መነሻ ገጽ Africa ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ
Africaሴካፋዜናዎች

ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

አጋራ
አጋራ

በሴካፋ ተካፋይ ለሆነው የኢትዮጵያ ከ23ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ።
ከ23 ዓመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት የእግር ኳስ ውድድር ከሰኔ 26/2013 እስከ ሐምሌ 11/2013ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ምክትሎቹ የሚመራ ሲሆን ለ35 ተጫዋቾችም ጥሪ አድርጓል። ወደ አፍሪካ ዋንጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲያልፍ የቡድኑ አባላት ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል እድሚያቸው በብሔራዊ ቡድኑ እንዲካተቱ የሚፈቅድላቸው 5 ተጫዋቾች ቡድኑ ልምምድ ከጀመረ ሰባት ቀናት በኋላ ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ ታውቋል። ምርጫው ከ13ቱም የፕሪሚየር ሊግ እና ከ4 ከፍተኛ ሊግ ክለቦች ተደርጓል።
ጥሪ የተደረገላቸው የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ሰኔ 04/2013 ከጠዋቱ 4 ሰዓት ወሎ ሰፈር በሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ በመገኘት ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
  2. የልደት የምስክር ወረቀት ከጀርባው ማህተም የተደረገበት
  3. ፓስፖርት ያላቸው ተጫዋቾች ፓስፖርት ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል።
    ብሔራዊ ቡድኑ በ3 የተለያዩ ጊዜያት በዋና አሰልጣኙ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን ጋዜጣዊ መግለጫውም
  4. ቡድኑ ሲሰበሰብ ምርጫውን እና ቀጣይ ዝግጅቱን በተመለከተ
  5. በዝግጅት መሃል የሚመቻች ጋዜጣዊ መግለጫ
  6. የሴካፋ ውድድር ከመጀመሩ በፊት
    ጥሪውን ፌዴሬሽኑ የሚዲያ አካላት እንዲያውቁት የሚያደርግ ሲሆን፤ የብሔራዊ ቡድኑን ዝግጅት ብቻ ቪዲዮ እና ምስል የሚዲያ አካላት ፕሮግራም በማሲያዝ መውሰድ ይችላሉ።
    የሚከተሉት ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል።
    ተ/ቁ ሙሉስም ክለብ የመጫወቻ ቦታ
    1 ፋሲል ገ/ሚካኤል ሰበታ ከነማ ግብ ጠባቂ
    2 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ ሰበታ ከነማ አማካይ
    3 ዱሬሳ ሹቤሳ ሰበታ ከነማ የመስመር አጥቂ
    4 ሀ/ሚካኤል አደፍርስ ሰበታ ከነማ የግራ ተከላካይ
    5 አብድልከሪም ወርቁ ወልቂጤ ከነማ አማካይ
    6 ያሬድ ታደስ ወልቂጤ ከነማ አማካይ
    7 ፍቅሩ ውዴሳ ሲዳማ ቡና ግብጠባቂ
    8 ብርሀኑ አሻሞ ሲዳማ ቡና የተከላካይ አማካይ
    9 አማኑኤል እንዳለ ሲዳማ ቡና የቀኝ ተከላካይ
    10 ይገዙ ቦጋለ ሲዳማ ቡና አጥቂ
    11 ኪሩቤል ሃይሉ ፋሲል ከነማ የተከላካይ አማካይ
    12 ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማ የመስመር አጥቂ
    13 አለምብርሀን ይግዛው ፋሲል ከነማ የመስመር አጥቂ
    14 ሀይሌ ገብረተንሳይ ኢት/ቡና የቀኝ ተከላካይ
    15 ሬድዋን ናስር ኢት/ቡና የተከላካይ አማካኝ
    16 ዊሊያም ሰለሞን ኢት/ቡና አማካኝ
    17 መናፍ አወል ባህርዳር ከነማ የመሃል ተከላካይ
    18 ሰለሞን ውዴሳ ባህርዳር ከነማ የመሃል ተከላካይ
    19 ብሩክ በየነ ሀዋሳ ከነማ አጥቂ
    20 ወንድማገኝ ሀይሉ ሃዋሳ ከነማ አማካኝ
    21 መስፍን ታፈሰ ሀዋሳ ከነማ አጥቂ
    22 ቸርነት ጉግሳ ወላይታ ዲቻ የመስመር አጥቂ
    23 ስንታየሁ መንግስቱ ወላይታ ዲቻ አጥቂ
    24 በረከት ወልዴ ወላይታ ዲቻ አማካይ
    25 አቡበከር ኑሪ ጅማ አባ ጅፋር ግብጠባቂ
    26 ቤካም አብደላ ጅማ አባ ጅፋር የመስመር አጥቂ
    27 አማኑኤል ተርፋ ቅ/ጊዮርጊስ የመሃል ተከላካይ
    28 አብዲሳ ጀማል አዳማ ከነማ የመስመር አጥቂ
    29 ሙዲን ሙሳ ድሬደዋ ከነማ የመስመር አጥቂ
    30 ፀጋሰው ዴማሞ ሀዲያ ሆሳና ተከላካይ
    31 ደስታ ዋሚሾ ሀዲያ ሆሳና አጥቂ
    32 ወልደአማኑኤል ጌቱ መብራት ሀይል ተከላካይ
    33 እያሱ ለገሰ አዲስ አበባ የመሃል ተከላካይ
    34 ኤርሚያስ በላይ አርባምንጭ ከነማ የተከላካይ አማካይ
    35 ታምራት ዳኘ ኢት/መድህን ግብ ጠባቂ
አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...