁለቱም ቡድኖች በኩል ጥሩ የኳስ ቅብብል የታየበት የመጀመርያው ኣጋማሽ ብዙ ሙከራዎችን ባያስተናግድም ወልዋሎዎች በግራ መስመር በኤፍሬም እሻሞ ና ብርሃኑ ቦጋለ በኩል በሚያደርጉዋቸው እንቅስቃሴዎች የተሻለ የግብ ማግባት እድሎችን መፍጠር ችለዋል።ፋሲሎችም ከራሳቸው ሜዳ በእጭር ቅብብል ለማለፍ ያደረጉት ጥረት ሊሳካላቸው ኣልቻለም።
- ማሰታውቂያ -
ሁለተኛው ኣጋማሽ ከድር ኩሊባሊን በኤፍሬም እለሙ የቀየሩት ፋሲሎች ከመጀመርያው ኣጋማሽ የተሻለ መንቀሳቀስ ችለዋል።በተለይ በሃብታሙ ተኸስተ እና ኤፍሬም አለሙ መሃል ላይ የነበራቸው ጥምረት ሚደነቅ ነበር የዚህ ጥምረት ውጤት ከጥሩ ቅብብል ከመሃል ተነስቶ እብዱራህማን ሙባረክ ያባከነው ኳስ ተጠቃሽ ናቸው።ቢጫ ለባሾቹ ወልዋሎዎችም ከመጀመርያው እጋማሽ እንጻር ቀዝቀዝ ቢሉም በእማኑኤል ጎበና እንዲሁም በኤፍሬም አሻሞ አማካኝነት አስደንጋጭ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል።
ከእንድ ዓመት በኃላ የትግራይና የአማራ ክልል ክለቦችን በየሜዳቸው እንዲጫወቱ ከተስማሙ በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ የተካሄደው ጨዋታ ጥሩ ፋክክር ቢያስተናግድም ያለ ምንም ግብ በኣቻ ውጤት ተጠናቋል።