ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

*……በነገው እትማችን ገብርዬን እንግዳችን አድርገነዋል…. ገብርዬ ማነው ካሉ የፕሪሚየር ሊጉ ተከታታይ አይደሉም ማለት ነው….ምክንያቱም ታማኙ ገብርዬ የፋሲል ከነማው ወታደር ያሬድ ባዬ ብቻ መሆኑን የማያውቅ የለማ….”የሻምፒዮኖቹ አምበል መሆኔ እየተሰማኝ ነው…ወልቂጤን አሽንፈን ዋንጫውን እናረጋግጣለን”…ሲልም ይናገራል….

*….በቅዱስ ጊዮርጊስ ቦርድ ከታገዱ ተጨዋቾች መሃል አንዱ የሆነው አስቻለሁ ታመነ የሚሰማውን ለሀትሪክ ተንፍሷል…”ተሳስቻለሁ ለጥፋቴም ይቅርታ እጠይቃለሁ የተከፉብኝን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተሰብ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብሏል….ጸጸት የተሰማው አስቻለሁ ” ከምወደውና ታሪክ ከሰራሁበት ከሰራሁበት ቅዱስ ጊዮርጊስ በዚህ መንገድ በመለያየቴ አዝናለሁ”
በማለትም ተናግሯል።

*….የወላይታ ድቻው ስንታየሁ መንግስቴንም አናግረነዋል….”ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ሁለት ግቦችን ባስቆጥርም ገና እየተማርኩ ያለው ተጨዋች ነኝ” በማለትም ተናግሯል።

*… ኮከቡ የአትሌቲክስ ስፖርት ኩራት ቀነኒሳ በቀለና የኢትዮዽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተጋጭተዋል…ምናልባትም በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላናየው የምንችልበት ገጠመኝም አለ… በቀጥታ ወክሉኝ እንቢ ካላችሁ ደግሞ እንቢታችሁን በደብዳቤ አሳውቁኝም ብሏል…

ከውጪ ዘገባዎቻችን:-

*…. ስለ ምርጡ የጨዋታ አቀጣጣይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ የምንላችሁ አለ….እሱ ደግሞ…”ክርስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል ሜሲ ለኔ ልዩ ናቸው” ሲልም ለሁለቱ የምድራችን ኮከቦች ያለውን ክብር ገልጿል…

*…. የቸልሲው ፑሊሲችና የሪያል ማድሪዱ ማርሴሎ የቃላት ጦርነታቸውን አጧጡፈውትል….ፑሊሲች “ከሪያል ማድሪድ ጋር ያልጨረስኩት የቤት ስራ አለብኝ” ሲል ማርሴሎ በበኩሉ ” ከቸልሲ ጋር የምናደርገው የቤት ስራ የተለየ ነው” በማለት ምላሹን ሰጥቷል።

*….በቀጣዩ ሳምንት ተጠባቂ ስለሆኑት ስለ ሻምፒዮንስ ሊግና ዩሮፓ ሊግ ወሳኝ የመልስ ጨዋታዎችና ምሽቶች ያዘጋጀነው ዘገባ አለ…..

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *