መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ መቐለ ከተማ አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትንና የቡድን መሪውን አሰናብቷል 
መቐለ ከተማ

መቐለ ከተማ አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትንና የቡድን መሪውን አሰናብቷል 

አጋራ
አጋራ

የመቐለ ከተማ እግር ኳስ ቡድን የአመራር ቦርድ በዛሬው እለት አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን  እና የክለቡ የቡድን መሪ የሆኑትን አቶ መኮንን ጎዳፋይን ከሀላፊነታቸው  አሰናብቷል ፡፡

አሰልጣኙንን ና የቡድን መሪውን ከሀላፊነት ለማንሳት እንደ ምክኒያት፡የተጠቀሰው ባሰለፍነው ሳምንት በአዲግራት ከተማ የመስቀል ዋንጫ በሚል  ስያሜ በነበረው ውድድር ሶስት የትግራይ ክልል ክለቦች ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ ፤መቐለ ከተማ ፤ሽረ ስሁል እንዲሁም ከአዲስአበባ መከላከያ ተገጋባዥ እንደነበር እሚታወስ ነው፡፡  በዚህ መሠረት  ለዋንጫ መድረስ የቻሉት ወልዋሎ አዲግራት ዮ ከ መቐለ ከተማ ሲሆኑ በጨዋታው ቀን ሁለቱም ቡድኖች ወደሜዳ ከገቡ በኃላ በተወሰኑ ደጋፊዎች መካከል ከስታዲየሙ የመቀመጫ ቦታ ጋር የተወሰኑ  ያለመግባባቶች እንደነበሩ እና ጨዋታው ሊጀመር ሲል አሰልጣኙ እና የቡድኑ መሪ ተጨዋቾቻቸው ከሜድ እንዲወጡ እንዳይጫወቱ በመንገር ጨዋታው እንዲቋረጥ ማድረጋቸው  እንደምክኒያት  የቦርዱ ስብሰባ ላይ  ከነበሩ የሀትሪክ ስፖርት እማኞች ገልፀዋል፡፡

አሰልጣኙን ለማናገር ያደረግነው ጥረት ከስልክ ኔትወርክ ችግር ጋር በተያያዘ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ፡፡

አሰለጣኝ ጌታቸው ዳዊት ከዚህ በፊት ወልዋሎ አዲግራትን ፤ ሽረ እንዳስላሴ ደደቢት  ማሰልጠናቸው ይታወቃል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቐለ ከተማዜናዎች

መቐለ ላይ ሀትሪክ ተሰራ ኦኪኪ አፎላቢ ሀዋሳ ላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።

መቐለ ላይ ሀትሪክ ተሰራ ኦኪኪ አፎላቢ ሀዋሳ ላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ...

መቐለ ከተማዜናዎች

አዲስ የተመሰረተው የትግራይ አሰልጣኞች ማህበር የጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ!

  የትግራይ አሰልጣኞች ማህበር ትናንት ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ...

መቐለ ከተማሪፖርትዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

ሪፖርት| ባህርዳር ከተማ የሊጉ መሪ መቐለ 70እንደርታ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል

ባህርዳር ከተማ ና መቐለ 70 እንደርታ ያገናኘው የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ በባህርዳር ከተማ...